ራእይ ዮሃንስ 11

AMHEVGአማርኛ19 ጥቅሶች4:00 አዳምጥ
አዳምጥ 4:00 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1በትር የሚመስል መለኪያ ለእኔ ተሰጠኝ፥ እንዲህም ተባለልኝ፦ “ተነሥተህ የእግዚአብሔርን መቅደስና መሠዊያውን በዚያም የሚሰግዱትን ለካ።

2በመቅደሱም ውጭ ያለው እድሞ ለአሕዛብ ተሰጥቶአልና ተወው አትለካውም፤ እነርሱም አርባ ሁለት ወር የተቀደሰችውን ከተማ ይረግጡአታል።

3ለሁለቱም ምስክሮቼ ማቅ ለብሰው ሺህ ከሁለት መቶ ስድሳ ቀን ትንቢት ሊናገሩ እሰጣለሁ።”

4እነዚህ በምድር ጌታ ፊት የሚቆሙ ሁለቱ ወይራዎችና ሁለቱ መቅረዞች ናቸው።

5ማንምም ሊጐዳቸው ቢወድ እሳት ከአፋቸው ይወጣል ጠላቶቻቸውንም ይበላል፤ ማንም ሊጐዳቸው ቢወድም እንዲሁ ሊገደል ይገባዋል።

6እነዚህ ትንቢት በሚናገሩበት ወራት ዝናብ እንዳይዘንብ ሰማይን ሊዘጉ ሥልጣን አላቸው፥ ውኃዎችንም ወደ ደም ሊለውጡ በሚፈልጉበትም ጊዜ ሁሉ በመቅሠፍት ሁሉ ምድርን ሊመቱ ሥልጣን አላቸው።

7ምስክራቸውን ከፈጸሙ በኋላ ከጥልቁ የሚወጣው አውሬ ይዋጋቸዋል ያሸንፋቸውማል ይገድላቸውማል።

8በድናቸውም በታላቂቱ ከተማ አደባባይ ይተኛል እርስዋም በመንፈሳዊ ምሳሌ ሰዶምና ግብፅ የተባለች ደግሞ ጌታቸው የተሰቀለባት ናት።

9ከወገኖችና ከነገዶችም ከቋንቋዎችም ከአሕዛብም የሆኑ ሰዎች ሦስት ቀን ተኵል በድናቸውን ይመለከታሉ፥ በድናቸውም ወደ መቃብር ሊገባ አይፈቅዱም።

10እነዚህም ሁለት ነቢያት በምድር የሚኖሩትን ስለ ሣቀዩ በምድር የሚኖሩት በእነርሱ ላይ ደስ ይላቸዋል በደስታም ይኖራሉ እርስ በርሳቸውም ስጦታ ይሰጣጣሉ።

11ከሦስቱ ቀን ተኵልም በኋላ ከእግዚአብሔር የወጣ የሕይወት መንፈስ ገባባቸው በእግሮቻቸውም ቆሙ፥ ታላቅም ፍርሃት በሚመለከቱት ላይ ወደቀባቸው።

12በሰማይም፦ “ወደዚህ ውጡ፡” የሚላቸውን ታላቅ ድምፅ ሰሙ፤ ጠላቶቻቸውም እየተመለከቱአቸው ወደ ሰማይ በደመና ወጡ።

13በዚያም ሰዓት ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፥ ከከተማይቱም አሥረኛው እጅ ወደቀ፥ በመናወጥም ሰባት ሺህ ሰዎች ተገደሉ፥ የቀሩትንም ፍርሃት ያዛቸው፥ ለሰማዩም አምላክ ክብር ሰጡ።

14ሁለተኛው ወዮ አልፎአል፤ እነሆ፥ ሦስተኛው ወዮ በቶሎ ይመጣል።

15ሰባተኛው መልአክ ነፋ፤ በሰማይም፦ “የዓለም መንግሥት ለጌታችንና ለእርሱ ለክርስቶስ ሆነች፥ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ይነግሣል፡” የሚሉ ታላላቅ ድምፆች ሆኑ።

16በእግዚአብሔርም ፊት በዙፋኖቻቸው የተቀመጡ ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በግምባራቸው ተደፍተው ለእግዚአብሔር እየሰገዱ፡

17እንዲህ አሉ፦ “ያለህና የነበርህ ሁሉን የምትገዛ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ትልቁን ኃይልህን ስለ ያዝህ ስለ ነገሥህም እናመሰግንሃለን፤

18አሕዛብም ተቈጡ፥ ቍጣህም መጣ፥ በሙታንም ትፈርድ ዘንድ ዘመን መጣ፥ ለባሪያዎችህም ለነቢያትና ለቅዱሳን ስምህንም ለሚፈሩት ለታናናሾችና ለታላላቆችም ዋጋቸውን ትሰጥ ዘንድ፥ ምድርንም የሚያጠፉትን ታጠፋ ዘንድ ዘመን መጣ።”

19በሰማይም ያለው የእግዚአብሔር መቅደስ ተከፈተ፥ የኪዳኑም ታቦት በመቅደሱ ታየ፥ መብረቅና ድምፅም ነጐድጓድም የምድርም መናወጥ ታላቅም በረዶ ሆነ።

ማብራሪያ

ምዕራፍ ፲፩፥ ፩ እና ፪። መቅደሱን ስለመለካት የሚናገረው ይህ ትንቢታዊ ክፍል የሕዝቅኤልን ራእይ የሚያመለክት ይመስላል። የዚህ መለኪያ ዓላማ የቤተ ክርስቲያንን መጠበቅ በሕዝባዊ አደጋ ጊዜያት፣ ወይም ለፈተናዋ፣ ወይም ደግሞ ለተሀድሶዋ ነው። አምላኪዎቹ የእግዚአብሔርን ክብር ፍጻሜያቸው ያደርጉ እንደሆነና ቃሉንም መመሪያቸው ያደርጉ እንደሆነ፣ በሁሉም የአምልኮ ተግባሮቻቸው መለካት አለባቸው። በውጨኛው አደባባይ ያሉት በሐሰት መንገድ ወይም በግብዝ ልብ ያመልካሉ፤ ከጠላቶቹም መካከል ይገኛሉ። እግዚአብሔር በዚህ ዓለም መቅደስና መሠዊያ እስከ ዘመን ፍጻሜ ድረስ ይኖረዋል። መቅደሱን በጥብቅ ይመለከታል። ቅድስቲቱ ከተማ፣ የሚታየው ቤተ ክርስቲያን፣ በእግር ትረገጣለች፤ በጣዖት አምላኪዎች፣ በማያምኑና በግብዞች ተሞልታለች። ነገር ግን የቤተ ክርስቲያን ውድመቶች የተወሰኑ ናቸው፤ ከችግሮቿም ሁሉ ትድናለች።

ራዕይ 11:3-13

በሚጨፈለቅበት ዘመን፣ እግዚአብሔር የታመኑ ምስክሮቹን ቃሉና አምልኮው እውነት መሆናቸውን እንዲሁም የመንገዶቹንም የላቀነት ለመመስከር አስቀርቶ ነበር። የእነዚህ ምስክሮች ቁጥር ትንሽ ቢሆንም፣ በቂ ግን ነው። ማቅ ለብሰው ይተነብያሉ። ይህ የተሠቃዩበትንና የተሳደዱበትን ሁኔታቸውን እንዲሁም የተቃወሙባቸውን አስጸያፊ ነገሮች በጥልቅ ማዘናቸውን ያመለክታል። በታላቅና ከባድ ሥራቸው ወቅት፣ ሥራው እስኪጠናቀቅ ድረስ ድጋፍ ያገኛሉ። ለ1260 ዓመታት በዋናው ጊዜ ማቅ ለብሰው ከተነበዩ በኋላ፣ የሰይጣን ታላቅ መሣሪያ የሆነው ፀረ-ክርስቶስ ለተወሰነ ጊዜ በኃይልና በአመፅ በእነርሱ ላይ ይዋጋቸው ነበር። ብርሃንን የሚቃወሙ ጽኑ ዓመፀኞች ትምህርታቸውና ምግባራቸው የሚያሠቃያቸውን የክርስቶስን ታማኝ አገልጋዮች ዝም ሲያሰኙ፣ ሲያርቁ ወይም ሲያጠፉ፣ እንደ መልካም ክስተት በመቁጠር ይደሰታሉ።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV I was given a reed like a measuring rod and was told, “Go and measure the temple of God and the altar, and count the wo… English BCV ድሕሪዙይ ዘንጊ ዝመስል መዐቀኒ ተውሃበኒ እሞ “ተስእ፤ ነቲ መቕደስ እግዚኣብሄርን፥ ነቲ መሰውእን ዓቅኖ፤ ነቶም ኣብኡ ዝሰግዱ ዘለዉውን ቍፀሮም።(ሀ) ትግርኛ GAZBIB Uleen akka ulee safaraa tokko anaaf in kenname; yommus tokko anatti dubbatee, ?Ka'i! Mana qulqullummaa Waaqayyoo iddoo … Afaan Oromoo BCV GIZ ወመጠወኒ ኅለተ ወርቅ ዘመጠነ በትር ወይቤለኒ፦ “ንሣእ ወመጥን ቤተ መቅደሱ ለእግዚአብሔር ወምሥዋዖ ወኀበሂ ይሰግዱ ሎቱ። giz GAZGAZ Uleen akka ulee safaraa tokko anaaf in kenname; yommus tokko anatti dubbatee, ?Ka'i! Mana qulqullummaa Waaqayyoo iddoo … Afaan Oromoo BCV aksum ድሕሪዙይ ዘንጊ ዝመስል መዐቀኒ ተውሃበኒ እሞ “ተስእ፤ ነቲ መቕደስ እግዚኣብሄርን፥ ነቲ መሰውእን ዓቅኖ፤ ነቶም ኣብኡ ዝሰግዱ ዘለዉውን ቍፀሮም።(ሀ) ትግርኛ AMHNIV ከዚያም ሸምበቆ የመሰለ መለኪያ በትር ተሰጠኝ፤ እንዲህም ተባልሁ፤ “ሄደህ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስና መሠዊያውን ለካ፤ በዚያም የሚያመልኩትን ቊጠር። አማርኛ SWAHSUV Nikapewa mwanzi kama fimbo; na mmoja akaniambia, Inuka, ukalipime hekalu la Mungu, na madhabahu, na hao wasujuduo humo. Kiswahili