ራእይ ዮሃንስ 16

AMHNIVአማርኛ21 ጥቅሶች4:08 አዳምጥ
አዳምጥ 4:08 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ከዚያም ለሰባቱ መላእክት፣ ኋሂዱ፤ ሰባቱን የእግዚአብሔር ቊጣ ጽዋዎች በምድር ላይ አፍስሱ” የሚል ታላቅ ድምፅ ከቤተ መቅደሱ ሰማሁ።

2የመጀመሪያው መልአክ ሄዶ ጽዋውን በምድር ላይ አፈሰሰ፤ የአውሬውን ምልክት በተቀበሉትና ለምስሉም በሰገዱት ሰዎች ላይ ክፉኛ የሚያሠቃይ ቊስል ወጣባቸው።

3ሁለተኛው መልአክ ጽዋውን በባሕር ላይ አፈሰሰ፤ ባሕሩም እንደ ሞተ ሰው ደም ሆነ፤ በባሕሩ ውስጥ የሚኖሩ ሕይወት ያላቸው ነገሮች ሁሉ ሞቱ።

4ሦስተኛው መልአክ ጽዋውን በወንዞችና በውሃ ምንጮች ላይ አፈሰሰ፤ እነርሱም ደም ሆኑ።

5ከዚያም በውሆች ላይ ሥልጣን ያለው መልአክ እንዲህ ሲል ሰማሁ፤ “ያለህና የነበርህ ቅዱሱ ሆይ፤ እንዲህ ስለ ፈረድህ፣ አንተ ጻድቅ ነህ፤

6የቅዱሳንንና የነቢያትን ደም ስላፈሰሱ፣ አንተም ደግሞ ደም እንዲጠጡ አደረግሃቸው፤ ይህ የሚገባቸው ነውና።”

7እንዲሁም ከመሠዊያው እንዲህ የሚል ድምፅ ሰማሁ፤ “አዎን፤ ሁሉን ቻይ ጌታ አምላክ ሆይ፤ ፍርድህ እውነትና ጽድቅ ነው።”

8አራተኛውም መልአክ ጽዋውን በፀሓይ ላይ አፈሰሰ፤ ፀሓይም ሰዎችን በእሳት እንድታቃጥል ኀይል ተሰጣት።

9እነርሱም በታላቅ ሐሩር ተቃጠሉ፤ በእነዚህም መቅሠፍቶች ላይ ሥልጣን ያለውን የእግዚአብሔርን ስም ተሳደቡ እንጂ ንስሓ አልገቡም፤ ክብርም አልሰጡትም።

10አምስተኛውም መልአክ ጽዋውን በአውሬው ዙፋን ላይ አፈሰሰ፤ የአውሬውም መንግሥት በጨለማ ተዋጠ፤ ሰዎችም ከሥቃያቸው የተነሣ ምላሳቸውን ያኝኩ ነበር፤

11ደግሞም ከሥቃያቸውና ከቊስላቸው የተነሣ የሰማይን አምላክ ተሳደቡ እንጂ ከሥራቸው ንስሓ አልገቡም።

12ስድስተኛውም መልአክ ጽዋውን በታላቁ ወንዝ በኤፍራጥስ ላይ አፈሰሰ፤ ከምሥራቅ ለሚመጡ ነገሥታት መንገድ እንዲዘጋጅላቸው የወንዙ ውሃ ደረቀ።

13ከዚያም ከዘንዶው አፍ፣ ከአውሬው አፍና ከሐሰተኛው ነቢይ አፍ እንቍራሪት የሚመስሉ ሦስት ርኩሳን መናፍስት ሲወጡ አየሁ።

14እነርሱም ምልክቶች የሚያደርጉ የአጋንንት መናፍስት ናቸው፤ ሁሉን በሚችል አምላክ ታላቅ ቀን ለሚሆነው ጦርነት እንዲሰበስቧቸው ወደ ዓለም ሁሉ ነገሥታት ይሄዳሉ።

15“እነሆ፤ እንደ ሌባ እመጣለሁ፤ ዕራቍቱን እንዳይሆን ኀፍረቱም እንዳይታይ ነቅቶ ልብሱን የሚጠብቅ ሰው ብፁዕ ነው።”

16እነርሱም ነገሥታቱን በዕብራይስጥ አርማጌዶን በሚባል ስፍራ ሰበሰቧቸው።

17ሰባተኛውም መልአክ ጽዋውን በአየር ላይ አፈሰሰ፤ በቤተ መቅደሱ ውስጥ ካለው ዙፋን “ተፈጸመ” የሚል ታላቅ ድምፅ ወጣ።

18ከዚያም መብረቅ፣ ድምፅ፣ ነጐድጓድና ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ ሰው በምድር ላይ ከተፈጠረ ጀምሮ እንዲህ ያለ ታላቅ የምድር መናወጥ ታይቶ አይታወቅም፤ ነውጡም እጅግ ታላቅ ነበር።

19ታላቂቱ ከተማ ከሦስት ተከፈለች፤ የሕዝቦች ከተሞችም ፈራረሱ፤ እግዚአብሔርም ታላቂቱን ባቢሎን አስታወሰ፤ በብርቱ ቍጣው ወይን ጠጅ የተሞላውን ጽዋ ሰጣት።

20ደሴቶች ሁሉ ሸሹ፤ ተራሮችም ሊገኙ አልቻሉም።

21በሚዛን ሲመዘን እያንዳንዱ አርባ አምስት ኪሎ ግራም የሚሆን ታላቅ በረዶ በሰዎች ላይ ከሰማይ ወረደባቸው፤ መቅሠፍቱ እጅግ አሠቃቂ ስለ ነበር፣ ሰዎቹ ከበረዶው መቅሠፍት የተነሣ እግዚአብሔርን ተሳደቡ።

ማብራሪያ

ራዕይ 16:1-7 የእግዚአብሔር ፈቃድ በሰማይ እንደተደረገች እንዲሁ በምድርም እንድትደረግ መጸለይ ይገባናል። እዚህ ላይ የእግዚአብሔር አቅርቦት (ፕሮቪደንስ) የሆኑ አስከፊ ፍርዶች በተከታታይ ቀርበዋል፤ ይህም ከግብፅ መቅሰፍቶች አንዳንዶቹን የሚያመለክት ይመስላል። ኃጢአቶቹ ተመሳሳይ እንደነበሩ ሁሉ ቅጣቶቹም እንዲሁ ነበሩ። ጽዋዎቹ ሰባቱን መለከቶች ያመለክታሉ፣ እነሱም የክርስቶስ ተቃዋሚ መነሳትን ያሳዩ ነበር፤ የቤተክርስቲያን ጠላቶች ውድቀት ደግሞ ከእነሱ መነሳት ጋር የተወሰነ ተመሳሳይነት ይኖረዋል። ምድራቸው፣ አየራቸው፣ ባሕራቸው፣ ወንዞቻቸው፣ ከተሞቻቸው ሁሉ፤ በዚያ ሕዝብ ክፋት ምክንያት ለጥፋት ተፈርደዋል፣ ሁሉም የተረገሙ ናቸው። የእግዚአብሔርን፣ የክርስቶስን እና የቅድስናን ግትር ጠላቶች ላይ የሚፈጸመውን መለኮታዊ የበቀል እርምጃ የሚያዩ ወይም የሚፈጽሙ መላእክት፣ የእርሱን ጽድቅና እውነት ሲያመሰግኑ፤ እንዲሁም በጭካኔ በሚያሳድዱ ሰዎች ላይ ቅዱሳኑንና ነቢያቱን ያደረሱባቸውን መከራና ስቃይ ሲያመጣ፣ አስፈሪ ፍርዶቹን ሲያመልኩ ምንም አያስደንቅም።

16:8-11 የሰው ልብ እጅግ በጣም ክፉ ስለሆነ፣ ልዩ የሆነው የእግዚአብሔር ጸጋ ከሌለ በቀር በጣም ከባድ መከራዎች እንኳን ማንንም ወደ ንስሐ አያመጡም። ገሃነም ራሱ በስድብ የተሞላ ነው፤ ሰዎች ይበልጥ በሰቃዩ መጠን፣ እና በመከራቸው ውስጥ የእግዚአብሔርን እጅ ይበልጥ በግልጽ በሚያዩ መጠን፣ በዚያው መጠን ይበልጥ በቁጣ በእርሱ ላይ እንደሚቆጡ የማያውቁት ሁሉ የሰው ልጅን ባህሪ ታሪክን፣ መጽሐፍ ቅዱስን፣ እና የራሳቸውን ልብ የማያውቁ ናቸው።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG ለሰባቱም መላእክት፦ “ሄዳችሁ የእግዚአብሔርን ቁጣ ጽዋዎች በምድር ውስጥ አፍስሱ፡” የሚል ታላቅ ድምፅ ከመቅደሱ ሰማሁ። አማርኛ ENGNIV Then I heard a loud voice from the temple saying to the seven angels, “Go, pour out the seven bowls of God's wrath on t… English BCV ካብታ መቕደስ ከዓ፥ ነቶም ሸውዓተ መላእኽቲ፥ “ኪዱ፥ ነቲ ፅዋዕ ቝጥዓ እግዚኣብሄር፥ ናብ ምድሪ ኣፍስስዎ” ዝብሎም፥ ብርቱዕ ድምፂ ሰማዕኹ። ትግርኛ GAZBIB Yommus mana qulqullummaa sana keessaa sagalee guddaa ergamoota torban sanaan, ?Dhaqaa, waciitii dheekkamsa Waaqayyoo to… Afaan Oromoo BCV GIZ ወይቤሎሙ ቃል እምሰማይ እምነ መቅደሱ ለእልክቱ ሰብዐቱ መላእክት፦ “ሑሩ ወከዐዉ ጽዋዐ መዓቱ ለእግዚአብሔር ውስተ ኵላ ምድር።” giz GAZGAZ Yommus mana qulqullummaa sana keessaa sagalee guddaa ergamoota torban sanaan, ?Dhaqaa, waciitii dheekkamsa Waaqayyoo to… Afaan Oromoo BCV aksum ካብታ መቕደስ ከዓ፥ ነቶም ሸውዓተ መላእኽቲ፥ “ኪዱ፥ ነቲ ፅዋዕ ቝጥዓ እግዚኣብሄር፥ ናብ ምድሪ ኣፍስስዎ” ዝብሎም፥ ብርቱዕ ድምፂ ሰማዕኹ። ትግርኛ SWAHSUV Nikasikia sauti kuu kutoka hekaluni, ikiwaambia wale malaika saba, Enendeni, mkavimimine vile vitasa saba vya ghadhabu … Kiswahili