ራእይ ዮሃንስ 19

AMHNIVአማርኛ21 ጥቅሶች4:33 አዳምጥ
አዳምጥ 4:33 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1“ከዚህ በኋላ የብዙ ሰዎችን ድምፅ የሚመስል ታላቅ ድምፅ በሰማይ እንዲህ ሲል ሰማሁ፤ ሃሌ ሉያ! ማዳን፣ ክብርና ኀይል የአምላካችን ነው፤

2ፍርዱ እውነትና ጽድቅ ነውና፤ በዝሙቷ ምድርን ያረከሰችውን፣ ታላቂቱን አመንዝራ ፈርዶባታል፤ ስለ አገልጋዮቹም ደም ተበቅሏታል።”

3ደግሞም እንዲህ አሉ፤ “ሃሌ ሉያ! ጢስ ከእርሷ ከዘላለም እስከ ዘላለም ይወጣል።”

4ሃያ አራቱ ሽማግሌዎችና አራቱ ሕያዋን ፍጡራን በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው አምላክ ወድቀው ሰገዱ፤ እንዲህም አሉ፤ “አሜን፣ ሃሌ ሉያ!”

5ከዚህ በኋላ እንዲህ የሚል ድምፅ ከዙፋኑ ወጣ፤ “እናንተ አገልጋዮቹ ሁሉ፣ እርሱን የምትፈሩ፣ ታናናሾችና ታላላቆችም፣ አምላካችንን አመስግኑ!”

6ደግሞም እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ፣ እንደ ኀይለኛ ወራጅ ውሃ ድምፅ፣ እንደ ብርቱም ነጐድጓድ ድምፅ የሚመስል እንዲህ ሲል ሰማሁ፤ ሃሌ ሉያ! ሁሉን ቻይ ጌታ አምላካችን ነግሦአልና።

7የበጉ ሰርግ ስለ ደረሰ፣ የእርሱም ሙሽራ ራሷን ስላዘጋጀች፣ ደስ ይበለን፤ ሐሤት እናድርግ ክብርም እንስጠው።

8የሚያንጸባርቅና ንጹሕ፣ ከተልባ እግር የተሠራ ቀጭን ልብስ እንድትለብስ ተሰጣት።” ከተልባ እግር የተሠራው ቀጭን ልብስ የቅዱሳን የጽድቅ ሥራ ነው።

9መልአኩም፣ “ ‘ወደ በጉ ሰርግ እራት የተጠሩ ብፁዓን ናቸው’ ብለህ ጻፍ” አለኝ፤ ቀጥሎም፣ “እነዚህ የእግዚአብሔር እውነተኛ ቃሎች ናቸው” አለኝ።

10እኔም ልሰግድለት በእግሩ ሥር ተደፋሁ፤ እርሱ ግን፣ “ተው! ይህን አታድርግ! እኔም ከአንተና የኢየሱስን ምስክር ከያዙት ወንድሞችህ ጋር አገልጋይ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ፤ የኢየሱስ ምስክር የትንቢት መንፈስ ነውና” አለኝ።

11ከዚያም ሰማይም ተከፍቶ አየሁ፤ እነሆ አንድ ነጭ ፈረስ ነበረ፤ በፈረሱም ላይ፣ “ታማኝና እውነተኛ” የሚባል ተቀምጦ ነበር፤ እርሱም በጽድቅ ይፈርዳል፤ ይዋጋልም።

12ዐይኖቹ እንደ እሳት ነበልባል ናቸው፤ በራሱም ላይ ብዙ ዘውዶች አሉ። ከእርሱ በቀር ማንም የማያውቀው ስም በእርሱ ላይ ተጽፎአል።

13እርሱ በደም የተነከረ ልብስ ለብሶአል፤ ስሙም የእግዚአብሔር ቃል ነው።

14የሰማይም ሰራዊት ነጭ፣ ንጹሕና ከተልባ እግር የተሠራ ቀጭን ልብስ ለብሰው፣ በነጫጭ ፈረሶች ላይ ተቀምጠው ይከተሉት ነበር።

15ሕዝቦችን የሚመታበት ስለታም ሰይፍ ከአፉ ወጣ፤ “በብረት በትርም ይገዛቸዋል።” እርሱም ሁሉን ቻይ የሆነውን የእግዚአብሔርን የብርቱ ቍጣ ወይን መጭመቂያ ይረግጣል።

16በልብሱና በጭኑ ላይ እንዲህ የሚል ስም ተጽፎአል፤ “የነገሥታት ንጉሥና የጌቶች ጌታ።”

17ቀጥሎም አንድ መልአክ በፀሓይ ውስጥ ቆሞ አየሁ፤ እርሱም በሰማይ መካከል ለሚበሩ ወፎች ሁሉ እንዲህ ሲል በታላቅ ድምፅ ጮኸ፤ “ኑ፤ ወደ ታላቁ የእግዚአብሔር እራት ተሰብሰቡ፤

18የምትሰበሰቡትም የነገሥታትን ሥጋ፣ የጦር አዛዦችን ሥጋ፣ የብርቱ ሰዎችን ሥጋ፣ የፈረሶችንና የፈረሰኞችን ሥጋ እንዲሁም የሰዎችን ሁሉ፣ ይኸውም የጌቶችንና የባሮችን፣ የታናናሾችንና የታላላቆችን ሥጋ እንድትበሉ ነው።”

19ከዚህ በኋላ አውሬው፣ የምድር ነገሥታትና ሰራዊታቸው በፈረሱ ላይ ከተቀመጠውና ከሰራዊቱ ጋር ለመዋጋት ተሰብስበው አየሁ።

20ነገር ግን አውሬው ተያዘ፤ ከእርሱም ጋር በፊቱ ምልክቶችን ያደርግ የነበረው ሐሰተኛው ነቢይ ተያዘ። በእነዚህ ምልክቶች የአውሬውን ምልክት የተቀበሉትንና ለምስሉ የሰገዱትን አሳተ። ሁለቱም በሕይወት እንዳሉ በዲን ወደሚቃጠለው የእሳት ባሕር ተጣሉ።

21የቀሩት ደግሞ በፈረሱ ላይ ከተቀመጠው አፍ በሚወጣው ሰይፍ ተገደሉ፤ ወፎችም ሁሉ ከሥጋቸው በልተው ጠገቡ።

ማብራሪያ

ራዕይ ፲፱፡፩-፲። ላለን ነገር እግዚአብሔርን ማመስገን፣ ወደፊት የሚደረግልንን ደግሞ እንደመጸለይ ነው። በዚህ አሸናፊ መዝሙር በመላእክትና በቅዱሳን መካከል ስምምነት አለ። ክርስቶስ የዋጃት ቤተ ክርስቲያኑ ሙሽራ ነው። ይህ ሁለተኛው አንድነት በሰማይ ይፈጸማል። ነገር ግን የክቡር የሺህ ዓመት መንግሥት መጀመሪያ (ይህም በምድር ላይ የክርስቶስን መንግሥት፣ ወይም ደስታ የሰፈነበትን የሺህ ዓመት ዘመን ያመለክታል) በምድር ላይ እንደ መተጫጨቱ በዓል ሊታሰብ ይችላል። ያን ጊዜ የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን በትምህርቷ፣ በሥርዓቷ፣ በአምልኮዋና በአኗኗሯ ከስህተቶች፣ ከመለያየቶችና ከብልሹነቶች ሁሉ የነጻች ሆና፣ እርሱ እንደ ውዴታውና እንደ ወዳጁ በግልጽ እንድትታወቅ ዝግጁ ትሆናለች።

ቤተ ክርስቲያን ታየች፤ የአመንዝሮች እናት በሆነችው በደማቅና በሚያብረቀርቅ ልብስ ሳይሆን፣ በንጹሕና በነጭ የተልባ እግር ልብስ። ለጽድቅ በተቆጠረላት እና ለቅድሳት በተሰጣት በክርስቶስ ጽድቅ ልብሶች። የወንጌል ተስፋዎች፣ በእግዚአብሔር መንፈስ በቅዱሳን ሥርዓቶች ውስጥ የተከፈቱ፣ የተተገበሩና የታተሙ የእግዚአብሔር እውነተኛ ቃላት፣ የሰርግ ግብዣው ናቸው። ይህ ክርስቲያኖች በሚመጡት አስደሳች ቀናት የሚቀበሉትን የብዙውን ጸጋና መጽናናት የሚያመለክት ይመስላል። ሐዋርያው ለመላኩ ክብርን አቀረበ። መልአኩ ግን እምቢ አለ። ሐዋርያውንም ለእውነተኛውና ብቸኛው የአምልኮ ዓላማ፣ እርሱንም እግዚአብሔርን ብቻ እንዲያመልክ መራው።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG ከዚህ በኋላ በሰማይ፦ “ሃሌ ሉያ፤ በዝሙትዋ ምድርን ያጠፋችይቱን ታላቂቱን ጋለሞታ ስለ ፈረደባት፥ የባሪያዎቹንም ደም ከእጅዋ ስለ ተበቀለ፥ ፍርዶቹ እውነትና ጽድቅ ናቸውና ማዳንና ክብር ኃይ… አማርኛ ENGNIV After this I heard what sounded like the roar of a great multitude in heaven shouting: “Hallelujah! Salvation and glory… English BCV ድሕሪዙይ፥ ኣብ ሰማይ ከም ናይ ብዙሕ ህዝቢ ዝበለ፥ ብርቱዕ ድምፂ፥ “ሃሌ ሉያ! ምድሓንን ክብርን ሓይልን ናይ ኣምላኽና እዩ። ትግርኛ GAZBIB Kana booddee tuuta baay'ee sagalee guddaadhaan waaqa keessaa huursu nan dhaga'e; innis, ?Haaleluyaa! Fayyinni, guddinni… Afaan Oromoo BCV GIZ ወእምድኅረ ዝንቱ ተሰምዐ ቃል ዐቢይ እምሰማይ ከመ ዘብዙኅ ሰብእ ወይብሉ፦ “ሃሌ ሉያ እስመ ስብሐት ወፍርቃን ወኀይል ለአምላክነ። giz GAZGAZ Kana booddee tuuta baay'ee sagalee guddaadhaan waaqa keessaa huursu nan dhaga'e; innis, ?Haaleluyaa! Fayyinni, guddinni… Afaan Oromoo BCV aksum ድሕሪዙይ፥ ኣብ ሰማይ ከም ናይ ብዙሕ ህዝቢ ዝበለ፥ ብርቱዕ ድምፂ፥ “ሃሌ ሉያ! ምድሓንን ክብርን ሓይልን ናይ ኣምላኽና እዩ። ትግርኛ SWAHSUV Baada ya hayo nikasikia sauti kama sauti ya makutano mengi, sauti kubwa mbinguni, ikisema, Haleluya; Kiswahili