ራእይ ዮሃንስ 10

AMHEVGአማርኛ11 ጥቅሶች2:08 አዳምጥ
አዳምጥ 2:08 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ሌላም ብርቱ መልአክ ደመና ተጐናጽፎ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፤ በራሱም ላይ ቀስተ ደመና ነበረ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ እግሮቹም እንደ እሳት ዓምዶች ነበሩ፥

2የተከፈተችንም ታናሽ መጽሐፍ በእጁ ያዘ። ቀኝ እግሩንም በባሕር ላይ ግራውንም በምድር ላይ አኖረ፥ እንደሚያገሣም አንበሳ በታላቅ ድምፅ ጮኸ።

3በጮኸም ጊዜ ሰባቱ ነጐድጓድ በየድምፃቸው ተናገሩ።

4ሰባቱ ነጐድጓድ በተናገሩ ጊዜ ልጽፍ አሰብሁ፤ ከሰማይም፦ “ሰባቱ ነጐድጓድ የተናገሩትን ነገር በማኅተም ዝጋው አትጻፈውም” የሚል ድምፅ ሰማሁ።

5በባሕርና በምድርም ላይ ሲቆም ያየሁት መልአክ ቀኝ እጁን ወደ ሰማይ አሻቅቦ ዘረጋ፥

6ሰማይንና በእርሱም ያሉትን፥ ምድርንና በእርስዋም ያሉትን፥ ባሕርንና በእርሱም ያሉትን በፈጠረው፥ ከዘላለምም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ሆኖ በሚኖረው ምሎ፦ “ወደ ፊት አይዘገይም፥

7ዳሩ ግን ሰባተኛው መልአክ ሊነፋ ባለው ጊዜ ድምፁም በሚሰማበት ዘመን፥ ለባሪያዎቹ ለነቢያት የምስራች እንደ ሰበከላቸው የእግዚአብሔር ምሥጢር ይፈጸማል” አለ።

8ከሰማይም የሰማሁት ድምፅ እንደ ገና ሲናገረኝና፦ “ሂድና በባሕርና በምድር ላይ ከሚቆመው መልአክ በእጁ ያለችውን የተከፈተችውን መጽሐፍ ውሰድ፡” ሲል ሰማሁ።

9ወደ መልአኩም ሄጄ፦ “ታናሺቱን መጽሐፍ ስጠኝ፡” አልሁት። እርሱም፦ “ውሰድና ብላት፥ ሆድህንም መራራ ታደርገዋለች በአፍህ ግን እንደ ማር ትጣፍጣለች፡” አለኝ።

10ከመልአኩም እጅ ታናሺቱን መጽሐፍ ወስጄ በላኋት በአፌም እንደ ማር ጣፋጭ ሆነች፤ ከበላኋት በኋላም ሆዴ መራራ ሆነ።

11“በብዙ ወገኖችና በአሕዛብም በቋንቋዎችም በነገሥታትም ላይ እንደ ገና ትንቢት ትናገር ዘንድ ይገባሃል” ተባለልኝ።

ማብራሪያ

10:1-7 ሐዋርያው ሌላ ምሳሌያዊ እይታ አየ። ይህን መገለጥ ያሳወቀው አካል ምናልባት ጌታችንና አዳኛችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነበር፤ ወይም ደግሞ የእርሱን ክብር ለመግለጥ ነበር። እርሱ ክብሩን ይሸፍናል፤ ይህ ክብር ደግሞ ሟች የሆኑ ዓይኖች ለማየት የሚከብድ ታላቅ ነው። በአሰራሮቹም ላይ መጋረጃ ይጥላል። በቀኙ ራሱ ላይ ቀስተ ደመና ነበረ፤ ጌታችን ሁልጊዜ ኪዳኑን ያስታውሳል። አስፈሪ ድምፁ በሰባት ነጎድጓዶች ተስተጋብቷል፤ እነዚህም የአምላክን አሳብ የሚገልጡ አስገራሚና አስፈሪ መንገዶች ናቸው። የሰባቱንም ነጎድጓዶች ይዘትም ሆነ እንዲገቱ የተደረጉበትን ምክንያት አናውቅም። በታሪክ ውስጥ ታላላቅ ክስተቶች አሉ፤ ምናልባትም ከክርስትና ቤተ ክርስቲያን ጋር የሚዛመዱ፣ በግልጽ ትንቢት ውስጥ ያልተገለጹ።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV Then I saw another mighty angel coming down from heaven. He was robed in a cloud, with a rainbow above his head; his fa… English BCV ድሕሪዙይ ካልእ ብርቱዕ መልኣኽ፥ ደመና ተወንዚፉ፥ ካብ ሰማይ ክወርድ እንተሎ ረአኹ። ኣብ ልዕሊ ርእሱ ኸዓ፥ ቀስተ ደመና ነበረ፤ ገፁ ድማ ኸም ፀሓይ ብሩህ ነበረ፤ ኣእጋሩውን፥ ከም ኣዕማድ… ትግርኛ GAZBIB Ergasii immoo ergamaan aango-qabeessi biraa tokko waaqa keessaa utuu gad bu'uu nan arge. Inni duumessa ofitti maree, na… Afaan Oromoo BCV GIZ ወእምዝ ወረደ ካልእ መልአክ ዐቢይ እምሰማይ ወይትዐጸፍ ደመና ውስተ ርእሱ ወብሩህ ገጹ ከመ ፀሓይ ወእገሪሁ ከመ አዕማደ እሳት። giz GAZGAZ Ergasii immoo ergamaan aango-qabeessi biraa tokko waaqa keessaa utuu gad bu'uu nan arge. Inni duumessa ofitti maree, na… Afaan Oromoo BCV aksum ድሕሪዙይ ካልእ ብርቱዕ መልኣኽ፥ ደመና ተወንዚፉ፥ ካብ ሰማይ ክወርድ እንተሎ ረአኹ። ኣብ ልዕሊ ርእሱ ኸዓ፥ ቀስተ ደመና ነበረ፤ ገፁ ድማ ኸም ፀሓይ ብሩህ ነበረ፤ ኣእጋሩውን፥ ከም ኣዕማድ… ትግርኛ AMHNIV ከዚህ በኋላ ሌላ ብርቱ መልአክ ደመና ተጐናጽፎ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፤ እርሱም በራሱ ላይ ቀስተ ደመና ነበር። ፊቱ እንደ ፀሓይ፣ እግሮቹ እንደ እሳት ዐምዶች ነበሩ። አማርኛ SWAHSUV Kisha nikaona malaika mwingine mwenye nguvu akishuka kutoka mbinguni, amevikwa wingu; na upinde wa mvua juu ya kichwa c… Kiswahili