ራእይ ዮሃንስ 17

AMHEVGአማርኛ18 ጥቅሶች3:27 አዳምጥ
አዳምጥ 3:27 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ሰባቱንም ጽዋዎች ከያዙ ከሰባቱ መላእክት አንዱ መጥቶ፦ “ና በብዙም ውኃዎች ላይ የተቀመጠችውን የታላቂቱን ጋለሞታ ፍርድ አሳይሃለሁ፤

2የምድርም ነገሥታት ከእርስዋ ጋር ሴሰኑ በምድርም የሚኖሩ ከዝሙትዋ ወይን ጠጅ ሰከሩ” ብሎ ተናገረኝ።

3በመንፈስም ወደ በረሀ ወሰደኝ፤ የስድብም ስሞች በሞሉበት፥ ሰባት ራሶችና አሥር ቀንዶችም ባሉበት በቀይ አውሬ ላይ አንዲት ሴት ተቀምጣ አየሁ።

4ሴቲቱም በቀይና በሐምራዊ ልብስ ተጐናጽፋ በወርቅና በከበሩ ድንጋዮች በዕንቈችም ተሸልማ ነበር፥ በእጅዋም የሚያስጸይፍ ነገር የዝሙትዋም ርኵሰት የሞላባትን የወርቅ ጽዋ ያዘች፤

5በግምባርዋም፦ “ምስጢር የሆነ ስም ታላቂቱ ባቢሎን፥ የጋለሞታዎችና የምድር ርኵሰት እናት፡” ተብሎ ተጻፈ።

6ሴቲቱም በቅዱሳን ደምና በኢየሱስ ምስክሮች ደም ሰክራ አየኋት። ባየኋትም ጊዜ እጅግ ታላቅ ድንቅ አደነቅሁ።

7መልአኩም አለኝ፦ “የምትደነቅ ስለ ምንድር ነው? የሴቲቱን ምስጢርና የሚሸከማትን፥ ሰባት ራሶችና አስር ቀንዶች ያሉትን የአውሬውን ምስጢር እኔ እነግርሃለሁ።

8ያየኸው አውሬ አስቀድሞ ነበረ፥ አሁንም የለም፥ ከጥልቁም ይወጣ ዘንድ አለው፥ ወደ ጥፋትም ይሄዳል፤ ስሞቻቸውም ከዓለም ፍጥረት ጀምሮ በሕይወት መጽሐፍ ያልተጻፉ በምድር የሚኖሩ አውሬው አስቀድሞ እንደነበረ አሁንም እንደሌለ፥ ነገር ግን እንዳለ ሲያዩ ያደንቃሉ።

9“ጥበብ ያለው አእምሮ በዚህ ነው። ሰባቱ ራሶች ሴቲቱ የተቀመጠችባቸው ሰባት ተራራዎች ናቸው፥

10ሰባት ነገሥታት ደግሞ ናቸው፤ አምስቱ ወድቀዋል አንዱም አለ፥ የቀረውም ገና አልመጣም፤ ሲመጣም፥ ጥቂት ጊዜ ሊቆይ ይገባዋል።

11የነበረውና የሌለውም አውሬ ራሱ ደግሞ ስምንተኛው ነው ከሰባቱም አንዱ ነው፥ ወደ ጥፋትም ይሄዳል።

12ያየሃቸውም አስሩ ቀንዶች ገና መንግሥትን ያልተቀበሉ አስር ነገሥታት ናቸው፥ ዳሩ ግን ከአውሬው ጋር ለአንድ ሰዓት እንደ ነገሥታት ሥልጣንን ይቀበላሉ።

13እነዚህ አንድ አሳብ አላቸው፥ ኃይላቸውንና ሥልጣናቸውንም ለአውሬው ይሰጣሉ።

14እነዚህ በጉን ይወጋሉ፤ በጉም የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉሥ ስለ ሆነ እነርሱን ድል ይነሣል፥ ከእርሱም ጋር ያሉ የተጠሩና የተመረጡ የታመኑም ደግሞ ድል ይነሣሉ።”

15አለኝም፦ “ጋለሞታይቱ የተቀመጠችባቸው ያየሃቸው ውኃዎች፥ ወገኖችና ብዙ ሰዎች አሕዛብም ቋንቋዎችም ናቸው።

16ያየኃቸውም አስር ቀንዶችና አውሬው ጋለሞታይቱን ይጣላሉ፤ ባዶዋንና ራቁትዋንም ያደርጓታል፥ ሥጋዋንም ይበላሉ፥ በእሳትም ያቃጥሉአታል።

17እግዚአብሔር አሳቡን እንዲያደርጉ አንድንም አሳብ እንዲያደርጉ የእግዚአብሔርም ቃል እስኪፈጸም ድረስ መንግሥታቸውን ለአውሬው እንዲሰጡ በልባቸው አግብቶአልና።

18ያየሃትም ሴት በምድር ነገሥታት ላይ የምትነግሥ ታላቂቱ ከተማ ናት።

ማብራሪያ

ራዕይ 17:1-6 በዚህ ምዕራፍ ውስጥ በግልጽ ሮም እንደሆነች ያመለክታል። አረማዊቷ ሮም በወታደራዊ ኃይል አሸንፋና ገዝታለች እንጂ በጥበብና በማታለል አልነበረም። ብሔራትን በአጠቃላይ ለጥንታዊ ልማዶቻቸውና ለአምልኳቸው ለቃቸው ነበር። ነገር ግን ጳጳሳዊቷ ሮም በተንኮልና በፖለቲካዊ ብልሃት፣ ከዓመፀኛ ማታለያዎች ሁሉ ጋር በመሆን፣ በነገሥታትና በብሔራት ላይ ሥልጣኗን እንዳገኘችና እንዳስጠበቀች የታወቀ ነው። እዚህም ጋር ለሥጋዊና ዓለማዊ አስተሳሰቦች የሚመጥኑ የዓለማዊ ክብርና የሀብት፣ የግርማ ሞገስና የትዕቢት አሳሳች ነገሮች ነበሩ። ብልጽግና፣ ግርማ ሞገስና ውበት የሰውን ልብ ትዕቢትና ምኞቶችን ያነሳሳሉ፣ ነገር ግን ከመለኮታዊ ቁጣ ዋስትና የላቸውም። ወርቃማው ጽዋ ይህች ምሥጢራዊት ባቢሎን ተጽዕኖዋን ያገኘችበትና ያስጠበቀችበት፣ እንዲሁም ሌሎችንም አስታ በማታለል አስጸያፊ ድርጊቶቿን እንዲቀላቀሉ ያደረገችበትን ማባበያዎችንና ማታለያዎችን ይወክላል። ከነውር ተግባሮቿ የተነሳ ‘የጋለሞቶች እናት’ ተብላ ተሰይማለች፤ ወደ ጣዖት አምልኮና ወደ ሁሉ ዓይነት ክፋት ታሰለጥናቸው ነበርና። ራሷን በቅዱሳን ደም፣ በኢየሱስም ምስክሮች ደም ሞላች። በእርሱም ሰከረች፤ እጅግም ደስ ስላሰኛት በፍጹም አልጠገበችውም። በክርስቲያኖች ተብዬዎች የፈሰሰው የክርስቲያኖች ደም ብዛት እጅግ የሚያስደንቅ ነው፤ ነገር ግን እነዚህን ትንቢቶች ስንመለከት፣ እነዚህ አስከፊ ድርጊቶች የወንጌልን እውነት ይመሰክራሉ። ሁሉም ከሚያብረቀርቅ፣ ከትርፋማ ወይም ከወቅታዊ ሃይማኖት ይጠንቀቅ።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV One of the seven angels who had the seven bowls came and said to me, “Come, I will show you the punishment of the great… English BCV ካብቶም ሸውዓተ ፅዋዓት ዝሓዙ ሸውዓተ መላእኽቲ፥ እቲ ሓደ ናባይ መፂኡ፦ “ፍርዲ፥ እታ ኣብ ልዕሊ ብዙሕ ማያት ተቐሚጣ ዘላ ዓባይ ኣመንዝራ፥ ከርእየካ ነዓ፤ ትግርኛ GAZBIB Kana booddee ergamoota torban waciitii torba qaban sana keessaa inni tokko dhufee anatti dubbatee, ?Kottu! Firdii ejjit… Afaan Oromoo BCV GIZ ወመጽአ አሐዱ እምነ እልክቱ ሰብዐቱ መላእክት እለ ይጸውሩ ሰብዐተ ጽዋዓተ፣ ወይቤለኒ፦ “ነዓ አርኢከ ደይና ለእንታክቲ ዘማ ዐባይ እንተ ትነብር ውስተ ማያት ብዙኅ። giz GAZGAZ Kana booddee ergamoota torban waciitii torba qaban sana keessaa inni tokko dhufee anatti dubbatee, ?Kottu! Firdii ejjit… Afaan Oromoo BCV aksum ካብቶም ሸውዓተ ፅዋዓት ዝሓዙ ሸውዓተ መላእኽቲ፥ እቲ ሓደ ናባይ መፂኡ፦ “ፍርዲ፥ እታ ኣብ ልዕሊ ብዙሕ ማያት ተቐሚጣ ዘላ ዓባይ ኣመንዝራ፥ ከርእየካ ነዓ፤ ትግርኛ AMHNIV ሰባቱን ጽዋዎች ከያዙት ከሰባቱ መላእክት አንዱ መጥቶ እንዲህ አለኝ፤ “ና፤ በብዙ ውሆች ላይ የተቀመጠችውን የታላቂቱን አመንዝራ ፍርድ አሳይሃለሁ። አማርኛ SWAHSUV Akaja mmoja wa wale malaika saba, wenye vile vitasa saba, akanena nami, akisema, Njoo huku, nitakuonyesha hukumu ya yul… Kiswahili