ትንቢተ ዘካርያስ 12

AMHEVGአማርኛ14 ጥቅሶች2:43 አዳምጥ
አዳምጥ 2:43 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ስለ እስራኤል የተነገረ የእግዚአብሔር ቃል ሸክም ይህ ነው። ሰማያትን የዘረጋ፥ ምድርንም የመሠረተ፥ የሰውንም መንፈስ በውስጡ የሠራ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦

2“እነሆ፥ ኢየሩሳሌምን በዙሪያዋ ላሉት ለአሕዛብ ሁሉ የመንገድገድ ዋንጫ አደርጋታለሁ፤ ደግሞም ኢየሩሳሌም ስትከበብ በይሁዳ ላይ እንዲሁ ይሆናል።

3በዚያም ቀን ኢየሩሳሌምን ለአሕዛብ ሁሉ ከባድ ድንጋይ አደርጋታለሁ፤ የሚሸከሙአት ሁሉ እጅግ ይቈስላሉ፤ የምድርም አሕዛብ ሁሉ በላይዋ ላይ ይከማቻሉ።

4“በዚያ ቀን፥ ይላል እግዚአብሔር፥ ፈረስን ሁሉ በድንጋጤ፥ ተቀማጭንም በእብድነት እመታለሁ፤ ዓይኖቼንም በይሁዳ ላይ እከፍታለሁ፥ የአሕዛብንም ፈረሶች ሁሉ በዕውርነት እመታለሁ።

5የይሁዳም አለቆች በልባቸው፦ ‘በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ በአምላካቸው በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ብርታት አለ፡’ ይላሉ።

6“በዚያ ቀን የይሁዳን አለቆች በእንጨት መካከል እንዳለ ትንታግ፥ በነዶችም መካከል እንዳለ እንደ ፋና ነበልባል አደርጋቸዋለሁ፤ በቀኝና በግራ በዙሪያ ያሉትን አሕዛብ ሁሉ ይበላሉ፤ ከዚያም ወዲያ ኢየሩሳሌም በስፍራዋ በኢየሩሳሌም ትኖራለች።

7እግዚአብሔርም የዳዊት ቤት ክብርና የኢየሩሳሌም ሰዎች ክብር በይሁዳ ክብር ላይ እንዳይታበይ የይሁዳን ድንኳኖች አስቀድሞ ያድናል።

8“በዚያ ቀን እግዚአብሔር በኢየሩሳሌም ለሚኖሩት ይመክትላቸዋል፤ በዚያም ቀን ከእነርሱ መካከል ደካማው እንደ ዳዊት ይሆናል፤ የዳዊትም ቤት በፊታቸው እንደ እግዚአብሔር መልአክ እንደ አምላክ ይሆናል።

9በዚያም ቀን በኢየሩሳሌም ላይ የሚመጡትን አሕዛብ ሁሉ ለማጥፋት እጋደላለሁ።

10“በዳዊትም ቤት ላይ፥ በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ላይ፥ የሞገስንና የልመናን መንፈስ አፈስሳለሁ፤ ወደ እርሱም ወደ ወጉት ይመለከታሉ፤ ሰውም ለአንድያ ልጁ እንደሚያለቅስ ያለቅሱለታል፥ ሰውም ለበኵር ልጁ እንደሚያዝን በመራራ ኀዘን ያዝኑለታል።

11“በዚያ ቀን በመጊዶን ሜዳ እንደ ነበረው እንደ ሐዳድሪሞን ልቅሶ ታላቅ ልቅሶ በኢየሩሳሌም ይሆናል።

12ምድሪቱም ታለቅሳለች፤ እያንዳንዱ ወገን ለብቻው፥ የዳዊት ቤት ወገን ለብቻው፥ ሴቶቻቸውም ለብቻቸው፤ የናታን ቤት ወገን ለብቻው፥ ሴቶቻቸውም ለብቻቸው፤

13የሌዊ ቤት ወገን ለብቻው፥ ሴቶቻቸውም ለብቻቸው፤ የሰሜኢ ወገን ለብቻው፥ ሴቶቻቸውም ለብቻቸው፤

14የቀሩት ወገኖች ሁሉ እያንዳንዱ ወገን ለብቻው፥ ሴቶቻቸውም ለብቻቸው ያለቅሳሉ።”

ማብራሪያ

12:1-8 እዚህ ጋር የቀረበው መለኮታዊ ትንቢት ለቤተ ክርስቲያን ጠላቶች ሁሉ ከባድ ሸክም ይሆናል። ነገር ግን ለእስራኤል ነው፤ ለመጽናናታቸውና ለጥቅማቸው ሲባል ነው። እግዚአብሔር የቤተ ክርስቲያን ጠላቶችን ምክር ከንቱ እንደሚያደርግና ጽናታቸውን እንደሚያደክም ተስፋ ተሰጥቷል። ትክክለኛው ትርጉም ግልጽ አይደለም፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ብዙውን ጊዜ ድሆችንና የተናቁትን በመጥራት ነው የሚጀምረው፤ በዚያም ቀን ደካሞችም ጭምር ዳዊትን ይመስላሉ፣ በጽናትም ሆነ በሌላው መልካም ነገር ሁሉ በልጠው ይታያሉ። በእርግጥም፣ የክርስቲያኖች ምሳሌዎችና ሥራዎች በእንጨት መካከል እንዳለ እሳት፣ በነዶ ውስጥ እንዳለች ችቦ ሆነው፣ የመለኮታዊ ፍቅርን ነበልባል ለኩሰው፣ ሃይማኖትን ወደ ቀኝና ወደ ግራ እንዲያሰራጩ የሚመኝ ነው።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV This is the word of the Lord concerning Israel. The Lord, who stretches out the heavens, who lays the foundation of the… English BCV ስለ እስራኤል ዝተነግረ ፆር ቃል እግዚኣብሄር እዙይ እዩ፤ ንሰማያት ዝዘርገሐ፥ ንምድሪ ዝመስረተ፥ ንመንፈስ ሰብውን ኣብ ውሽጡ ዝፈጠረ እግዚኣብሄር ከምዙይ ይብል፦ ትግርኛ GAZBIB Dubbiin Waaqayyo waa'ee Israa'eliif dubbate kanatti fufee jira; Waaqayyo inni waaqota diriirse, inni hundee lafaa kaa'e… Afaan Oromoo BCV GIZ ተረፈ ቃለ እግዚአብሔር ላዕለ እስራኤል፤ ይቤ እግዚአብሔር፦ ዘሰፍሐ ሰማየ ወሣረረ ምድረ ወይፈጥር መንፈስ ላዕለ ሰብእ፤ giz GAZGAZ Dubbiin Waaqayyo waa'ee Israa'eliif dubbate kanatti fufee jira; Waaqayyo inni waaqota diriirse, inni hundee lafaa kaa'e… Afaan Oromoo BCV aksum ስለ እስራኤል ዝተነግረ ፆር ቃል እግዚኣብሄር እዙይ እዩ፤ ንሰማያት ዝዘርገሐ፥ ንምድሪ ዝመስረተ፥ ንመንፈስ ሰብውን ኣብ ውሽጡ ዝፈጠረ እግዚኣብሄር ከምዙይ ይብል፦ ትግርኛ AMHNIV ስለ እስራኤል የተነገረው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው፤ ሰማያትን የዘረጋ፣ ምድርን የመሠረተ የሰውንም መንፈስ በውስጡ የሠራ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ አማርኛ SWAHSUV Ufunuo wa neno la Bwana juu ya Israeli. Haya ndiyo asemayo Bwana, azitandaye mbingu, auwekaye msingi wa dunia, aiumbaye… Kiswahili