ወደ ሮሜ 2

AMHNIVአማርኛ29 ጥቅሶች4:34 አዳምጥ
አዳምጥ 4:34 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ስለዚህ አንተ በሌላው ላይ የምትፈርድ፣ የምታመካኝበት የለህም፤ በሌላው ላይ በምትፈርድበት ነገር ሁሉ፣ ራስህን ትኰንናለህ፤ ፈራጅ የሆንኸው አንተ ያንኑ ታደርጋለህና።

2እንደዚህ በሚያደርጉትም ላይ የእግዚአብሔር ፍርድ ትክክለኛ መሆኑን እናውቃለን።

3እንግዲህ አንተ ሰው በሌሎች ላይ እየፈረድህ፣ ያንኑ የምታደርግ ከሆነ ከእግዚአብሔር ፍርድ የምታመልጥ ይመስልሃል?

4ወይስ የእግዚአብሔር ቸርነት ወደ ንስሓ የሚመራህ መሆኑን ሳትገነዘብ፣ የቸርነቱን፣ የቻይነቱን የትዕግሥቱን ባለጠግነት ትንቃለህ?

5ነገር ግን በድንዳኔህና ንስሓ በማይገባ ልብህ ምክንያት ትክክለኛ ፍርዱ ሲገለጥ በእግዚአብሔር የቊጣ ቀን በራስህ ላይ ቊጣን ታከማቻለህ።

6እግዚአብሔር “ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው ይሰጠዋል”፤

7በጎ የሆነውን ጸንቶ በማድረግ ክብርን፣ ሞገስንና ዘላለማዊነትን ለሚሹ የዘላለም ሕይወት ይሰጣቸዋል።

8ነገር ግን በራስ ወዳዶች፣ እውነትን ትተው ክፋትን በሚከተሉ ፍርድና ቊጣ ይደርስባቸዋል።

9ክፉ በሚያደርግ በማንኛውም ሰው፣ አስቀድሞ በአይሁድ ከዚያም በአሕዛብ ላይ መከራና ጭንቀት ይሆናል፤

10ነገር ግን በጎ ለሚሠራ ለማንኛውም፣ አስቀድሞ ለአይሁድ ከዚያም ለአሕዛብ ክብር፣ ሞገስና ሰላም ይሆንለታል፤

11እግዚአብሔር ለማንም አያደላምና።

12ሕግ ሳይኖራቸው ኀጢአት የሠሩ ሁሉ ያለ ሕግ ይጠፋሉ፤ ሕግ እያላቸው ኀጢአት የሠሩ በሕግ ይፈረድባቸዋል፤

13ምክንያቱም በእግዚአብሔር ፊት ጻድቃን የሚባሉት ለሕጉ የሚታዘዙ እንጂ፣ ሕጉን የሚሰሙ አይደሉም።

14ሕግ የሌላቸው አሕዛብ ሕግ የሚያዝዘውን ነገር በተፈጥሮ ሲያደርጉ፣ ሕግ ባይኖራቸውም እነርሱ ለራሳቸው ሕግ ናቸው።

15ኅሊናቸው ስለሚመሰክር፣ ሐሳባቸው ስለሚከሳቸው፣ ደግሞም ስለሚከላከልላቸው የሕግ ትእዛዝ በልባቸው የተጻፈ መሆኑን ያሳያሉ።

16ይህም በወንጌል እንደማስተምረው እግዚአብሔር በሰው ልብ የተሰወረውን በክርስቶስ በኩል በሚፈርድበት ዕለት ግልጽ ይሆናል።

17አንተ ይሁዲ ነኝ ካልህ፣ በሕግ የምትተማመንና ከእግዚአብሔር ጋር ባለህ ግንኙነት የምትኵራራ፣

18በሕግ በመመራትህም ፈቃዱን ዐውቀህ ፍጹም የሆነውን ለይተህ ከያዝህ፣

19ለዕውሮች መሪ፣ በጨለማ ላሉትም ብርሃን መሆንህን ርግጠኛ ከሆንህ፣

20በሕጉም ካገኘኸው ዕውቀትና እውነት የተነሣ አላዋቂ ለሆኑት መካሪ፣ ለሕፃናት አስተማሪ ከሆንህ፣

21እንግዲህ አንተ ሌሎችን የምታስተምር፣ ራስህን አታስተምርምን? አትስረቅ ብለህ የምትሰብክ፣ ትሰርቃለህን?

22አንተ ሰዎች ማመንዘር የለባቸውም የምትል፣ ታመነዝራለህን? አንተ ጣዖትን የምትጸየፍ፣ ቤተ መቅደስን ትመዘብራለህን?

23አንተ በሕግ የምትመካ፣ ሕግን በመተላለፍ እግዚአብሔርን ታዋርዳለህን?

24ይህም “በእናንተ ምክንያት የእግዚአብሔር ስም በአሕዛብ ዘንድ ይሰደባል” ተብሎ እንደ ተጻፈው መሆኑ ነው።

25ሕግን የምትፈጽም ከሆነ ግዝረት ዋጋ አለው፤ ሕግን የምትተላለፍ ከሆነ ግን እንዳ ልተገረዝህ ትሆናለህ።

26ያልተገረዙት ሕጉ የሚያዝዘውን የሚፈጽሙ ከሆነ፣ እንደ ተገረዙ አይቈጠሩምን?

27አንተ የተጻፈ ሕግ፣ ግዝረትም ቢኖርህ፣ ሕግ ተላላፊ በመሆንህ፣ በሥጋ ያልተገረዘው ለሕግ በመታዘዙ ይፈርድብሃል።

28አንድ ሰው ለይምሰል በውጫዊው ብቻ ይሁዲ ልሁን ቢል ይሁዲ አይሆንም፤ እውነትኛ ግዝረትም ውጫዊና ሥጋዊ ሥርዐት አይደለም።

29ዳሩ ግን አንድ ሰው ይሁዲ የሚሆነው በውስጣዊ ማንነቱ ይሁዲ ሆኖ ሲገኝ ነው። ግዝረትም ግዝረት የሚሆነው በተጻፈው ሕግ ሳይሆን፣ በመንፈስ የልብ ግዝረት ሲኖር ነው። እንዲህ ያለው ሰው ምስጋናው ከሰው ሳይሆን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።

ማብራሪያ

2:1-16 አይሁድ ራሳቸውን ቅዱስ ሕዝብ እንደሆኑ፣ በመብትም ለልዩ ጥቅሞቻቸው ይገባናል ብለው ሲያስቡ፣ እነርሱ ግን የማያመሰግኑ፣ ዓመፀኞችና ጻድቅ ያልሆኑ ነበሩ። ነገር ግን እንዲህ የሚያደርጉ ሁሉ፣ ከየትኛውም ብሔር፣ ዕድሜና ደረጃ የሆኑ ቢሆኑም፣ የእግዚአብሔር ፍርድ እንደ እውነተኛ ማንነታቸው እንደሚሆን ሊታወቃቸው ይገባል። ጉዳዩ እጅግ ግልጽ ስለሆነ፣ የኃጢአተኛውን የራሱን ሐሳብ እንደ ማስረጃ ማቅረብ እንችላለን። በፈቃደኝነት በሚፈጸም ኃጢአት ሁሉ የእግዚአብሔርን በጎነት ንቀት ይዟል። የሰው አለመታዘዝ ቅርንጫፎች እጅግ ብዙና የተለያዩ ቢሆኑም፣ ሁሉም ከአንድ ሥር ይፈልቃሉ። ነገር ግን በእውነተኛ ንስሐ ውስጥ፣ መልካሙን ለመምረጥና ክፉውን ለመጣል የሚያነሳሳ፣ በአእምሮ ሁኔታ ውስጥ ከተፈጠረ ለውጥ የተነሣ፣ የቀድሞው ኃጢአተኝነት ጥላቻ ሊኖር ይገባል። እንዲሁም የውስጣዊ መከራ ስሜትን ያሳያል። በንስሐ ውስጥ የሚፈጠረው ታላቅ ለውጥ እንዲህ ያለ ነው፤ እርሱም መለወጥ ነው፣ በእያንዳንዱ ሰው ዘንድም ያስፈልጋል። የኃጢአተኞች ጥፋት ከደነደነና ንስሐ ከማይገባ ልብ በኋላ መሄዳቸው ነው። ኃጢአተኛ ሥራዎቻቸው 'ቁጣን እንደመሰብሰብ' በሚለው ኃይለኛ ቃል ይገለጻሉ። ጻድቅ ሰውን በሚገልጸው ቃል ውስጥ፣ የሕግን ሙሉ ፍላጎት ልብ ይበሉ። ምክንያቶቹ ንጹሕ እንዲሆኑ ይጠይቃል፣ ከምድራዊ ምኞት ወይም ዓላማ የመጡ ሥራዎችን ሁሉ ውድቅ ያደርጋል። ጻድቅ ያልሆነውን ሰው ሲገልጽ፣ ክርክር የክፉ ነገር ሁሉ መሠረት ተደርጎ ቀርቧል። የሰው ፈቃድ ከእግዚአብሔር ጋር በጠላትነት ውስጥ ነው። የተጻፈ ሕግ የሌላቸው አሕዛብ እንኳ፣ በተፈጥሮ ብርሃን ምን ማድረግ እንዳለባቸው የሚያመላክት ነገር በውስጣቸው ነበራቸው።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG ስለዚህ፥ አንተ የምትፈርድ ሰው ሁሉ ሆይ፥ የምታመካኘው የለህም፤ በሌላው በምትፈርድበት ነገር ራስህን ትኰንናለህና፤ አንተው ፈራጁ እነዚያን ታደርጋለህና። አማርኛ ENGNIV You, therefore, have no excuse, you who pass judgment on someone else, for at whatever point you judge the other, you a… English BCV ስለዙይ ኣታ ንኻልእ እትፈርድ ሰብ፥ እተመኽንዮ የብልካን፤ በቲ ዅሉ ንኻልእ እትፈርደሉ ነገር፥ ንባዕልኻ ትዅንን ኣለኻ፤ ነቲ ፈራዲ ዝኾንካሉ፥ ንስኻውን ንእኡ ትገብሮ ኣለኻሞ።(ሀ) ትግርኛ GAZBIB Kanaafis ati yaa isa nama biraatti faradduu, waan itti qabattu hin qabdu! Ati inni namatti faraddu, isuma namichi sun h… Afaan Oromoo BCV GIZ ዕጓለ እመሕያው በምንትኑ ዘትትዋሥኦ ለመኰንነ ጽድቅ ሶበ አንተ ዝኰ ዘትግዕዝ በላዕለ ባዕድ፤ ሶበ ለሊከ ትገብር ዝኰ ዘትጸልእ በላዕለ ቢጽከ፤ አኮኑ ርእሰከ ትግዕዝ እስመ ለሊከ ትገብሮ። giz GAZGAZ Kanaafis ati yaa isa nama biraatti faradduu, waan itti qabattu hin qabdu! Ati inni namatti faraddu, isuma namichi sun h… Afaan Oromoo BCV aksum ስለዙይ ኣታ ንኻልእ እትፈርድ ሰብ፥ እተመኽንዮ የብልካን፤ በቲ ዅሉ ንኻልእ እትፈርደሉ ነገር፥ ንባዕልኻ ትዅንን ኣለኻ፤ ነቲ ፈራዲ ዝኾንካሉ፥ ንስኻውን ንእኡ ትገብሮ ኣለኻሞ።(ሀ) ትግርኛ SWAHSUV Kwa hiyo, wewe mtu uwaye yote uhukumuye, huna udhuru; kwa maana katika hayo umhukumuyo mwingine wajihukumu mwenyewe kuw… Kiswahili