ትንቢተ ናሆም 2

AMHEVGአማርኛ13 ጥቅሶች2:28 አዳምጥ
አዳምጥ 2:28 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1የሚቀጠቅጥ በአንተ ላይ ወጥቶአል፤ ምሽግን ጠብቅ፥ መንገድንም ሰልል፤ ወገብህን አጽና፥ ኃይልህንም እጅግ አበርታ።

2ዘራፊዎች ዘርፈዋቸዋልና፥ የወይናቸውንም አረግ አጥፍተዋልና እግዚአብሔር የያዕቆብን ክብር እንደ እስራኤል ክብር ይመልሳል።

3የኃያላኑ ጋሻ ቀልቶአል፥ ጽኑዓንም ቀይ ልብስ ለብሰዋል። እርሱም በሚያዘጋጅበት ቀን ሰረገሎች እንደ እሳት ይንቦገቦጋሉ፤ የጦሩም ሶመያ ይወዛወዛል።

4ሰረገሎች በመንገድ ላይ ይነጕዳሉ፥ አደባባይም ይጋጫሉ፤ መልካቸው እንደ ፋና ነው፥ እንደ መብረቅም ይከንፋሉ።

5መሳፍንቱን ያስባል፤ በአረማመዳቸው ይሰናከላሉ፤ ፈጥነው በቅጥርዋ ላይ ይወጣሉ፥ መጠጊያም ተዘጋጀለት።

6የወንዞቹም መዝጊያዎች ተከፈቱ፥ የንጉሡ ቤትም ቀለጠች።

7ንግሥት ተገለጠች፥ ተማረከችም፥ ሴቶች ባሪያዎችዋም እንደ ርግብ እየጮኹና ደረታቸውን እየመቱ ዋይ ዋይ ይላሉ።

8ነነዌ ግን ከዱሮ ዘመን ጀምራ እንደ ተከማቸ ውኃ ነበረች፤ አሁን ግን ይሸሻሉ፤ እነርሱም፦ “ቁሙ፥ ቁሙ፡” ይላሉ፥ ነገር ግን የሚመለስ የለም።

9መዝገብዋ መጨረሻ የለውምና፥ የከበረውም የዕቃዋ ሁሉ ብዛት አይቈጠርምና ብሩን በዝብዙ፥ ወርቁንም በዝብዙ።

10ባዶና ባድማ ምድረ በዳም ሆናለች፤ ልብ ቀልጦአል፥ ጕልበቶችም ተብረክርከዋል፤ በወገብም ሁሉ ሕማም አለ፥ የሰዎችም ሁሉ ፊት ጠቍሮአል።

11የአንበሾችም መደብ፥ የአንበሾችም ደቦል የሚሰማራበት፥ አንበሳውና አንበሳይቱ ግልገሉም ሳይፈሩ የሚሄዱት ስፍራ ወዴት ነው?

12አንበሳው ለልጆቹ የሚበቃውን ነጠቀ፥ ለእንስቶቹም ሰበረላቸው ዋሻውን በንጥቂያ፥ መደቡንም በቅሚያ ሞልቶታል።

13እነሆ በአንቺ ላይ ነኝ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ ሰረገሎችዋንም አቃጥዬ አጤሳለሁ፥ ሰይፍም የአንበሳ ደቦሎችሽን ይበላቸዋል፤ ንጥቂያሽንም ከምድር አጠፋለሁ፥ የመልክተኞችሽን ድምፅ ከእንግዲህ ወዲህ አይሰማም።

ማብራሪያ

2:1-10 ነነዌ ይህንን ፍርድ ልታስወግደው አትችልም፤ በእግዚአብሔር ላይ ምንም ምክር ወይም ኃይል የለም። እግዚአብሔር በትዕቢተኞች ከተሞች ላይ ይመለከታል፣ እናም ያዋርዳቸዋል። ወራሪው ጠላት በነነዌ ላይ በሚገለጥበት ጊዜ የሚኖረውን አስፈሪ ገጽታ በተለየ ሁኔታ ተገልጿል። የአሦር ግዛት ወደ ባቢሎን ምርኮ ልትወሰድ እንደተቃረበች ንግሥት ተመስሏል። በሕሊና ውስጥ ያለ ጥፋተኝነት በክፉ ቀን ሰዎችን በፍርሃት ይሞላል፤ ሀብትና ክብር በመከራ ጊዜ፣ ወይም በቁጣ ቀን ለእኛ ምን ይረዱናል? ሆኖም ግን ለእንደዚህ አይነቶቹ ነገሮች ስንትና ስንት…

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6