ወደ ሮሜ 2

AMHEVGአማርኛ28 ጥቅሶች3:39 አዳምጥ
አዳምጥ 3:39 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ስለዚህ፥ አንተ የምትፈርድ ሰው ሁሉ ሆይ፥ የምታመካኘው የለህም፤ በሌላው በምትፈርድበት ነገር ራስህን ትኰንናለህና፤ አንተው ፈራጁ እነዚያን ታደርጋለህና።

2እንደዚህም በሚያደርጉት ላይ የእግዚአብሔር ፍርድ እውነተኛ እንደ ሆነ እናውቃለን።

3አንተም እንደዚህ በሚያደርጉ የምትፈርድ ያንም የምታደርግ ሰው ሆይ፥ አንተ ከእግዚአብሔር ፍርድ የምታመልጥ ይመስልሃልን?

4ወይስ የእግዚአብሔር ቸርነት ወደ ንስሐ እንዲመራህ ሳታውቅ የቸርነቱንና የመቻሉን የትዕግሥቱንም ባለጠግነት ትንቃለህን?

5ነገር ግን እንደ ጥንካሬህና ንስሐ እንደማይገባ ልብህ የእግዚአብሔር ቅን ፍርድ በሚገለጥበት በቍጣ ቀን ቍጣን በራስህ ላይ ታከማቻለህ።

6እርሱ ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው ያስረክበዋል፤

7በበጎ ሥራ በመጽናት ምስጋናንና ክብርን የማይጠፋንም ሕይወት ለሚፈልጉ የዘላለምን ሕይወት ይሰጣቸዋል፤

8ለዓመፃ በሚታዘዙ እንጂ ለእውነት በማይታዘዙትና በአድመኞች ላይ ግን ቍጣና መቅሠፍት ይሆንባቸዋል።

9ክፉውን በሚያደርግ ሰው ነፍስ ሁሉ መከራና ጭንቀት ይሆንበታል፥ አስቀድሞ በአይሁዳዊ ደግሞም በግሪክ ሰው፤

10ነገር ግን በጎ ሥራ ለሚያደርጉ ሁሉ ምስጋናና ክብር ሰላምም ይሆንላቸዋል፥ አስቀድሞ ለአይሁዳዊ ደግሞም ለግሪክ ሰው።

11እግዚአብሔር ለሰው ፊት አያዳላምና።

12ያለ ሕግ ኃጢአት ያደረጉ ሁሉ ያለ ሕግ ደግሞ ይጠፋሉና፤ ሕግም ሳላቸው ኃጢአት ያደረጉ ሁሉ በሕግ ይፈረድባቸዋል፤

13በእግዚአብሔር ፊት ሕግን የሚያደርጉት ይጸድቃሉ እንጂ ሕግን የሚሰሙ ጻድቃን አይደሉምና።

14ሕግ የሌላቸው አሕዛብ ከባሕርያቸው የሕግን ትእዛዝ ሲያደርጉ፥ እነዚያ ሕግ ባይኖራቸው እንኳ ለራሳቸው ሕግ ናቸውና፤

15እነርሱም ሕሊናቸው ሲመሰክርላቸው፥ አሳባቸውም እርስ በርሳቸው ሲካሰስ ወይም ሲያመካኝ በልባቸው የተጻፈውን የሕግ ሥራ ያሳያሉ።

16ይህም እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ እኔ በወንጌል እንዳስተማርሁ በሰው ዘንድ የተሰወረውን በሚፈርድበት ቀን ይሆናል።

17አንተ ግን አይሁዳዊ ብትባል በሕግም ብትደገፍ በእግዚአብሔርም ብትመካ፥

18ፈቃዱንም ብታውቅ ከሕግም ተምረህ የሚሻለውን ፈትነህ ብትወድ፤

19በሕግም የእውቀትና የእውነት መልክ ስላለህ፥ የዕውሮች መሪ፥ በጨለማም ላሉ ብርሃን፥ የሰነፎችም አስተማሪ፥ የሕፃናትም መምህር እንደ ሆንህ በራስህ ብትታመን፤

21እንግዲህ አንተ ሌላውን የምታስተምር ራስህን አታስተምርምን? አትስረቅ ብለህ የምትሰብክ ትሰርቃለህን?

22አታመንዝር የምትል ታመነዝራለህን? ጣዖትን የምትጸየፍ ቤተ መቅደስን ትዘርፋለህን?

23በሕግ የምትመካ ሕግን በመተላለፍ እግዚአብሔርን ታሳፍራለህን?

24“በእናንተ ሰበብ የእግዚአብሔር ስም በአሕዛብ መካከል ይሰደባልና” ተብሎ እንደ ተጻፈ።

25ሕግን ብታደርግ መገረዝስ ይጠቅማል፤ ሕግን ተላላፊ ብትሆን ግን መገረዝህ አለ መገረዝ ሆኖአል።

26እንግዲህ ያልተገረዘ ሰው የሕግን ሥርዓት ቢጠብቅ አለመገረዙ እንደ መገረዝ ሆኖ አይቈጠርለትምን?

27ከፍጥረቱም ያልተገረዘ ሕግን የሚፈጽም ሰው የሕግ መጽሐፍና መገረዝ ሳለህ ሕግን በምትተላለፈው በአንተ ይፈርድብሃል።

28በግልጥ አይሁዳዊ የሆነ አይሁዳዊ አይደለምና፥ በግልጥ በሥጋ የሚደረግ መገረዝም መገረዝ አይደለምና፤

29ዳሩ ግን በስውር አይሁዳዊ የሆነ አይሁዳዊ ነው፥ መገረዝም በመንፈስ የሚደረግ የልብ መገረዝ ነው እንጂ በመጽሐፍ አይደለም፤ የእርሱ ምስጋና ከእግዚአብሔር ነው እንጂ ከሰው አይደለም።

ማብራሪያ

2:1-16 አይሁድ ራሳቸውን ቅዱስ ሕዝብ እንደሆኑ፣ በመብትም ለልዩ ጥቅሞቻቸው ይገባናል ብለው ሲያስቡ፣ እነርሱ ግን የማያመሰግኑ፣ ዓመፀኞችና ጻድቅ ያልሆኑ ነበሩ። ነገር ግን እንዲህ የሚያደርጉ ሁሉ፣ ከየትኛውም ብሔር፣ ዕድሜና ደረጃ የሆኑ ቢሆኑም፣ የእግዚአብሔር ፍርድ እንደ እውነተኛ ማንነታቸው እንደሚሆን ሊታወቃቸው ይገባል። ጉዳዩ እጅግ ግልጽ ስለሆነ፣ የኃጢአተኛውን የራሱን ሐሳብ እንደ ማስረጃ ማቅረብ እንችላለን። በፈቃደኝነት በሚፈጸም ኃጢአት ሁሉ የእግዚአብሔርን በጎነት ንቀት ይዟል። የሰው አለመታዘዝ ቅርንጫፎች እጅግ ብዙና የተለያዩ ቢሆኑም፣ ሁሉም ከአንድ ሥር ይፈልቃሉ። ነገር ግን በእውነተኛ ንስሐ ውስጥ፣ መልካሙን ለመምረጥና ክፉውን ለመጣል የሚያነሳሳ፣ በአእምሮ ሁኔታ ውስጥ ከተፈጠረ ለውጥ የተነሣ፣ የቀድሞው ኃጢአተኝነት ጥላቻ ሊኖር ይገባል። እንዲሁም የውስጣዊ መከራ ስሜትን ያሳያል። በንስሐ ውስጥ የሚፈጠረው ታላቅ ለውጥ እንዲህ ያለ ነው፤ እርሱም መለወጥ ነው፣ በእያንዳንዱ ሰው ዘንድም ያስፈልጋል። የኃጢአተኞች ጥፋት ከደነደነና ንስሐ ከማይገባ ልብ በኋላ መሄዳቸው ነው። ኃጢአተኛ ሥራዎቻቸው 'ቁጣን እንደመሰብሰብ' በሚለው ኃይለኛ ቃል ይገለጻሉ። ጻድቅ ሰውን በሚገልጸው ቃል ውስጥ፣ የሕግን ሙሉ ፍላጎት ልብ ይበሉ። ምክንያቶቹ ንጹሕ እንዲሆኑ ይጠይቃል፣ ከምድራዊ ምኞት ወይም ዓላማ የመጡ ሥራዎችን ሁሉ ውድቅ ያደርጋል። ጻድቅ ያልሆነውን ሰው ሲገልጽ፣ ክርክር የክፉ ነገር ሁሉ መሠረት ተደርጎ ቀርቧል። የሰው ፈቃድ ከእግዚአብሔር ጋር በጠላትነት ውስጥ ነው። የተጻፈ ሕግ የሌላቸው አሕዛብ እንኳ፣ በተፈጥሮ ብርሃን ምን ማድረግ እንዳለባቸው የሚያመላክት ነገር በውስጣቸው ነበራቸው።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV You, therefore, have no excuse, you who pass judgment on someone else, for at whatever point you judge the other, you a… English BCV ስለዙይ ኣታ ንኻልእ እትፈርድ ሰብ፥ እተመኽንዮ የብልካን፤ በቲ ዅሉ ንኻልእ እትፈርደሉ ነገር፥ ንባዕልኻ ትዅንን ኣለኻ፤ ነቲ ፈራዲ ዝኾንካሉ፥ ንስኻውን ንእኡ ትገብሮ ኣለኻሞ።(ሀ) ትግርኛ GAZBIB Kanaafis ati yaa isa nama biraatti faradduu, waan itti qabattu hin qabdu! Ati inni namatti faraddu, isuma namichi sun h… Afaan Oromoo BCV GIZ ዕጓለ እመሕያው በምንትኑ ዘትትዋሥኦ ለመኰንነ ጽድቅ ሶበ አንተ ዝኰ ዘትግዕዝ በላዕለ ባዕድ፤ ሶበ ለሊከ ትገብር ዝኰ ዘትጸልእ በላዕለ ቢጽከ፤ አኮኑ ርእሰከ ትግዕዝ እስመ ለሊከ ትገብሮ። giz GAZGAZ Kanaafis ati yaa isa nama biraatti faradduu, waan itti qabattu hin qabdu! Ati inni namatti faraddu, isuma namichi sun h… Afaan Oromoo BCV aksum ስለዙይ ኣታ ንኻልእ እትፈርድ ሰብ፥ እተመኽንዮ የብልካን፤ በቲ ዅሉ ንኻልእ እትፈርደሉ ነገር፥ ንባዕልኻ ትዅንን ኣለኻ፤ ነቲ ፈራዲ ዝኾንካሉ፥ ንስኻውን ንእኡ ትገብሮ ኣለኻሞ።(ሀ) ትግርኛ AMHNIV ስለዚህ አንተ በሌላው ላይ የምትፈርድ፣ የምታመካኝበት የለህም፤ በሌላው ላይ በምትፈርድበት ነገር ሁሉ፣ ራስህን ትኰንናለህ፤ ፈራጅ የሆንኸው አንተ ያንኑ ታደርጋለህና። አማርኛ SWAHSUV Kwa hiyo, wewe mtu uwaye yote uhukumuye, huna udhuru; kwa maana katika hayo umhukumuyo mwingine wajihukumu mwenyewe kuw… Kiswahili