ራእይ ዮሃንስ 12

AMHNIVአማርኛ17 ጥቅሶች3:34 አዳምጥ
አዳምጥ 3:34 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ታላቅና አስደናቂ ምልክት በሰማይ ታየ፤ ፀሓይን የለበሰች፣ ጨረቃን ከእግሮቿ በታች የረገጠችና በራሷም ላይ ዐሥራ ሁለት ከዋክብት ያሉት አክሊል የደፋች አንዲት ሴት ታየች።

2እርሷም ነፍሰ ጡር ነበረች፤ ልትወልድ ስትል ምጥ ይዞአት ተጨንቃ ጮኸች።

3ከዚያም ሌላ ምልክት በሰማይ ታየ፤ እነሆ፤ ሰባት ራሶችና ዐሥር ቀንዶች የነበሩት፣ በራሶቹም ላይ ሰባት አክሊል የደፋ ታላቅ ቀይ ዘንዶ ታየ።

4ጅራቱ የከዋክብትን አንድ ሦስተኛ ከሰማይ ስቦ ወደ ምድር ጣላቸው፤ እርሷም በወለደች ጊዜ ልጇን ለመዋጥ ፈልጎ ዘንዶው ልትወልድ በተቃረበችው ሴት ፊት ቆመ።

5ሕዝቦችን ሁሉ በብረት በትር የሚገዛውን ወንድ ልጅ ወለደች፤ ልጇም ወደ እግዚአብሔርና ወደ ዙፋኑ ተነጠቀ።

6ሴቲቱም አንድ ሺህ ሁለት መቶ ሥልሳ ቀን ክብካቤ እንዲደረግላት እግዚአብሔር ወዳ ዘጋጀላት ስፍራ ወደ በረሓ ሸሸች።

7በሰማይም ጦርነት ሆነ፤ ሚካኤልና መላእክቱ ከዘንዶው ጋር ተዋጉ፤ ዘንዶውና መላእክቱም መልሰው ተዋጓቸው፤

8ነገር ግን ድል ተመቱ፤ በሰማይም የነበራቸውን ስፍራ ዐጡ።

9ታላቁ ዘንዶ፣ የጥንቱ እባብ ተጣለ፤ እርሱም ዲያብሎስ ወይም ሰይጣን ተብሎ የሚጠራው፣ ዓለምን ሁሉ የሚያስተው ነው፤ እርሱ ወደ ምድር ተጣለ፤ መላእክቱም ከእርሱ ጋር ተጣሉ።

10ከዚህ በኋላ ታላቅ ድምፅ በሰማይ እንዲህ ሲል ሰማሁ፤ “አሁን የአምላካችን ማዳን፣ ኀይልና መንግሥት፣ የእርሱ ክርስቶስ ሥልጣንም መጥቶአል። ቀንና ሌሊት በአምላካችን ፊት ሲከሳቸው የነበረው፣ የወንድሞቻችን ከሳሽ ተጥሎአልና።

11እነርሱም በበጉ ደም፣ በምስክርነታቸውም ቃል፣ ድል ነሡት፤ እስከ ሞት ድረስ እንኳ፣ ለነፍሳቸው አልሳሱም።

12ስለዚህ ሰማያት ሆይ፣ በውስጣቸውም የምትኖሩ ሆይ፣ ደስ ይበላችሁ፤ ምድርና ባሕር ግን ወዮላችሁ ምክንያቱም ዲያብሎስ ጥቂት ዘመን ብቻ እንደ ቀረው ስላወቀ፣ በታላቅ ቍጣ ተሞልቶ ወደ እናንተ ወርዶአል።

13ዘንዶው ወደ ምድር እንደተጣለ ባየ ጊዜ፣ ወንድ ልጅ የወለደችውን ሴት አሳደዳት።

14ሴቲቱም በበረሓ ወደ ተዘጋጀላት ስፍራ በርራ መሄድ እንድትችል ሁለት የታላቁ ንስር ክንፎች ተሰጣት፤ ይህም የሆነው በዚያ ከእባቡ ፊት ርቃ ለአንድ ዘመን፣ ለዘመናትና ለዘመን እኩሌታ በክብካቤ እንድትኖር ነው።

15እባቡም ሴቲቱ በጐርፍ ተጠራርጋ እንድትወሰድ፣ እንደ ወንዝ ያለ ውሃ ከአፉ ተፋ።

16ምድር ግን ሴቲቱን ረዳቻት፤ አፏንም ከፍታ ዘንዶው ከአፉ ያፈሰሰውን ወንዝ ዋጠች።

17ዘንዶውም በሴቲቱ ላይ ተቈጣ፤ ከቀሩት ልጆቿም ጋር ሊዋጋ ሄደ፤ እነርሱ የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚጠብቁና የኢየሱስን ምስክር አጥብቀው የያዙ ናቸው።

ማብራሪያ

ዮሐንስ ራእይ 12:1-6

ሐዋርያው በራእይ በሰማይ ቤተ ክርስቲያንን፣ የምእመናን እናትን፣ በሴት ምሳሌነት አይቶአታል። እርስዋም ፀሐይን ለብሳ ነበር፤ በጽድቅ ተቀባይነት (በመጽደቅ)፣ በቅድሳት እና ከጽድቅ ፀሐይ ከሆነው ከክርስቶስ ጋር ባላት አንድነት የተነሳ ታበራ ነበር። ጨረቃ ከእግሮችዋ በታች ነበር፤ ይህም በሙሴ ከተገለጠው ከተንጸባራቂውና ደካማው የራእይ ብርሃን የበላይ እንደነበረች ያሳያል። በራሷ ላይ የአሥራ ሁለት ከዋክብት አክሊል ነበራት፤ በአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት የተሰበከው የወንጌል ትምህርት ለሁሉም እውነተኛ አማኞች የክብር አክሊል ነው። ቅዱስ ቤተሰብን ለመውለድ በምጥ ላይ እንደነበረች፤ የኃጢአተኞች መንቃት ወደ ንስሐቸው እንዲያመራ ትመኝ ነበር።

ዘንዶ የሰይጣን እና የእርሱ ዋና ወኪሎች፣ ወይም በምድር ላይ እርሱን ወክለው የሚገዙ የታወቀ ምሳሌ ነው። በዚያን ጊዜ በሰባት ኮረብቶች ላይ የተገነባችው ከተማ የነበረችው የሮም አረማዊ ግዛት ነበር። አሥር ቀንዶች እንዳሉት፣ ወደ አሥር መንግሥታት የተከፈለ ነበር። ሰባት አክሊሎች የነበሩት ሲሆን፣ እነዚህም ሰባት የአገዛዝ ዓይነቶችን ይወክላሉ። በጅራቱም የሰማይን ከዋክብት አንድ ሦስተኛውን እየጎተተ ወደ ምድር እንደ ጣለ፣ ይህ የሚያሳየው የአገልጋዮችንና የመምህራንን ስደትና ማሳት ነው። የክርስትናን ሃይማኖት ለመጨፍለቅ የሚያሰድድ ቢሆንም፣ የጠላቶች ተቃውሞ ቢኖርም፣ ቤተ ክርስቲያን እውነተኛና ታማኝ የሆኑ ምስክሮችን፣ ክርስቶስ በእውነት ሙሉ በሙሉ እንደገና የተመሠረተባቸውን፣ ወንድ ዘር ወለደች፤ እርሱም አሕዛብን የሚገዛው የእግዚአብሔር ልጅ የሆነው የክርስቶስ ምሥጢር ነበር፤ አባላቱም በእርሱ መብት ያንኑ ክብር የሚካፈሉበት። ይህ የተባረከ ዘር በእግዚአብሔር ተጠብቆ ነበር።

ራእይ ፲፪፥፯-፲፩

የዘንዶው ሙከራዎች በቤተ ክርስቲያን ላይ ከንቱ ሆነዋል፤ ለራሱ ፍላጎቶችም ገዳይ ሆነውበታል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG ታላቅ ምልክትም በሰማይ ታየ ፀሐይን ተጐናጽፋ ጨረቃ ከእግሮችዋ በታች ያላት በራስዋም ላይ የአሥራ ሁለት ከዋክብት አክሊል የሆነላት አንዲት ሴት ነበረች። አማርኛ ENGNIV A great and wondrous sign appeared in heaven: a woman clothed with the sun, with the moon under her feet and a crown of… English BCV ዓብዪ ምልክት ድማ ኣብ ሰማይ ተርኣየ፦ ፀሓይ ዝተወንዘፈት፥ ወርሒ እውን ኣብ ትሕቲ ኣእጋራ ዘለዋ፥ ዓሰርተ ኽልተ ኸዋኽብቲ ዘለዎ ኣክሊል ድማ፥ ኣብ ርእሳ ዝደፍአት፥ ሓንቲ ሰበይቲ ተርኣየት። ትግርኛ GAZBIB Wanti guddaan dinqisiisaan tokko, waaqa keessatti in argame; dubartiin biiftuu uffattee, ji'a miilla jala kaa'attee, go… Afaan Oromoo BCV GIZ ወአስተርአየ ተኣምር ዐቢይ በውስተ ሰማይ ብእሲት እንተ ትለብስ ፀሓየ፤ ወወርኅ ታሕተ እገሪሃ ወዲበ ርእሳኒ አክሊል ዘዐሠርቱ ወክልኤቱ ከዋክብት። giz GAZGAZ Wanti guddaan dinqisiisaan tokko, waaqa keessatti in argame; dubartiin biiftuu uffattee, ji'a miilla jala kaa'attee, go… Afaan Oromoo SWAHSUV Na ishara kuu ilionekana mbinguni; mwanamke aliyevikwa jua, na mwezi ulikuwa chini ya miguu yake, na juu ya kichwa chak… Kiswahili ENGESV And a great sign appeared in heaven: a woman clothed with the sun, with the moon under her feet, and on her head a crow… English