ትንቢተ ዘካርያስ 10

AMHNIVአማርኛ12 ጥቅሶች2:44 አዳምጥ
አዳምጥ 2:44 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1የበልግ ዝናብ እንዲሰጣችሁ እግዚአብሔርን ጠይቁ፤ ማዕበሉን ደመና የሚያደርግ እግዚአብሔር ነው፤ እርሱ ለሰዎች በቂ ዝናብን፣ ለእያንዳንዱም የምድርን ተክል ይሰጣል።

2ተራፊም አሳሳች ነገር ይናገራል፤ ሟርተኞች የሐሰት ራእይ ያያሉ፤ የውሸት ሕልም ይናገራሉ፤ ከንቱ መጽናናት ይሰጣሉ፤ ስለዚህ ሕዝቡ እንደ በጎች ተቅበዘበዙ፤ እረኛ በማጣትም ተጨነቁ።

3“ቍጣዬ በእረኞች ላይ ነዶአል፤ መሪዎችንም እቀጣለሁ፤ እግዚአብሔር ጸባኦት፣ ለመንጋው ለይሁዳ ቤት ይጠነቀቃልና፤ በጦርነትም ጊዜ እንደ ክብሩ ፈረስ ያደርጋቸዋል።

4ከይሁዳ፣ የማእዘን ድንጋይ፣ የድንኳን ካስማ፣ የጦርነት ቀስት፣ ገዥም ሁሉ ይወጣል።

5ጠላትን መንገድ ላይ እንዳለ ጭቃ ይረጋግጣሉ፤ በአንድነት እንደ ጦር ሰልፈኛ ይሆናሉ፤ እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ስለ ሆነ ተዋግተው፤ ፈረሰኞችን ያዋርዳሉ።

6“የይሁዳን ቤት አበረታለሁ፤ የዮሴፍንም ቤት እታደጋለሁ። ስለምራራላቸው፣ ወደቦታቸው እመልሳቸዋለሁ፤ እነርሱም በእኔ እንዳልተተዉ ሰዎች ይሆናሉ፤ እኔ አምላካቸው እግዚአብሔር ነኝና፣ ጸሎታቸውን እሰማለሁ።

7ኤፍሬማውያን እንደ ኀያላን ሰዎች ይሆናሉ፤ ልባቸውም የወይን ጠጅ እንደ ጠጣ ሰው ሐሤት ያደርጋል። ልጆቻቸው ያዩታል፤ ደስተኛም ይሆናሉ፤ ልባቸውም በእግዚአብሔር ደስ ይለዋል።

8በፉጨት እጠራቸዋለሁ፤ በአንድነት እሰበስባቸዋለሁ፤ በእርግጥ እቤዣቸዋለሁ፤ እንደ ቀድሞው ይበዛሉ።

9በሕዝቦች መካከል ብበትናቸውም፣ በሩቅ ምድር ሆነው ያስቡኛል፤ እነርሱና ልጆቻቸው ተርፈው፣ በሕይወት ይመለሳሉ።

10ከግብፅ እመልሳቸዋለሁ፤ ከአሦርም እሰበስባቸዋለሁ፤ ወደ ገለዓድና ወደ ሊባኖስ አመጣቸዋለሁ፤ በቂ ስፍራም አይገኝላቸውም።

11በመከራ ባሕር ውስጥ ያልፋሉ፤ የባሕሩ ማዕበል ጸጥ ይላል፤ የዐባይም ጥልቅ ሁሉ ይደርቃል። የአሦር ትምክሕት ይዋረዳል፤ የግብፅም በትረ መንግሥት ያበቃል።

12በእግዚአብሔር አበረታቸዋለሁ፤ በስሙም ይመላለሳሉ፤” ይላል እግዚአብሔር።

ማብራሪያ

10:1-5

መንፈሳዊ በረከቶች በምድራዊ ብልጽግና ምሳሌያዊ አነጋገሮች ስር ቃል ተገብቶላቸው ነበር። ወቅቱን የጠበቀ ዝናብ ታላቅ ምሕረት ነው፤ ይህም በጣም በሚያስፈልግበት ጊዜ እግዚአብሔርን ልንለምነው የምንችለውና እንዲመጣም ልንጠብቀው የሚገባን ነው። በጸሎታችን ምሕረትን በትክክለኛው ጊዜያቸው ልንለምን ይገባናል። እግዚአብሔር ብሩህ ደመናዎችን ያደርጋል፣ የዝናብ ውሽንፍርንም ይሰጣል። ይህ ምናልባት የመንፈስ ቅዱስን ተጽዕኖዎች በእምነትና በጸሎት ለመሻት የሚያበረታታ ሊሆን ይችላል፤ በእነዚህ አማካኝነት በተስፋዎቹ ውስጥ የቀረቡት በረከቶች የሚገኙና የሚደሰቱባቸው ናቸው። ነቢዩ አባቶቻቸው እንዳደረጉት ለጣዖታት መማጸን የሞኝነት ተግባር እንደሆነ ያሳያል። ጌታ ከመንጋው የተረፈውን በምሕረት ጎበኘ፤ ለግጭትና ለድልም ድፍረታቸውንና ብርታታቸውን ሊያድስ ነበር።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG በኋለኛው ዝናብ ጊዜ ከእግዚአብሔር ዘንድ ዝናቡን ለምኑ፤ እግዚአብሔር መብረቅ ያደርጋል፤ እርሱም የበልግ ዝናብን ለእያንዳንዱም በሜዳ ውስጥ ሣርን ይሰጣል። አማርኛ ENGNIV Ask the Lord for rain in the springtime; it is the Lord who makes the storm clouds. He gives showers of rain to men, an… English BCV ብጊዜ ዳሕረዋይ ዝናም፥ ካብ እግዚኣብሄር ዝናም ለምኑ፤ እግዚኣብሄር መብረቅ ይገብር፤ ዝናምን ንነፍሲ ወከፍ ድማ ሳዕሪ ኣብ ግራት ክህብ እዩ። ትግርኛ GAZBIB Bokkaa ji'a birraa akka isiniif kennuuf Waaqayyoon kadhadhaa! Isatu duumessa bokkaa qabuu fi bokkaa tiifuu namootaaf er… Afaan Oromoo BCV GIZ ወዝናመ ጾደየ ወመፀወ፡ እግዚአብሔር ገብረ ለምትሀተ ዐይን ወይሁቦሙ ዝናመ ተጐን ወይበቍል ሣዕር በገዳም። giz GAZGAZ Bokkaa ji'a birraa akka isiniif kennuuf Waaqayyoon kadhadhaa! Isatu duumessa bokkaa qabuu fi bokkaa tiifuu namootaaf er… Afaan Oromoo BCV aksum ብጊዜ ዳሕረዋይ ዝናም፥ ካብ እግዚኣብሄር ዝናም ለምኑ፤ እግዚኣብሄር መብረቅ ይገብር፤ ዝናምን ንነፍሲ ወከፍ ድማ ሳዕሪ ኣብ ግራት ክህብ እዩ። ትግርኛ SWAHSUV Mwombeni Bwana mvua wakati wa masika, naam, Bwana afanyaye umeme, naye atawapa manyunyu ya mvua, kila mtu atapewa nyasi… Kiswahili