ራእይ ዮሃንስ 5

AMHNIVአማርኛ14 ጥቅሶች3:00 አዳምጥ
አዳምጥ 3:00 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1በዙፋኑ ላይ የተቀመጠው በውስጥና በውጭ በኩል የተጻፈበት፣ በሰባት ማኅተም የታሸገ ጥቅልል መጽሐፍ በቀኝ እጁ ይዞ አየሁ።

2አንድ ብርቱ መልአክ በታላቅ ድምፅ፣ “ማኅተሞቹን ለመፍታትና መጽሐፉን ለመክፈት የተገባው ማን ነው?” ብሎ ሲያውጅ አየሁ።

3ነገር ግን በሰማይም ሆነ በምድር፣ ከምድርም በታች መጽሐፉን ለመክፈት ወይም ገልጦ ለመመልከት የሚችል ማንም አልነበረም።

4እኔም መጽሐፉን ለመክፈት ወይም ገልጦ ለመመልከት የተገባው ማንም ባለመኖሩ እጅግ አለቀስሁ።

5ከዚያም ከሽማግሌዎቹ አንዱ፣ “አታልቅስ፤ እነሆ፤ ከይሁዳ ነገድ የሆነው አንበሳ፣ የዳዊት ሥር ድል ነሥቶአል፤ እርሱ መጽሐፉን ሊከፍትና ሰባቱንም ማኅተሞች ሊፈታ ይችላል” አለኝ።

6ከዚያም በዙፋኑና በአራቱ ሕያዋን ፍጡራን፣ በሽማግሌዎቹም መካከል የታረደ የሚመስል በግ ቆሞ አየሁ፤ በጉም ሰባት ቀንዶችና ሰባት ዐይኖች ነበሩት፤ እነርሱም ወደ ምድር ሁሉ የተላኩት ሰባቱ የእግዚአብሔር መናፍስት ናቸው።

7እርሱም መጥቶ በዙፋኑ ላይ ከተቀመጠው ቀኝ እጅ መጽሐፉን ወሰደ።

8መጽሐፉን በወሰደ ጊዜ አራቱ ሕያዋን ፍጡራን፣ ሃያ አራቱ ሽማግሌዎችም በበጉ ፊት በግምባራቸው ተደፉ፤ እያንዳንዳቸውም የቅዱሳን ጸሎት የሆኑትን በገናና ዕጣን የሞላበትን የወርቅ ሙዳይ ይዘው ነበር።

9እንዲህም እያሉ አዲስ መዝሙር ዘመሩ፤ “መጽሐፉን ልትወስድ፣ ማኅተሞቹንም ልትፈታ ይገባሃል፤ ምክንያቱም ታርደሃል፤ በደምህም ከነገድ ሁሉ፣ ከቋንቋ ሁሉ፣ ከወገን ሁሉ፣ ከሕዝብ ሁሉ ሰዎችን ለእግዚአብሔር ዋጅተሃል።

10ለአምላካችንም መንግሥትና ካህናት አድርገሃቸዋል፤ እነርሱም በምድር ላይ ይነግሣሉ።”

11ከዚያም ተመለከትሁ፤ የብዙ መላእክትን ድምፅ ሰማሁ፤ ቍጥራቸውም ሺህ ጊዜ ሺህና እልፍ ጊዜ እልፍ ነበረ፤ እነርሱም በዙፋኑና በሕያዋን ፍጡራኑ፣ በሽማግሌዎቹም ዙሪያ ከበው ነበር፤

12በታላቅ ድምፅም እንዲህ ብለው ዘመሩ፤ “የታረደው በግ ኀይልና ባለጠግነት፣ ጥበብና ብርታት፣ ክብርና ሞገስ፣ ምስጋናም፣ ሊቀበል ይገባዋል።

13ከዚያም በሰማይና በምድር፣ ከምድር በታችና በባሕር፣ በእነርሱ ውስጥ ያሉ ፍጡራንም ሁሉ እንዲህ ብለው ሲዘምሩ ሰማሁ፤ “በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠውና ለበጉ፣ ምስጋናና ሞገስ፣ ክብርና ኀይል፣ ከዘላለም እስከ ዘላለም ይሁን።”

14አራቱ ሕያዋን ፍጡራንም፣ “አሜን” አሉ፤ ሽማግሌዎቹም በግምባራቸው ተደፍተው ሰገዱ።

ማብራሪያ

ራእይ 5:1-7

ሐዋርያው በዙፋኑ ላይ የተቀመጠው በእጁ በዚያን ጊዜ በልማድ በሚታወቀው መልኩ የተጠቀለለ የብራና ጥቅልል አየ፤ እርሱም በሰባት ማኅተሞች የታተመ ነበር። ይህ ሊገለጡ ያሉት የእግዚአብሔርን ምስጢራዊ ዓላማዎች ይወክል ነበር። መለኮታዊው አምላካዊ ጥበቃ (ፕሮቪደንስ) በቤተክርስቲያኗና በዓለም ላይ ያለው እቅድና አፈጻጸም፣ ተወስኖ፣ ጸንቶ፣ መዝገብ ላይ ተመዝግቦ ይገኛል። የእግዚአብሔር ምክሮች በፍጹም ከፍጥረት ዓይንና ግንዛቤ የተሰወሩ ናቸው። የተለያዩት ክፍሎች በአንዴ አይፈቱም አይከፈቱም፤ ይልቁንም፣ የእግዚአብሔር ምክርና አድራጎት ምስጢር ሁሉ በዓለም እስኪፈጸም ድረስ፣ እርስ በእርስ ተከታትለው ይገለጣሉ።

ፍጥረታት ሊከፍቱትም ሊያነቡትም አይችሉም፤ ጌታ ብቻ እርሱን ማድረግ ይችላል። እግዚአብሔርን በብዛት ያዩት ይበልጥ ለማየት ይጓጓሉ፤ ክብሩንም ያዩ ፈቃዱን ለማወቅ ይፈልጋሉ። ነገር ግን መልካም ሰዎችም ቢሆኑ የመለኮታዊውን አድራጎት ምስጢሮች ለማየት በጣም ይቸኩሉና ይጣደፉ ይሆናል። እንዲህ ያሉት ፍላጎቶች በቶሎ ካልተመለሱ፣ ወደ ሐዘንና ትካዜ ይቀየራሉ። ዮሐንስ የእግዚአብሔርን ድንጋጌዎች መጽሐፍ ማየት ባለመቻሉ እጅግ ካለቀሰ፣ ብዙዎች የክርስቶስን ወንጌል ባለማወቃቸው ምን ያህል እንባ ሊያፈሱ ይገባል! ዘላለማዊ ድነት የተመካው በእርሱ ላይ አይደለምን! በዚህ ዓለም ውስጥ ስለ ራሳችን የሆኑ የወደፊት ክስተቶችን መተንበይ ስለማንችል ማልቀስ አያስፈልገንም፤ የወደፊቱን ተስፋ በጉጉት መጠበቅ ወይም የወደፊት አደጋዎችን አስቀድሞ ማየት አሁን ላለው ተግባርና ትግል ብቁ እንዳንሆን ያደርገናል፣ ወይም ደግሞ የበለጸጉ ቀናቶ…

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6