ራእይ ዮሃንስ 10

AMHNIVአማርኛ11 ጥቅሶች2:16 አዳምጥ
አዳምጥ 2:16 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ከዚህ በኋላ ሌላ ብርቱ መልአክ ደመና ተጐናጽፎ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፤ እርሱም በራሱ ላይ ቀስተ ደመና ነበር። ፊቱ እንደ ፀሓይ፣ እግሮቹ እንደ እሳት ዐምዶች ነበሩ።

2በእጁም የተከፈተች ትንሽ ጥቅልል መጽሐፍ ይዞ ነበር፤ ቀኝ እግሩን በባሕር ላይ፣ ግራ እግሩን በምድር ላይ አኖረ፤

3እንደሚያገሣ አንበሳም ድምፁን ከፍ አድርጎ ጮኸ፤ በጮኸም ጊዜ የሰባቱ ነጐድጓዶች ድምፆች ተናገሩ።

4ሰባቱ ነጐድጓዶች በተናገሩ ጊዜ፣ ለመጻፍ ተዘጋጀሁ፤ ነገር ግን፣ “ሰባቱ ነጐድጓዶች የተናገሩትን በማኅተም ዝጋው እንጂ አትጻፍ” የሚል ድምፅ ከሰማይ ሰማሁ።

5ከዚህ በኋላ በባሕርና በምድር ላይ ቆሞ ያየሁት መልአክ ቀኝ እጁን ወደ ሰማይ አነሣ፤

6እርሱም ከዘላለም እስከ ዘላለም በሚኖረው፣ ሰማይንና በውስጡ ያሉትን፣ ምድርንና በውስጧ ያሉትን፣ ባሕርንና በውስጡ ያሉትን በፈጠረው በእርሱ ማለ፤ እንዲህም አለ፤ “ከእንግዲህ መዘግየት አይኖርም፤

7ነገር ግን ሰባተኛው መልአክ መለከቱን በሚነፋባቸው ቀኖች፣ ለአገልጋዮቹ ለነቢያት በገለጠላቸው መሠረት የእግዚአብሔር ምስጢር ይፈጸማል።”

8ከዚያም ከሰማይ የሰማሁት ድምፅ እንደ ገና እንዲህ ሲል ተናገረ፤ “ሂድ፤ በባሕርና በምድር ላይ ከቆመው መልአክ እጅ የተከፈተችውን ጥቅልል መጽሐፍ ውሰድ።”

9እኔም ወደ መልአኩ ሄጄ ትንሿን ጥቅልል መጽሐፍ እንዲሰጠኝ ጠየቅሁት፤ እርሱም፣ “ውሰድና ብላት፤ ሆድህን መራራ ታደርገዋለች፤ በአፍህ ግን እንደ ማር ትጣፍጣለች” አለኝ።

10ትንሿንም መጽሐፍ ከመልአኩ እጅ ተቀብዬ በላኋት፤ በአፌ እንደ ማር ጣፈጠች፤ ከበላኋት በኋላ ግን ሆዴ መራራ ሆነ፤

11ከዚያም፣ “ስለ ብዙ ሕዝቦች፣ ወገኖች፣ ቋንቋዎችና ነገሥታት እንደ ገና ትንቢት ልትናገር ይገባሃል” ተባልሁ።

ማብራሪያ

10:1-7 ሐዋርያው ሌላ ምሳሌያዊ እይታ አየ። ይህን መገለጥ ያሳወቀው አካል ምናልባት ጌታችንና አዳኛችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነበር፤ ወይም ደግሞ የእርሱን ክብር ለመግለጥ ነበር። እርሱ ክብሩን ይሸፍናል፤ ይህ ክብር ደግሞ ሟች የሆኑ ዓይኖች ለማየት የሚከብድ ታላቅ ነው። በአሰራሮቹም ላይ መጋረጃ ይጥላል። በቀኙ ራሱ ላይ ቀስተ ደመና ነበረ፤ ጌታችን ሁልጊዜ ኪዳኑን ያስታውሳል። አስፈሪ ድምፁ በሰባት ነጎድጓዶች ተስተጋብቷል፤ እነዚህም የአምላክን አሳብ የሚገልጡ አስገራሚና አስፈሪ መንገዶች ናቸው። የሰባቱንም ነጎድጓዶች ይዘትም ሆነ እንዲገቱ የተደረጉበትን ምክንያት አናውቅም። በታሪክ ውስጥ ታላላቅ ክስተቶች አሉ፤ ምናልባትም ከክርስትና ቤተ ክርስቲያን ጋር የሚዛመዱ፣ በግልጽ ትንቢት ውስጥ ያልተገለጹ።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG ሌላም ብርቱ መልአክ ደመና ተጐናጽፎ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፤ በራሱም ላይ ቀስተ ደመና ነበረ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ እግሮቹም እንደ እሳት ዓምዶች ነበሩ፥ አማርኛ ENGNIV Then I saw another mighty angel coming down from heaven. He was robed in a cloud, with a rainbow above his head; his fa… English BCV ድሕሪዙይ ካልእ ብርቱዕ መልኣኽ፥ ደመና ተወንዚፉ፥ ካብ ሰማይ ክወርድ እንተሎ ረአኹ። ኣብ ልዕሊ ርእሱ ኸዓ፥ ቀስተ ደመና ነበረ፤ ገፁ ድማ ኸም ፀሓይ ብሩህ ነበረ፤ ኣእጋሩውን፥ ከም ኣዕማድ… ትግርኛ GAZBIB Ergasii immoo ergamaan aango-qabeessi biraa tokko waaqa keessaa utuu gad bu'uu nan arge. Inni duumessa ofitti maree, na… Afaan Oromoo BCV GIZ ወእምዝ ወረደ ካልእ መልአክ ዐቢይ እምሰማይ ወይትዐጸፍ ደመና ውስተ ርእሱ ወብሩህ ገጹ ከመ ፀሓይ ወእገሪሁ ከመ አዕማደ እሳት። giz GAZGAZ Ergasii immoo ergamaan aango-qabeessi biraa tokko waaqa keessaa utuu gad bu'uu nan arge. Inni duumessa ofitti maree, na… Afaan Oromoo BCV aksum ድሕሪዙይ ካልእ ብርቱዕ መልኣኽ፥ ደመና ተወንዚፉ፥ ካብ ሰማይ ክወርድ እንተሎ ረአኹ። ኣብ ልዕሊ ርእሱ ኸዓ፥ ቀስተ ደመና ነበረ፤ ገፁ ድማ ኸም ፀሓይ ብሩህ ነበረ፤ ኣእጋሩውን፥ ከም ኣዕማድ… ትግርኛ SWAHSUV Kisha nikaona malaika mwingine mwenye nguvu akishuka kutoka mbinguni, amevikwa wingu; na upinde wa mvua juu ya kichwa c… Kiswahili