1እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፥ የሚያሳጣኝም የለም።
2በለመለመ መስክ ያሳድረኛል፤ በዕረፍት ውኃ ዘንድ ይመራኛል።
3ነፍሴን መለሳት፥ ስለ ስሙም በጽድቅ መንገድ መራኝ።
4በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ፡ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም፤ በትርህና ምርኵዝህ እነርሱ ያጸናኑኛል።
5በፊቴ ገበታን አዘጋጀህልኝ፡ በጠላቶቼ ፊት ለፊት፡ ራሴን በዘይት ቀባህ፥ ጽዋዬም የተረፈ ነው።
6ቸርነትህና ምሕረትህ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ይከተሉኛል፥ በእግዚአብሔርም ቤት ለዘላለም እኖራለሁ።