ትንቢተ ዘካርያስ 12

AMHNIVአማርኛ14 ጥቅሶች3:04 አዳምጥ
አዳምጥ 3:04 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ስለ እስራኤል የተነገረው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው፤ ሰማያትን የዘረጋ፣ ምድርን የመሠረተ የሰውንም መንፈስ በውስጡ የሠራ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤

2“ኢየሩሳሌምን በዙሪያዋ ላሉት ሕዝቦች ሁሉ የሚያንገደግድ ጽዋ አደርጋታለሁ፤ ይሁዳም እንደ ኢየሩሳሌም ሁሉ ትከበባለች።

3የምድር አሕዛብ ሁሉ በእርሷ ላይ በሚሰበሰቡበት በዚያ ቀን፣ ኢየሩሳሌምን ለአሕዛብ ሁሉ የማይነቃነቅ ዐለት አደርጋታለሁ፤ ለማነቃነቅ የሚሞክሩ ሁሉ ራሳቸውን ይጐዳሉ።

4በዚያን ቀን እያንዳንዱን ፈረስ በድንጋጤ፣ የተቀመጡባቸውንም ሰዎች እብደት እመታለሁ” ይላል እግዚአብሔር። “የይሁዳን ቤት በዐይኔ እጠብቃለሁ፤ ነገር ግን የአሕዛብን ፈረሶች ሁሉ አሳውራለሁ።

5የይሁዳ መሪዎች በልባቸው፣ ‘የኢየሩሳሌም ሕዝቦች ብርቱ ናቸው፤ አምላካቸው እግዚአብሔር ጸባኦት ነውና’ ይላሉ።

6“በዚያ ቀን የይሁዳን መሪዎች በዕንጨት ክምር ውስጥ እንዳለ የእሳት ምድጃ፣ በነዶም መካከል እንዳለ የፋና ነበልባል አደርጋቸዋለሁ፤ በግራና በቀኝ ዙሪያውን ያሉትን ሕዝቦች ይበላሉ፤ ኢየሩሳሌም ግን ከስፍራዋ ንቅንቅ አትልም።

7“የዳዊት ቤትና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ክብር ከይሁዳ ክብር እንዳይበልጥ እግዚአብሔር በመጀመሪያ የይሁዳን መኖሪያዎች ያድናል።

8ከመካከላቸው እጅግ ደካማ የሆነው እንደ ዳዊት፣ የዳዊት ቤትም ፊት ፊታቸው እንደሚሄድ እንደ እግዚአብሔር መልአክ፣ እንደ አምላክ ይሆንላቸው ዘንድ በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን እግዚአብሔር ይከልላቸዋል።

9በዚያ ቀን ኢየሩሳሌምን በወጓት አሕዛብ ሁሉ ላይ እወጣለሁ።

10“በዳዊት ቤትና በኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ላይ የርኅራኄና የልመና መንፈስ አፈሳለሁ፤ ወደ ወጉኝ ወደ እኔም ይመለከታሉ፤ እነርሱም ለአንድያ ልጅ እንደሚለቀስ ያለቅሱለታል፤ ለበኵር ልጅ ምርር ተብሎ እንደሚለቀስም አምርረው ያለቅሱለታል።”

11በዚያ ቀን በመጊዶን ሜዳ ለሐዳድሪሞን እንደተለቀሰ ሁሉ በኢየሩሳሌም የሚለቀሰውም እንደዚሁ ታላቅ ልቅሶ ይሆናል።

12ምድሪቱ ታለቅሳለች፤ የየነገዱ ወንዶች ለየራሳቸው ያለቅሳሉ፤ ሚስቶቻቸውም ለየራሳቸው ያለቅሳሉ፤ በዚህም ዐይነት የዳዊት ቤት ነገድ ወንዶች ከነሚስቶቻቸው፣ የናታን ቤት ነገድ ወንዶች ከነሚስቶቻቸው፣

13የሌዊ ቤት ነገድ ወንዶች ከነሚስቶቻቸው፣ የሰሜኢ ቤት ነገድ ወንዶች ከነሚስቶቻቸው፣

14የቀሩትም ነገዶች ወንዶች ሁሉ ከነሚስቶቻቸው ያለቅሳሉ።

ማብራሪያ

12:1-8 እዚህ ጋር የቀረበው መለኮታዊ ትንቢት ለቤተ ክርስቲያን ጠላቶች ሁሉ ከባድ ሸክም ይሆናል። ነገር ግን ለእስራኤል ነው፤ ለመጽናናታቸውና ለጥቅማቸው ሲባል ነው። እግዚአብሔር የቤተ ክርስቲያን ጠላቶችን ምክር ከንቱ እንደሚያደርግና ጽናታቸውን እንደሚያደክም ተስፋ ተሰጥቷል። ትክክለኛው ትርጉም ግልጽ አይደለም፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ብዙውን ጊዜ ድሆችንና የተናቁትን በመጥራት ነው የሚጀምረው፤ በዚያም ቀን ደካሞችም ጭምር ዳዊትን ይመስላሉ፣ በጽናትም ሆነ በሌላው መልካም ነገር ሁሉ በልጠው ይታያሉ። በእርግጥም፣ የክርስቲያኖች ምሳሌዎችና ሥራዎች በእንጨት መካከል እንዳለ እሳት፣ በነዶ ውስጥ እንዳለች ችቦ ሆነው፣ የመለኮታዊ ፍቅርን ነበልባል ለኩሰው፣ ሃይማኖትን ወደ ቀኝና ወደ ግራ እንዲያሰራጩ የሚመኝ ነው።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG ስለ እስራኤል የተነገረ የእግዚአብሔር ቃል ሸክም ይህ ነው። ሰማያትን የዘረጋ፥ ምድርንም የመሠረተ፥ የሰውንም መንፈስ በውስጡ የሠራ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ አማርኛ ENGNIV This is the word of the Lord concerning Israel. The Lord, who stretches out the heavens, who lays the foundation of the… English BCV ስለ እስራኤል ዝተነግረ ፆር ቃል እግዚኣብሄር እዙይ እዩ፤ ንሰማያት ዝዘርገሐ፥ ንምድሪ ዝመስረተ፥ ንመንፈስ ሰብውን ኣብ ውሽጡ ዝፈጠረ እግዚኣብሄር ከምዙይ ይብል፦ ትግርኛ GAZBIB Dubbiin Waaqayyo waa'ee Israa'eliif dubbate kanatti fufee jira; Waaqayyo inni waaqota diriirse, inni hundee lafaa kaa'e… Afaan Oromoo BCV GIZ ተረፈ ቃለ እግዚአብሔር ላዕለ እስራኤል፤ ይቤ እግዚአብሔር፦ ዘሰፍሐ ሰማየ ወሣረረ ምድረ ወይፈጥር መንፈስ ላዕለ ሰብእ፤ giz GAZGAZ Dubbiin Waaqayyo waa'ee Israa'eliif dubbate kanatti fufee jira; Waaqayyo inni waaqota diriirse, inni hundee lafaa kaa'e… Afaan Oromoo BCV aksum ስለ እስራኤል ዝተነግረ ፆር ቃል እግዚኣብሄር እዙይ እዩ፤ ንሰማያት ዝዘርገሐ፥ ንምድሪ ዝመስረተ፥ ንመንፈስ ሰብውን ኣብ ውሽጡ ዝፈጠረ እግዚኣብሄር ከምዙይ ይብል፦ ትግርኛ SWAHSUV Ufunuo wa neno la Bwana juu ya Israeli. Haya ndiyo asemayo Bwana, azitandaye mbingu, auwekaye msingi wa dunia, aiumbaye… Kiswahili