ትንቢተ ዘካርያስ 10

AMHEVGአማርኛ12 ጥቅሶች2:37 አዳምጥ
አዳምጥ 2:37 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1በኋለኛው ዝናብ ጊዜ ከእግዚአብሔር ዘንድ ዝናቡን ለምኑ፤ እግዚአብሔር መብረቅ ያደርጋል፤ እርሱም የበልግ ዝናብን ለእያንዳንዱም በሜዳ ውስጥ ሣርን ይሰጣል።

2ተራፊም ከንቱነትን ተናግረዋልና፥ ምዋርተኞችም ውሸትን አይተዋልና፤ ሕልምንም የሚያዩ በሐሰት ተናግረዋል፥ በከንቱም ያጽናናሉ፤ እረኛም የላቸውምና እንደ በጎች ተቅበዝብዘዋል ተጨንቀውማል።

3ቍጣዬ በእረኞች ላይ ነድዶአል፥ አውራ ፍየሎችንም እቀጣለሁ፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም የይሁዳን ቤት መንጋውን ጐብኝቶአል፥ በሰልፍም ውስጥ እንዳለ እንደ ክብሩ ፈረስ ያደርጋቸዋል።

4ከእርሱ ዘንድ የማዕዘኑ ድንጋይ፥ ከእርሱም ዘንድ ችንካሩ፥ ከእርሱም ዘንድ የሰልፉ ቀስት፥ ከእርሱም ዘንድ አስገባሪው ሁሉ በአንድ ላይ ይመጣሉ።

5በሰልፍም ጊዜ ጠላቶቻቸውን በመንገድ ጭቃ ውስጥ እንደሚረግጡ ኃያላን ይሆናሉ፤ እግዚአብሔርም ከእነርሱ ጋር ነውና ይዋጋሉ፥ ፈረሰኞችም ያፍራሉ።

6ወድጃቸዋለሁና የይሁዳን ቤት አበረታለሁ፥ የዮሴፍንም ቤት አድናለሁ፤ አደላድላቸዋለሁም፤ እመልሳቸዋለሁ፤ እኔም አምላካቸው እግዚአብሔር ነኝና፥ እኔም እሰማቸዋለሁና እንዳልጣልኋቸው ይሆናሉ።

7የኤፍሬምም ሰዎች እንደ ኃያላን ይሆናሉ፥ ልባቸውም የወይን ጠጅ እንደ ጠጣ ሰው ደስ ይለዋል፤ ልጆቻቸውም አይተው ደስ ይላቸዋል፥ ልባቸውም በእግዚአብሔር ሐሤት ያደርጋል።

8ተቤዥቼአቸዋለሁና በፉጨት ጠርቼ እሰበስባቸዋለሁ፤ ቀድሞም በዝተው እንደ ነበሩ ይበዛሉ።

9በአሕዛብም መካከል ብዘራቸው እንኳ በሩቅ አገር ሳሉ ያስቡኛል፥ ከልጆቻቸውም ጋር በሕይወት ይኖራሉ፥ ይመለሱማል።

10ከግብፅም ምድር እመልሳቸዋለሁ፥ ከአሦርም እሰበስባቸዋለሁ፤ ወደ ገለዓድና ወደ ሊባኖስ ምድር አመጣቸዋለሁ፥ የሚበቃም ቦታ አይገኝላቸውም።

11እርሱም በጭንቅ ባሕር ያልፋል፥ የባሕርንም ሞገድ ይመታል፥ የወንዙም ጥልቅ ሁሉ ይደርቃል፤ የአሦርም ትዕቢት ይዋረዳል፥ የግብፅም በትረ መንግሥት ይርቃል።

12በአምላካቸው በእግዚአብሔር አበረታቸዋለሁ፥ በስሙም ይመካሉ፥ ይላል እግዚአብሔር።

ማብራሪያ

10:1-5

መንፈሳዊ በረከቶች በምድራዊ ብልጽግና ምሳሌያዊ አነጋገሮች ስር ቃል ተገብቶላቸው ነበር። ወቅቱን የጠበቀ ዝናብ ታላቅ ምሕረት ነው፤ ይህም በጣም በሚያስፈልግበት ጊዜ እግዚአብሔርን ልንለምነው የምንችለውና እንዲመጣም ልንጠብቀው የሚገባን ነው። በጸሎታችን ምሕረትን በትክክለኛው ጊዜያቸው ልንለምን ይገባናል። እግዚአብሔር ብሩህ ደመናዎችን ያደርጋል፣ የዝናብ ውሽንፍርንም ይሰጣል። ይህ ምናልባት የመንፈስ ቅዱስን ተጽዕኖዎች በእምነትና በጸሎት ለመሻት የሚያበረታታ ሊሆን ይችላል፤ በእነዚህ አማካኝነት በተስፋዎቹ ውስጥ የቀረቡት በረከቶች የሚገኙና የሚደሰቱባቸው ናቸው። ነቢዩ አባቶቻቸው እንዳደረጉት ለጣዖታት መማጸን የሞኝነት ተግባር እንደሆነ ያሳያል። ጌታ ከመንጋው የተረፈውን በምሕረት ጎበኘ፤ ለግጭትና ለድልም ድፍረታቸውንና ብርታታቸውን ሊያድስ ነበር።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV Ask the Lord for rain in the springtime; it is the Lord who makes the storm clouds. He gives showers of rain to men, an… English BCV ብጊዜ ዳሕረዋይ ዝናም፥ ካብ እግዚኣብሄር ዝናም ለምኑ፤ እግዚኣብሄር መብረቅ ይገብር፤ ዝናምን ንነፍሲ ወከፍ ድማ ሳዕሪ ኣብ ግራት ክህብ እዩ። ትግርኛ GAZBIB Bokkaa ji'a birraa akka isiniif kennuuf Waaqayyoon kadhadhaa! Isatu duumessa bokkaa qabuu fi bokkaa tiifuu namootaaf er… Afaan Oromoo BCV GIZ ወዝናመ ጾደየ ወመፀወ፡ እግዚአብሔር ገብረ ለምትሀተ ዐይን ወይሁቦሙ ዝናመ ተጐን ወይበቍል ሣዕር በገዳም። giz GAZGAZ Bokkaa ji'a birraa akka isiniif kennuuf Waaqayyoon kadhadhaa! Isatu duumessa bokkaa qabuu fi bokkaa tiifuu namootaaf er… Afaan Oromoo BCV aksum ብጊዜ ዳሕረዋይ ዝናም፥ ካብ እግዚኣብሄር ዝናም ለምኑ፤ እግዚኣብሄር መብረቅ ይገብር፤ ዝናምን ንነፍሲ ወከፍ ድማ ሳዕሪ ኣብ ግራት ክህብ እዩ። ትግርኛ AMHNIV የበልግ ዝናብ እንዲሰጣችሁ እግዚአብሔርን ጠይቁ፤ ማዕበሉን ደመና የሚያደርግ እግዚአብሔር ነው፤ እርሱ ለሰዎች በቂ ዝናብን፣ ለእያንዳንዱም የምድርን ተክል ይሰጣል። አማርኛ SWAHSUV Mwombeni Bwana mvua wakati wa masika, naam, Bwana afanyaye umeme, naye atawapa manyunyu ya mvua, kila mtu atapewa nyasi… Kiswahili