ትንቢተ ዘካርያስ 9

AMHNIVአማርኛ17 ጥቅሶች3:47 አዳምጥ
አዳምጥ 3:47 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1የእግዚአብሔር ቃል ንግር በሴድራክ ምድር ላይ ይወርድበታል፤ በደማስቆም ላይ ያርፍበታል፤ የሰዎችና የእስራኤል ነገዶች ሁሉ ዐይን፣ በእግዚአብሔር ላይ ዐርፎአልና።

2ደግሞም በአዋሳኟ በሐማት፣ ጥበበኞች ቢሆኑም እንኳ በጢሮስና በሲዶና ላይ ያርፍባቸዋል።

3ጢሮስ ለራሷ ምሽግ ሠርታለች፤ ብሩን እንደ ዐፈር ወርቁንም እንደ መንገድ ላይ ትቢያ ቈልላለች።

4ጌታ ግን ሀብቷን ይወስዳል፤ በባሕር ያላትንም ኀይል ይደምስሳል፤ እርሷም በእሳት ፈጽማ ትጠፋለች።

5አስቀሎና አይታ ትርዳለች፤ ጋዛ በሥቃይ ትቃትታለች፤ አቃሮናም እንደዚሁ ትሠቃያለች፤ ተስፋዋ ይመነምናልና። ጋዛ ንጉሥዋን ታጣለች፤ አስቀሎናም ባድማ ትሆናለች።

6ድብልቅ ሕዝቦች አዛጦንን ይይዛሉ፤ የፍልስጥኤማውያንንም ትምክሕት እቈርጣለሁ።

7ደሙን ከአፋቸው፣ የተከለከለውንም ምግብ ከመንጋጋቸው አወጣለሁ። የተረፉት ለአምላካችን ይሆናሉ፤ በይሁዳም አለቆች ይሆናሉ፤ አቃሮንም እንደ ኢያቡሳዊ ይሆናል።

8እኔ ግን ቤቴን ከዘራፊ ኀይሎች እጠብቃለሁ፤ ጨቋኝ ከእንግዲህ ሕዝቤን አይወርስም፤ አሁን ነቅቼ እጠብቃለሁና።

9አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፤ እጅግ ደስ ይበልሽ፤ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፤ እልል በዪ፤ እነሆ፤ ጻድቁና አዳኙ ንጉሥሽ፣ ትሑት ሆኖ፣ በአህያ ላይ ተቀምጦ፣ በአህያ ግልገል፣ በውርንጫዪቱ ላይ ሆኖ ወደ አንቺ ይመጣል።

10ሠረገሎችን ከኤፍሬም፣ የጦር ፈረሶችን ከኢየሩሳሌም እወስዳለሁ፤ የጦርነቱም ቀስት ይሰበራል፤ ሰላምን ለአሕዛብ ያውጃል፤ ግዛቱም ከባሕር እስከ ባሕር፣ ከወንዙም እስከ ምድር ዳር ድረስ ይዘረጋል።

11ለአንቺ ደግሞ፣ ከአንቺ ጋር ከገባሁት የደም ቃል ኪዳን የተነሣ፣ እስረኞችሽን ውሃ ከሌለበት ጒድጓድ ነጻ እለቃቸዋለሁ።

12እናንት በተስፋ የምትኖሩ እስረኞች፤ ወደ ምሽጎቻችሁ ተመለሱ፤ አሁንም ቢሆን ሁለት ዕጥፍ አድርጌ እንደምመልስላችሁ እናገራለሁ።

13ቀስቴን እንደ ገተርሁ፣ ይሁዳን እገትረዋለሁ፤ ኤፍሬምንም ፍላጻ አደርገዋለሁ፤ ጽዮን ሆይ፤ ልጆችሽን አስነሣለሁ፤ ግሪክ ሆይ፤ በአንቺ ልጆች ላይ ይነሣሉ፤ እንደ ተዋጊ ሰይፍም አደርግሻለሁ።

14እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ ይገለጣል፤ ፍላጻውም እንደ መብረቅ ይወጣል፤ ጌታ እግዚአብሔር መለከት ይነፋል፤ በደቡብም ዐውሎ ንፋስ ውስጥ ይጓዛል፤

15እግዚአብሔር ጸባኦትም ይከልላቸዋል፤ ጠላቶቻቸውን ይደመስሳሉ፤ በድንጋይ ወንጭፍም ያሸንፋሉ፤ ይጠጣሉ፤ በወይን ጠጅ እንደ ሰከረ ሰው ይጮኻሉ፤ የመሠዊያውን ማእዘኖች ለመርጨት፣ እንደ ተዘጋጀ ዕቃ፣ እነርሱም እንደዚሁ ተሞልተዋል።

16ሕዝቡን የራሱ መንጋ አድርጎ በዚያ ቀን አምላካቸው እግዚአብሔር ያድናቸዋል። በአክሊል ላይ እንዳለ ዕንቍ፣ በገዛ ምድሩ ላይ ያብለጨልጫሉ።

17እንዴት ውብና አስደናቂ ይሆናሉ፤ እህል ጎልማሶችን፣ አዲስ የወይን ጠጅም ቈነጃጅትን ያሳምራል።

ማብራሪያ

9:1-8 እዚህ ላይ በበርካታ ሕዝቦች ላይ የተነገሩ ፍርዶች ተዘርዝረዋል። መቄዶናውያንና የአሌክሳንደር ተተኪዎች በእነዚህ አገሮች ጦርነት ውስጥ ሳሉ፣ ጌታ ሕዝቡን እንደሚጠብቅ ቃል ገብቷል። የእግዚአብሔር ቤት በጠላት አገር መካከል ይገኛል፤ ቤተ ክርስቲያኑም በእሾህ መካከል እንዳለች ጽጌረዳ ናት። የእግዚአብሔር ኃይልና ቸርነት በእርሷ ልዩ ጥበቃ ውስጥ ይታያል። ጌታ በቤተ ክርስቲያኑ ዙሪያ ይሰፍራል፤ የትዕቢተኞች ተቃዋሚዎች ሠራዊት ሲያልፍና ሲመለስም ዓይኖቹ በእርሷ ላይ ይጠብቃሉ፣ ስለዚህም ሊያሸንፏት አይችሉም። ብዙም ሳይቆይ ደግሞ ምንም ዓይነት አስጨናቂ (ግብር ሰብሳቢ) በእርሷ ዘንድ ዳግመኛ የማያልፍበት ጊዜ ይመጣል።

9:9-17 ነቢዩ ስለ መሲሑ መምጣት በደስታ ይገልጣል፤ እርሱም ጥንቶቹ አይሁድ ይህን ትንቢት ስለ እርሱ እንደሆነ የፈቱት ነው። ኢየሩሳሌም ሲገባም በሕዝቡ ሁለንተናዊ ሆሣዕና መካከለ የንጉሣቸውን ባህርይ ተጎናጸፈ። ነገር ግን መንግሥቱ መንፈሳዊ መንግሥት ነው። በውጫዊ ኃይል ወይም በሥጋዊ የጦር መሣሪያ አይራመድም። ወንጌሉ ለዓለም ይሰበካል፤ በአሕዛብም ዘንድ ተቀባይነትን ያገኛል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG የእግዚአብሔር ቃል ሸክም በሴድራክ ምድር ላይ ነው፥ በደማስቆም ላይ ያርፋል፤ የእግዚአብሔር ዓይን ወደ ሰውና ወደ እስራኤል ነገድ ሁሉ ዘንድ ነው፤ አማርኛ ENGNIV The word of the Lord is against the land of Hadrach and will rest upon Damascus– for the eyes of men and all the tribes… English BCV ፆር ቃል እግዚኣብሄር ኣብ ምድሪ ሴድራክ እዩ፤ ኣብ ልዕሊ ደማስቆውን ይዓርፍ፤ ዓይኒ እግዚኣብሄር ከዓ፥ ኣብ ልዕሊ ሰባትን ኣብ ልዕሊ ዅሉ ነገድ እስራኤልን እዩ። ትግርኛ GAZBIB Dubbiin Waaqayyo waa'ee biyya Hadraakiif dubbate mandara Damaasqoo irras in ga'e; iji namoota kan biraa, iji gosoota Is… Afaan Oromoo BCV GIZ ተረፈ ቃለ እግዚአብሔር በምድረ ሴድራ ወደማስቆ መሥዋዕቱ ለእግዚአብሔር ወኵሉ ሕዝበ እስራኤል። giz GAZGAZ Dubbiin Waaqayyo waa'ee biyya Hadraakiif dubbate mandara Damaasqoo irras in ga'e; iji namoota kan biraa, iji gosoota Is… Afaan Oromoo BCV aksum ፆር ቃል እግዚኣብሄር ኣብ ምድሪ ሴድራክ እዩ፤ ኣብ ልዕሊ ደማስቆውን ይዓርፍ፤ ዓይኒ እግዚኣብሄር ከዓ፥ ኣብ ልዕሊ ሰባትን ኣብ ልዕሊ ዅሉ ነገድ እስራኤልን እዩ። ትግርኛ SWAHSUV Ufunuo wa neno la Bwana, lililosemwa juu ya nchi ya Hadraki, na Dameski itakuwa mahali pake pa kustarehe; kwa maana jic… Kiswahili