መኃልየ መኃልይ 5

AMHNIVአማርኛ16 ጥቅሶች3:13 አዳምጥ
አዳምጥ 3:13 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1እኅቴ ሙሽራዬ፣ ወደ አትክልት ቦታዬ መጥቻለሁ፤ ከርቤዬን ከቅመሜ ጋር ሰብስቤአለሁ፤ የማር እንጀራዬን ከነወለላው በልቻለሁ፤ ወይኔንና ወተቴንም ጠጥቻለሁ። ወዳጆች ሆይ፤ ብሉ፤ ጠጡ፤ እናንት ፍቅረኞች ሆይ፤ እስክትረኩ ጠጡ።

2እኔ ተኝቻለሁ፤ ልቤ ግን ነቅቶአል፤ ስሙ! ውዴ በር ያንኳኳል፤ እንዲህ ይላል፤ “እኅቴ ወዳጄ፣ ርግቤ፣ አንቺ እንከን የሌለብሽ፤ ክፈቺልኝ፤ ራሴ በጤዛ፣ ጠጒሬም በሌሊቱ ርጥበት ረስርሶአል።”

3ቀሚሴን አውልቄአለሁ፤ ታዲያ እንዴት እንደ ገና ልልበስ? እግሬን ታጥቤአለሁ፤ እንዴት እንደ ገና ላቈሽሸው?

4ውዴ እጁን በበሩ ቀዳዳ አሾለከ፤ ልቤም ስለ እርሱ ይታወክ ጀመር።

5ለውዴ ልከፍትለት ተነሣሁ፤ በከርቤ ነጠብጣብ የራሱት እጆቼ፣ በከርቤም ፈሳሽ የተነከሩት ጣቶቼ፣ የመወርወሪያውን እጀታ ያዙ።

6ለውዴ ከፈትሁለት፤ ውዴ ግን አልነበረም፤ ሄዶአል፤ በመሄዱም ልቤ ደነገጠ፤ ፈለግሁት፤ ነገር ግን አላገኘሁትም፤ ጠራሁት፤ ነገር ግን አልመለሰልኝም።

7የከተማዪቱም ጠባቂዎች፣ በከተማዪቱ ውስጥ ሲዘዋወሩ አገኙኝ፤ እነዚህ የቅጥሩ ጠባቂዎች፣ ደበደቡኝ፤ አቈሰሉኝ፤ ልብሴንም ገፈፉኝ።

8እናንት የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፤ እማጠናችኋለሁ፤ ውዴን ካገኛችሁት፣ ምን ትሉት መሰላችሁ? በፍቅሩ መታመሜን ንገሩት።

9አንቺ ከሴቶች ሁሉ የተዋብሽ ሆይ፤ ውድሽ ከሌሎች እንዴት ቢበልጥ ነው? እስከዚህ የምትማጠኚንስ፣ ውድሽ ከሌሎች እንዴት ቢበልጥ ነው?

10ውዴ ፍልቅልቅና ደመ ግቡ ነው፤ ከዐሥር ሺሆችም የሚልቅ ነው።

11ራሱ የጠራ ወርቅ፣ ጠጒሩ ዞማ፣ እንደ ቊራም የጠቈረ ነው።

12ዐይኖቹ፣ በጅረት አጠገብ እንዳሉ ርግቦች፣ በወተት የታጠቡ፣ እንደ ዕንቊም ጒብ ጒብ ያሉ ናቸው።

13ጒንጮቹ የሽቱ መዐዛ የሚያመጡ፣ የቅመማ ቅመም መደቦችን ይመስላሉ፤ ከንፈሮቹም ከርቤ እንደሚያንጠባጥቡ፣ ውብ አበቦች ናቸው።

14ክንዶቹ በዕንቊ ፈርጥ ያጌጠ፣ የወርቅ ዘንግን ይመስላሉ፤ ሰውነቱም በሰንፔር ፈርጥ ያጌጠ፣ አምሮ የተሠራ የዝሆን ጥርስን ይመስላል።

15እግሮቹ በንጹሕ ወርቅ መቆሚያ ላይ የተተከሉ፣ የዕብነ በረድ ምሰሶዎችን ይመስላሉ፤ መልኩ እንደ ሊባኖስ ነው፤ እንደ ዝግባ ዛፎቹም ምርጥ ነው።

16አፉ ራሱ ጣፋጭ ነው፤ ሁለንተናውም ያማረ ነው፤ እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፤ ውዴ ይህ ነው፤ ባልንጀራዬም እርሱ ነው።

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG እኅቴ ሙሽራዬ ሆይ፥ ወደ ገነቴ ገባሁ፥ ከርቤዬን ከሽቱዬ ጋር ለቀምሁ፥ እንጀራዬን ከማሬ ጋር በላሁ፥ የወይን ጠጄን ከወተቴ ጋር ጠጣሁ። ባልንጀሮቼ ሆይ፥ ብሉ፤ ወዳጄ ሆይ፥ ጠጪ እስክትረኪ … አማርኛ ENGNIV I have come into my garden, my sister, my bride; I have gathered my myrrh with my spice. I have eaten my honeycomb and … English BCV ሓፍተይ፥ መርዓተይ፥ ናብ ገነተይ ኣትየ፥ ከርበይን ምዑዝ ቀመማተይን እእክብ ኣለኹ። ሕብስተይ ምስ መዓረይ፥ ወይነይ ድማ ምስ ፀባይ ሰተኹ። ኣቱም ኣዕርኽተይ፥ ብልዑ፤ ስተዩ፤ ኣቱም ፍቑራት፥… ትግርኛ GAZBIB “Yaa obboleettii ko, kaadhima ko! Ani gara iddoo dhaabaa kootii dhufeera, qumbii koo fi urgooftuu koo walitti qabadheer… Afaan Oromoo BCV GIZ ቦእኩ ውስተ ገነትየ እኅትየ መርዓት አረርኩ ከርቤ ምስለ አፈዋትየ፤ በላዕኩ ኅብስትየ ምስለ መዓርየ፤ ሰተይኩ ወይንየ ምስለ ሐሊብየ፣ በልዑ ካልአንየ፤ ሰትዩ ወሰከሩ ውሉድ አኃውየ። giz GAZGAZ “Yaa obboleettii ko, kaadhima ko! Ani gara iddoo dhaabaa kootii dhufeera, qumbii koo fi urgooftuu koo walitti qabadheer… Afaan Oromoo BCV aksum ሓፍተይ፥ መርዓተይ፥ ናብ ገነተይ ኣትየ፥ ከርበይን ምዑዝ ቀመማተይን እእክብ ኣለኹ። ሕብስተይ ምስ መዓረይ፥ ወይነይ ድማ ምስ ፀባይ ሰተኹ። ኣቱም ኣዕርኽተይ፥ ብልዑ፤ ስተዩ፤ ኣቱም ፍቑራት፥… ትግርኛ SWAHSUV Naingia bustanini mwangu, umbu langu, bibi arusi, Nachuma manemane yangu na rihani, Nala sega la asali na asali yangu, … Kiswahili