መኃልየ መኃልይ 5

AMHEVGአማርኛ16 ጥቅሶች2:53 አዳምጥ
አዳምጥ 2:53 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1እኅቴ ሙሽራዬ ሆይ፥ ወደ ገነቴ ገባሁ፥ ከርቤዬን ከሽቱዬ ጋር ለቀምሁ፥ እንጀራዬን ከማሬ ጋር በላሁ፥ የወይን ጠጄን ከወተቴ ጋር ጠጣሁ። ባልንጀሮቼ ሆይ፥ ብሉ፤ ወዳጄ ሆይ፥ ጠጪ እስክትረኪ ድረስ ጠጪ።

2እኔ ተኝቻለሁ፥ ልቤ ግን ነቅቶአል፤ የውዴ ቃል ነው፥ እርሱም ደጁን ይመታል፤ እኅቴ፥ ወዳጄ፥ ርግቤ፥ መደምደሚያዬ ሆይ፥ በራሴ ጠል፥ በቈንዳላዬም የሌሊት ነጠብጣብ፡ ሞልቶበታልና ክፈችልኝ።

3ቀሚሴን አወለቅሁ እንዴት እለብሰዋለሁ? እግሬን ታጠብሁ እንዴት አሳድፈዋለሁ?

4ውዴ እጁን በቀዳዳ ሰደደ፥ አንጀቴም ስለ እርሱ ታወከ።

5ለውዴ እከፍትለት ዘንድ ተነሣሁ፤ እጆቼ በደጅ መወርወሪያ ላይ ከርቤን አፈሰሱ፥ ጣቶቼ ፈሳሹን ከርቤ አንጠበጠቡ።

6ለውዴ ከፈትሁለት፥ ውዴ ግን ፈቀቅ ብሎ አልፎ ነበር። ነፍሴ ከቃሉ የተነሣ ደነገጠች፤ ፈለግሁት፥ አላገኘሁትም፤ ጠራሁት፥ አልመለሰልኝም።

7ከተማይቱን የሚዞሩት ጠባቂዎች አገኙኝ፤ መቱኝ፥ አቈሰሉኝም፤ ቅጥር ጠባቂዎችም የዓይነ ርግብ መሸፈኛዬን ወሰዱት።

8እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፥ አምላችኋለሁ፤ ውዴን ያገኛችሁት እንደ ሆነ፥ እኔ ከፍቅር የተነሣ መታመሜን ንገሩት።

9አንቺ በሴቶች ዘንድ የተዋብሽ ሆይ፥ ከሌላ ወዳጅ ይልቅ ውድሽ ማን ነው? ይህን የሚያህል አምለሽናልና፡ ከሌላ ወዳጅ ይልቅ ውድሽ ማን ነው?

10ውዴ ነጭና ቀይ ነው፥ ከእልፍ የተመረጠ ነው።

11ራሱ ምዝምዝ ወርቅ ነው፤ ቈንዳላው የተዝረፈረፈ ነው፥ እንደ ቁራ ጥቁረትም ጥቁር ነው።

12ዓይኖቹ በሙሉ ፈሳሽ አጠገብ እንዳሉ፡ በወተት እንደ ታጠቡ በፈሳሽ ውኃ አጠገብ እንደ ተቀመጡ፡ እንደ ርግቦች ናቸው።

13ጕንጩና ጕንጩ የሽቱ መደብ፡ እርከን እንዳለበት እንደ ሽቱ አትክልት ናቸው፤ ከንፈሮቹ እንደ አበቦች ናቸው፥ የሚፈስስ ከርቤንም ያንጠበጥባሉ።

14እጆቹ የቢረሌ ፈርጥ እንዳለበት እንደ ወርቅ ቀለበት ናቸው፤ አካሉ ብልሃተኛ እንደ ሠራው፡ በሰንፔር እንዳጌጠ እንደ ዝሆን ጥርስ ነው።

15እግሮቹ በምዝምዝ ወርቅ እንደ ተመሠረቱ፡ እንደ ዕብነ በረድ ምሰሶች ናቸው፤ መልኩ እንደ ሊባኖስና እንደ ዝግባ ዛፍ መልካም ነው።

16አፉ እጅግ ጣፋጭ ነው፥ እርሱም ፈጽሞ ያማረ፤ ነው እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፥ ውዴ ይህ ነው፥ ባልንጀራዬም ይህ ነው።

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV I have come into my garden, my sister, my bride; I have gathered my myrrh with my spice. I have eaten my honeycomb and … English BCV ሓፍተይ፥ መርዓተይ፥ ናብ ገነተይ ኣትየ፥ ከርበይን ምዑዝ ቀመማተይን እእክብ ኣለኹ። ሕብስተይ ምስ መዓረይ፥ ወይነይ ድማ ምስ ፀባይ ሰተኹ። ኣቱም ኣዕርኽተይ፥ ብልዑ፤ ስተዩ፤ ኣቱም ፍቑራት፥… ትግርኛ GAZBIB “Yaa obboleettii ko, kaadhima ko! Ani gara iddoo dhaabaa kootii dhufeera, qumbii koo fi urgooftuu koo walitti qabadheer… Afaan Oromoo BCV GIZ ቦእኩ ውስተ ገነትየ እኅትየ መርዓት አረርኩ ከርቤ ምስለ አፈዋትየ፤ በላዕኩ ኅብስትየ ምስለ መዓርየ፤ ሰተይኩ ወይንየ ምስለ ሐሊብየ፣ በልዑ ካልአንየ፤ ሰትዩ ወሰከሩ ውሉድ አኃውየ። giz GAZGAZ “Yaa obboleettii ko, kaadhima ko! Ani gara iddoo dhaabaa kootii dhufeera, qumbii koo fi urgooftuu koo walitti qabadheer… Afaan Oromoo BCV aksum ሓፍተይ፥ መርዓተይ፥ ናብ ገነተይ ኣትየ፥ ከርበይን ምዑዝ ቀመማተይን እእክብ ኣለኹ። ሕብስተይ ምስ መዓረይ፥ ወይነይ ድማ ምስ ፀባይ ሰተኹ። ኣቱም ኣዕርኽተይ፥ ብልዑ፤ ስተዩ፤ ኣቱም ፍቑራት፥… ትግርኛ AMHNIV እኅቴ ሙሽራዬ፣ ወደ አትክልት ቦታዬ መጥቻለሁ፤ ከርቤዬን ከቅመሜ ጋር ሰብስቤአለሁ፤ የማር እንጀራዬን ከነወለላው በልቻለሁ፤ ወይኔንና ወተቴንም ጠጥቻለሁ። ወዳጆች ሆይ፤ ብሉ፤ ጠጡ፤ እናንት … አማርኛ SWAHSUV Naingia bustanini mwangu, umbu langu, bibi arusi, Nachuma manemane yangu na rihani, Nala sega la asali na asali yangu, … Kiswahili