የማርቆስ ወንጌል 9

AMHEVGአማርኛ46 ጥቅሶች6:51 አዳምጥ
አዳምጥ 6:51 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1እውነት እላችኋለሁ፥ በዚህ ከቆሙት ሰዎች የእግዚአብሔር መንግሥት በኃይል ስትመጣ እስኪያዩ ድረስ፥ ሞትን የማይቀምሱ አንዳንዶች አሉ፡ አላቸው።

2ከስድስት ቀንም በኋላ ኢየሱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ዮሐንስንም ይዞ ወደ ረጅም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው። በፊታቸውም ተለወጠ፥ ልብሱም አንጸባረቀ፤

3አጣቢም በምድር ላይ እንደዚያ ሊያነጣው እስከማይችል በጣም ነጭ ሆነ።

4ኤልያስና ሙሴም ታዩአቸው፥ ከኢየሱስም ጋር ይነጋገሩ ነበር።

5ጴጥሮስም መልሶ ኢየሱስን፦ “መምህር ሆይ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነውና አንድ ለአንተ አንድም ለሙሴ አንድም ለኤልያስ ሦስት ዳሶች እንሥራ” አለው።

6እጅግ ስለ ፈሩ የሚለውን አያውቅም ነበር።

7ደመናም መጥቶ ጋረዳቸው፥ ከደመናውም፦ “የምወደው ልጄ ይህ ነው፥ እርሱን ስሙት፡” የሚል ድምፅ መጣ።

8ድንገትም ዞረው ሲመለከቱ ከእነርሱ ጋር ከኢየሱስ ብቻ በቀር ማንንም አላዩም።

9ከተራራውም ሲወርዱ የሰው ልጅ ከሙታን እስኪነሣ ድረስ ያዩትን ለማንም እንዳይነግሩ አዘዛቸው።

10ቃሉንም ይዘው፦ “ከሙታን መነሣት ምንድር ነው?” እያሉ እርስ በርሳቸው ተጠያየቁ።

11እነርሱም፦ “ኤልያስ አስቀድሞ ሊመጣ እንዲገባው ጻፎች ስለ ምን ይላሉ?” ብለው ጠየቁት።

12እርሱም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ “ኤልያስማ አስቀድሞ ይመጣል ሁሉንም ያቀናናል፤ ስለ ሰው ልጅም እንዴት ተብሎ ተጽፎአል? ብዙ መከራ እንዲቀበል እንዲናቅም።

13ነገር ግን እላችኋለሁ፥ ኤልያስ ደግሞ መጥቶአል፥ ስለ እርሱም እንደ ተጸፈ የወደዱትን ሁሉ አደረጉበት።”

14ወደ ደቀ መዛሙርቱም በመጣ ጊዜ ብዙ ሕዝብ ሲከብቡአቸው ጻፎችም ከእነርሱ ጋር ሲከራከሩ አየ።

15ወዲያውም ሕዝቡ ሁሉ ባዩት ጊዜ ደነገጡ፥ ወደ እርሱም ሮጠው እጅ ነሡት።

16ጻፎችንም፦ “ስለ ምን ከእነርሱ ጋር ትከራከራላችሁ?” ብሎ ጠየቃቸው።

17ከሕዝቡ አንዱ መልሶ፦ “መምህር ሆይ፥ ዲዳ መንፈስ ያደረበትን ልጄን ወደ አንተ አምጥቼአለሁ፤

18በያዘውም ስፍራ ሁሉ ይጥለዋል፤ አረፋም ይደፍቃል፥ ጥርሱንም ያፋጫል ይደርቃልም፤ እንዲያወጡለትም ለደቀ መዛሙርትህ ነገርኋቸው፥ አልቻሉምም፡” አለው።

19እርሱም መልሶ፦ “የማታምን ትውልድ ሆይ፥ እስከመቼ ከእናንተ ጋር እኖራለሁ? እስከ መቼስ እታገሣችኋለሁ? ወደ እኔ አምጡት፡” አላቸው።

20ወደ እርሱም አመጡት። እርሱንም ባየ ጊዜ ያ መንፈስ ወዲያው አንፈራገጠው፤ ወደ ምድርም ወድቆ አረፋ እየደፈቀ ተንፈራፈረ።

21አባቱንም፦ “ይህ ከያዘው ስንት ዘመን ነው?” ብሎ ጠየቀው። እርሱም፦ “ከሕፃንነቱ ጀምሮ ነው፤

22ብዙ ጊዜም ሊያጠፋው ወደ እሳትም ወደ ውኃም ጣለው፤ ቢቻልህ ግን እዘንልን እርዳንም፡” አለው።

23ኢየሱስም፦ “ቢቻልህ ትላለህ፤ ለሚያምን ሁሉ ይቻላል፡” አለው።

24ወዲያውም የብላቴናው አባት ጮኾ፦ “አምናለሁ፤ አለማመኔን እርዳው” አለ።

25ኢየሱስም ሕዝቡ እንደ ገና ሲራወጥ አይቶ ርኵሱን መንፈስ ገሠጸና፦ “አንተ ዲዳ ደንቆሮም መንፈስ፥ እኔ አዝሃለሁ፥ ከእርሱ ውጣ እንግዲህም አትግባበት፡” አለው።

26ጮኾም እጅግም አንፈራግጦት ወጣ፤ ብዙዎችም፦ “ሞተ” እስኪሉ ድረስ እንደ ሙት ሆነ።

27ኢየሱስ ግን እጁን ይዞ አስነሣው ቆመም።

28ወደ ቤትም ከገባ በኋላ ደቀ መዛሙርቱ፦ “እኛ ልናወጣው ያልቻልን ስለ ምንድር ነው?” ብለው ብቻውን ጠየቁት።

29“ይህ ወገን በጸሎትና በጦም ካልሆነ በምንም ሊወጣ አይችልም፡” አላቸው።

30ከዚያም ወጥተው በገሊላ በኩል አለፉ፤ ደቀ መዛሙርቱንም ያስተምር ስለ ነበር ማንም ያውቅ ዘንድ አልወደደም፤ ለእነርሱም፦ “የሰው ልጅ በሰዎች እጅ አልፎ ይሰጣል፥ ይገድሉትማል፥ ተገድሎም በሦስተኛው ቀን ይነሣል፡” ይላቸው ነበር።

32እነርሱም ነገሩን አላስተዋሉም፥ እንዳይጠይቁትም ፈሩ።

33ወደ ቅፍርናሆምም መጣ። በቤትም ሆኖ፦ “በመንገድ እርስ በርሳችሁ ምን ተነጋገራችሁ?” ብሎ ጠየቃቸው።

34እነርሱ ግን በመንገድ፦ “ከሁሉ የሚበልጥ ማን ይሆን?” ተባብለው ነበርና ዝም አሉ።

35ተቀምጦም አሥራ ሁለቱን ጠርቶ፦ “ሰው ፊተኛ ሊሆን ቢወድ ከሁሉ በኋላ የሁሉም አገልጋይ ይሁን” አላቸው።

36ሕፃንም ይዞ በመካከላቸው አቆመው፡ አቅፎም እንዲህ አላቸው፦

37“እንደዚህ ካሉ ሕፃናት አንዱን በስሜ የሚቀበል ሁሉ እኔን ይቀበላል፤ የሚቀበለኝም ሁሉ የላከኝን እንጂ እኔን አይቀበልም።”

38ዮሐንስ መልሶ፦ “መምህር ሆይ፥ አንድ ሰው በስምህ አጋንንትን ሲያወጣ አየነው፥ ስለማይከተለንም ከለከልነው” አለው።

39ኢየሱስ ግን አለ፦ “በስሜ ተአምር ሠርቶ በቶሎ በእኔ ላይ ክፉ መናገር የሚችል ማንም የለምና አትከልክሉት፤

40የማይቃወመን እርሱ ከእኛ ጋር ነውና።

41የክርስቶስ ስለ ሆናችሁ በስሜ ጽዋ ውኃ የሚያጠጣችሁ ሁሉ፥ ዋጋው እንዳይጠፋበት እውነት እላችኋለሁ።”

42“በእኔም ከሚያምኑት ከእነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን የሚያሰናክል ሁሉ ትልቅ የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ወደ ባሕር ቢጣል ይሻለው ነበር።

43እጅህ ብታሰናክልህ ቍረጣት፤ ሁለት እጅ ኖሮህ ትላቸው ወደማይሞትበት እሳቱም ወደማይጠፋበት ወደ ገሃነም ወደማይጠፋ እሳት ከመሄድ ጕንድሽ ሆነህ ወደ ሕይወት መግባት ይሻላል።

45“እግርህ ብታሰናክልህ ቍረጣት፤ ሁለት እግር ኖሮህ ትላቸው ወደማይሞትበት እሳቱም ወደማይጠፋበት ወደ ገሃነም ወደማይጠፋ እሳት ከመጣል አንካሳ ሆነህ ወደ ሕይወት መግባት ይሻልሃል።

47“ዓይንህ ብታሰናክልህ አውጣት፤ ሁለት ዓይን ኖሮህ ትላቸው ወደማይሞትበት እሳቱም ወደማይጠፋበት ወደ ገሃነመ እሳት ከመጣል አንዲት ዓይን ኖራህ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት ይሻልሃል።

49“ሰው ሁሉ በእሳት ይቀመማልና፥ መሥዋዕትም ሁሉ በጨው ይቀመማል።

50ጨው መልካም ነው፤ ጨው ግን አልጫ ቢሆን በምን ታጣፍጡታላችሁ? በነፍሳችሁ ጨው ይኑርባችሁ፥ እርስ በርሳችሁም ተስማሙ።”

ማብራሪያ

፱፥፩-፲፫ የክርስቶስ መንግሥት መቃረብን የሚያበስር ትንቢት እዚህ ቀርቧል። የዚያች መንግሥት ቅድመ እይታ በክርስቶስ መልክ መቀየር ተሰጥቷል። ከዓለም ተለይቶ ከክርስቶስ ጋር ብቻውን መሆን መልካም ነው። በሰማይ ከሁሉም ቅዱሳን ጋር ተከብሮ ከክርስቶስ ጋር መኖር ደግሞ እንዴት መልካም ነው! ነገር ግን እኛ መልካም በሆንንበት ጊዜ ለሌሎች ግድ አይሰጠንም፤ በደስታችን ሙላትም የወንድሞቻችንን ብዙ ፍላጎቶች እንረሳለን።

እግዚአብሔር ኢየሱስን የራሱ እንደሆነ አድርጎ ያውቀዋል፤ እንደ ተወዳጅ ልጁም ይቀበለዋል፤ በእርሱም እኛን ለመቀበል ዝግጁ ነው። ስለዚህ እኛም እርሱን እንደ ተወዳጅ አዳኛችን ልናውቀውና ልንቀበለው ይገባል፤ በእርሱም ለመገዛት ራሳችንን አሳልፈን ልንሰጥ ይገባል። ክርስቶስ ደስታና ማጽናናት በሚለዩአት ጊዜ ነፍስን አይተዋትም። ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ ስለ ኤልያስ የተነገረውን ትንቢት ገለጸላቸው። ይህ የዮሐንስ መጥምቅ ለደረሰበት ክፉ አያያዝ በጣም ይስማማ ነበር።

9:14-29 የሚሰቃየው ወጣት አባት የደቀ መዛሙርቱን የኃይል ማጣት አሰላሰለ፤ ክርስቶስ ግን ያልተሳካለትን ነገር ከእምነት ማጣት ጋር እንዲያያይዘው ይሻል። ለማመናችን እጅግ ብዙ ቃል ተገብቶለታል። ልታምን ከቻልክ፣ የጠነከረ ልብህ ሊለዝብ ይችላል፣ መንፈሳዊ በሽታዎችህ ሊፈወሱ ይችላሉ፤ ደካማ ብትሆንም እስከ መጨረሻው መጽናት ትችላለህ። ስለ እምነት ማጣት የሚያማርሩ ሰዎች፣ አለማመንን ለማሸነፍ የሚያግዛቸውን ጸጋ ለማግኘት ወደ ክርስቶስ መመልከት አለባቸው፣ ጸጋውም ለእነርሱ በቂ ይሆናል። ክርስቶስ የፈወሰውን ሙሉ በሙሉ ይፈውሳል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV And he said to them, “I tell you the truth, some who are standing here will not taste death before they see the kingdom… English BCV ቀፂሉውን ኢየሱስ “ኣብዙይ ቆይሞም ካብ ዘለዉ፥ ንመንግስቲ እግዚኣብሄር ብሓይሊ ኽትመፅእ እንተላ ኽሳዕ ዝሪእዋ፥ ዘይሞቱ ኸም ዘለዉ፥ ብሓቂ እብለኩም ኣለኹ” በሎም። ትግርኛ GAZBIB Kana booddee Yesus, ?Dhuguma, dhuguman isinitti hima, namoota as dhaabatanii jiran keessaa, kaan utuu hin du'in, mootum… Afaan Oromoo BCV GIZ ወይቤሎሙ፦ “አማን እብለክሙ ሀለዉ እምእለ ይቀውሙ ዝየ እለ ኢይጥዕምዎ ለሞት እስከ ይሬእይዋ ለመንግሥተ እግዚአብሔር እንዘ ትመጽእ በኀይል።” giz GAZGAZ Kana booddee Yesus, ?Dhuguma, dhuguman isinitti hima, namoota as dhaabatanii jiran keessaa, kaan utuu hin du'in, mootum… Afaan Oromoo BCV aksum ቀፂሉውን ኢየሱስ “ኣብዙይ ቆይሞም ካብ ዘለዉ፥ ንመንግስቲ እግዚኣብሄር ብሓይሊ ኽትመፅእ እንተላ ኽሳዕ ዝሪእዋ፥ ዘይሞቱ ኸም ዘለዉ፥ ብሓቂ እብለኩም ኣለኹ” በሎም። ትግርኛ AMHNIV ቀጥሎም፣ “እውነት እላችኋለሁ፤ እዚህ ከቆሙት መካከል የእግዚአብሔር መንግሥት በኀይል ስትመጣ እስከሚያዩ ድረስ ሞትን የማይቀምሱ አንዳንዶች አሉ” አላቸው። አማርኛ SWAHSUV Akawaambia, Amin, nawaambia, Pana watu katika hawa wasimamao hapa, ambao hawataonja mauti kabisa, hata watakapouona ufa… Kiswahili