ራእይ ዮሃንስ 17

AMHNIVአማርኛ18 ጥቅሶች3:44 አዳምጥ
አዳምጥ 3:44 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ሰባቱን ጽዋዎች ከያዙት ከሰባቱ መላእክት አንዱ መጥቶ እንዲህ አለኝ፤ “ና፤ በብዙ ውሆች ላይ የተቀመጠችውን የታላቂቱን አመንዝራ ፍርድ አሳይሃለሁ።

2የምድር ነገሥታት ከእርሷ ጋር አመነዘሩ፤ የምድር ነዋሪዎችም በዝሙቷ የወይን ጠጅ ሰከሩ።”

3ቀጥሎም መልአኩ በመንፈስ ወደ በረሓ ወሰደኝ፤ በዚያም አንዲት ሴት በስድብ ስሞች በተሞላ፣ ሰባት ራሶችና ዐሥር ቀንዶች ባሉት ቀይ አውሬ ላይ ተቀምጣ አየሁ።

4ሴቲቱም ሐምራዊና ቀይ ልብስ ተጐናጽፋ ነበር፤ ደግሞም በወርቅ፣ በከበሩ ድንጋዮችና በዕንቆችም አጊጣ ነበር፤ በእጇም የሚያስጸይፍ ነገርና የዝሙቷ ርኵሰት የሞላበትን የወርቅ ጽዋ ይዛ ነበር።

5በግምባሯም ላይ እንዲህ የሚል የምስጢር ስም ተጽፎ ነበር፤ ታላቂቱ ባቢሎን፣ የአመንዝሮችና የምድር ርኵሰቶች እናት።

6ሴቲቱንም በቅዱሳን ደምና በኢየሱስ ምስክሮች ደም ሰክራ አየኋት። ባየኋትም ጊዜ እጅግ ተደነቅሁ።

7ከዚያም መልአኩ እንዲህ አለኝ፤ የምትደነቀው ለምንድን ነው? የሴቲቱን፣ እርሷ የተቀመጠችበትንም፣ እንዲሁም ሰባት ራሶችና ዐሥር ቀንዶች ያሉትን የአውሬውን ምስጢር እነግርሃለሁ።

8ያየኸው አውሬ ቀደም ሲል ነበረ፤ አሁን ግን የለም፤ በኋላም ከጥልቁ ጒድጓድ ይወጣል፤ ወደ ጥፋቱም ይሄዳል። ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ስማቸው በሕይወት መጽሐፍ ተጽፎ ያልተገኘ የምድር ነዋሪዎች አውሬው ቀድሞ የነበረ፣ አሁን ግን የሌለ፣ በኋላም የሚመጣ መሆኑን ሲያዩ ይደነቃሉ።

9“ይህም፣ ጥበብ ያለው አእምሮ ይጠይቃል። ሰባቱ ራሶች ሴቲቱ የምትቀመጥባቸው ሰባት ተራሮች ናቸው፤

10እነርሱም ደግሞ ሰባት ነገሥታት ናቸው። አምስቱ ወድቀዋል፤ አንዱ አለ፤ ሌላውም ገና አልመጣም፤ ሲመጣ ግን ሊቈይ የሚገባው ለጥቂት ጊዜ ነው።

11ቀድሞ የነበረውና አሁን የሌለው አውሬ ስምንተኛው ንጉሥ ነው፤ እርሱም ከሰባቱ አንዱ ሲሆን ወደ ጥፋቱ ይሄዳል።

12“ያየሃቸው ዐሥሩ ቀንዶች ገና መንግሥትን ያልተቀበሉ፣ ዐሥር ነገሥታት ናቸው፤ ነገር ግን ከአውሬው ጋር ለአንድ ሰዓት እንዲነግሡ ሥልጣን ይቀበላሉ።

13አንድ ሐሳብም አላቸው፤ ኀይላቸውንና ሥልጣናቸውንም ለአውሬው ይሰጣሉ፤

14እነዚህ በጉን ይወጋሉ፤ በጉ ግን ድል ይነሣቸዋል፤ ምክንያቱም እርሱ የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉሥ ነው፤ ከእርሱ ጋር ያሉ የተጠሩት፣ የተመረጡትና የታመኑትም አብረው ድል ይነሣሉ።”

15መልአኩም እንዲህ አለኝ፤ “አመንዝራዪቱ ተቀምጣባቸው ያየሃቸው ውሆች፦ ወገኖች፣ ብዙ ሰዎች፣ ሕዝቦችና ቋንቋዎች ናቸው።

16አውሬውና ያየሃቸው ዐሥሩ ቀንዶች አመንዝራዪቱን ይጠሏታል፤ ባዶዋንና ዕራቍቷን ያስቀሯታል። ሥጋዋን ይበላሉ፤ በእሳትም ያቃጥሏታል።

17የእግዚአብሔር ቃል እስኪፈጸም ድረስ ዕቅዱን እንዲፈጽሙ፣ ደግሞም በአንድ ሐሳብ እንዲስማሙና ሥልጣናቸውንም ለአውሬው እንዲሰጡ ይህን ሐሳብ በልባቸው ያኖረ እግዚአብሔር ነውና።

18ያየሃትም ሴት በምድር ነገሥታት ላይ የምትነግሥ ታላቂቱ ከተማ ናት።

ማብራሪያ

ራዕይ 17:1-6 በዚህ ምዕራፍ ውስጥ በግልጽ ሮም እንደሆነች ያመለክታል። አረማዊቷ ሮም በወታደራዊ ኃይል አሸንፋና ገዝታለች እንጂ በጥበብና በማታለል አልነበረም። ብሔራትን በአጠቃላይ ለጥንታዊ ልማዶቻቸውና ለአምልኳቸው ለቃቸው ነበር። ነገር ግን ጳጳሳዊቷ ሮም በተንኮልና በፖለቲካዊ ብልሃት፣ ከዓመፀኛ ማታለያዎች ሁሉ ጋር በመሆን፣ በነገሥታትና በብሔራት ላይ ሥልጣኗን እንዳገኘችና እንዳስጠበቀች የታወቀ ነው። እዚህም ጋር ለሥጋዊና ዓለማዊ አስተሳሰቦች የሚመጥኑ የዓለማዊ ክብርና የሀብት፣ የግርማ ሞገስና የትዕቢት አሳሳች ነገሮች ነበሩ። ብልጽግና፣ ግርማ ሞገስና ውበት የሰውን ልብ ትዕቢትና ምኞቶችን ያነሳሳሉ፣ ነገር ግን ከመለኮታዊ ቁጣ ዋስትና የላቸውም። ወርቃማው ጽዋ ይህች ምሥጢራዊት ባቢሎን ተጽዕኖዋን ያገኘችበትና ያስጠበቀችበት፣ እንዲሁም ሌሎችንም አስታ በማታለል አስጸያፊ ድርጊቶቿን እንዲቀላቀሉ ያደረገችበትን ማባበያዎችንና ማታለያዎችን ይወክላል። ከነውር ተግባሮቿ የተነሳ ‘የጋለሞቶች እናት’ ተብላ ተሰይማለች፤ ወደ ጣዖት አምልኮና ወደ ሁሉ ዓይነት ክፋት ታሰለጥናቸው ነበርና። ራሷን በቅዱሳን ደም፣ በኢየሱስም ምስክሮች ደም ሞላች። በእርሱም ሰከረች፤ እጅግም ደስ ስላሰኛት በፍጹም አልጠገበችውም። በክርስቲያኖች ተብዬዎች የፈሰሰው የክርስቲያኖች ደም ብዛት እጅግ የሚያስደንቅ ነው፤ ነገር ግን እነዚህን ትንቢቶች ስንመለከት፣ እነዚህ አስከፊ ድርጊቶች የወንጌልን እውነት ይመሰክራሉ። ሁሉም ከሚያብረቀርቅ፣ ከትርፋማ ወይም ከወቅታዊ ሃይማኖት ይጠንቀቅ።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG ሰባቱንም ጽዋዎች ከያዙ ከሰባቱ መላእክት አንዱ መጥቶ፦ “ና በብዙም ውኃዎች ላይ የተቀመጠችውን የታላቂቱን ጋለሞታ ፍርድ አሳይሃለሁ፤ አማርኛ ENGNIV One of the seven angels who had the seven bowls came and said to me, “Come, I will show you the punishment of the great… English BCV ካብቶም ሸውዓተ ፅዋዓት ዝሓዙ ሸውዓተ መላእኽቲ፥ እቲ ሓደ ናባይ መፂኡ፦ “ፍርዲ፥ እታ ኣብ ልዕሊ ብዙሕ ማያት ተቐሚጣ ዘላ ዓባይ ኣመንዝራ፥ ከርእየካ ነዓ፤ ትግርኛ GAZBIB Kana booddee ergamoota torban waciitii torba qaban sana keessaa inni tokko dhufee anatti dubbatee, ?Kottu! Firdii ejjit… Afaan Oromoo BCV GIZ ወመጽአ አሐዱ እምነ እልክቱ ሰብዐቱ መላእክት እለ ይጸውሩ ሰብዐተ ጽዋዓተ፣ ወይቤለኒ፦ “ነዓ አርኢከ ደይና ለእንታክቲ ዘማ ዐባይ እንተ ትነብር ውስተ ማያት ብዙኅ። giz GAZGAZ Kana booddee ergamoota torban waciitii torba qaban sana keessaa inni tokko dhufee anatti dubbatee, ?Kottu! Firdii ejjit… Afaan Oromoo BCV aksum ካብቶም ሸውዓተ ፅዋዓት ዝሓዙ ሸውዓተ መላእኽቲ፥ እቲ ሓደ ናባይ መፂኡ፦ “ፍርዲ፥ እታ ኣብ ልዕሊ ብዙሕ ማያት ተቐሚጣ ዘላ ዓባይ ኣመንዝራ፥ ከርእየካ ነዓ፤ ትግርኛ SWAHSUV Akaja mmoja wa wale malaika saba, wenye vile vitasa saba, akanena nami, akisema, Njoo huku, nitakuonyesha hukumu ya yul… Kiswahili