ትንቢተ ሚክያስ 4

AMHNIVአማርኛ13 ጥቅሶች3:02 አዳምጥ
አዳምጥ 3:02 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1በመጨረሻው ዘመን፣ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ተራራ፣ ከተራሮች ልቆ ይታያል፤ ከኰረብቶች በላይ ከፍ ይላል፤ ሕዝቦችም ወደ እርሱ ይጐርፋሉ።

2ብዙ አሕዛብ መጥተው እንዲህ ይላሉ፤ “ኑ፤ ወደ እግዚአብሔር ተራራ፣ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንሂድ፤ በመንገዱ እንድንሄድ፣ መንገዱን ያስተምረናል።” ሕግ ከጽዮን ይመጣል፤ የእግዚአብሔርም ቃል ከኢየሩሳሌም።

3እርሱ በብዙ ሕዝብ መካከል ይፈርዳል፤ በሩቅና በቅርብ ባሉ ኀያላን መንግሥታት መካከል ያለውን ግጭት ያቆማል፤ ሰይፋቸውን ማረሻ፣ ጦራቸውንም ማጭድ ያደርጉታል። አንዱ መንግሥት በሌላው መንግሥት ላይ ሰይፍ አያነሣም፤ ከእንግዲህም የጦርነት ትምህርት አይማሩም።

4እያንዳንዱ ሰው በገዛ ወይኑ ሥር፣ ከገዛ በለሱም ሥር ይቀመጣል፤ የሚያስፈራቸው አይኖርም፤ የእግዚአብሔር ጸባኦት አፍ ተናግሮአልና።

5አሕዛብ ሁሉ፣ በአማልክቶቻቸው ስም ይሄዳሉ፤ እኛ ግን በአምላካችን በእግዚአብሔር ስም፣ ከዘላለም እስከ ዘላለም እንሄዳለን።

6እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “በዚያች ቀን ሽባውን እሰበስባለሁ፤ ስደተኞችንና ለሐዘን ያደረግኋቸውን፣ ወደ አንድ ቦታ አመጣለሁ።

7የሽባዎችን ትሩፍ፣ የተገፉትንም ብርቱ ሕዝብ አደርጋለሁ፤ ከዚያች ቀን አንሥቶ እስከ ዘላለም፣ እግዚአብሔር በጽዮን ተራራ በእነርሱ ላይ ይነግሣል።

8አንተ የመንጋው መጠበቂያ ማማ ሆይ፤ የጽዮን ሴት ልጅ ዐምባ ሆይ፤ የቀድሞው ግዛትህ ይመለስልሃል፤ የመንግሥትም ሥልጣን ለኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ይሆናል።”

9አሁንስ እንደዚህ የምትጮኺው ለምንድን ነው? ንጉሥ የለሽምን? ምጥ እንደ ያዛት ሴት የተጨነቅሽው፣ መካሪሽ ስለ ጠፋ ነውን?

10የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ፤ ምጥ እንደ ያዛት ሴት ተጨነቂ፤ አሁንስ ከከተማ ወጥተሽ፣ በሜዳ ላይ መስፈር አለብሽና፤ ወደ ባቢሎን ትሄጃለሽ፣ በዚያ ከጠላት እጅ ትድኛለሽ፤ እግዚአብሔር በዚያ፣ ከጠላቶችሽ ይታደግሻል።

11አሁን ግን ብዙ አሕዛብ፣ በአንቺ ላይ ተሰብስበዋል፤ እነርሱም፣ “የረከሰች ትሁን፤ ዐይናችንም ጽዮንን መዘባበቻ አድርጎ ይያት” ይላሉ።

12ነገር ግን የእግዚአብሔርን ሐሳብ አያውቁም፤ በአውድማ ላይ እንደ ነዶ የሚሰበስባቸውን፣ የእርሱን ዕቅድ አያስተውሉም።

13የጽዮን ልጅ ሆይ፤ ተነሥተሽ አበራዪ፤ የብረት ቀንድ እሰጥሻለሁና፤ የናስ ሰኰና እሰጥሻለሁ፤ አሕዛብንም ታደቂያቸዋለሽ።” በግፍ ያግበሰበሱትን ትርፍ ለእግዚአብሔር፣ ሀብታቸውንም ለምድር ሁሉ ጌታ ታቀርቢያለሽ።

ማብራሪያ

ሚክያስ 4:1-8

አሕዛብ እስካሁን ድረስ ሰይፎቻቸውን ማረሻ አድርገው ለመቅረጽ የሚያስችል ያህል ለሰላም አለቃ አልተገዙም፤ ጦርነትም አላቆመም። እነዚህ ግን የወንጌል ቤተ ክርስቲያንን የሚመለከቱ እጅግ ውድ የሆኑ ተስፋዎች ናቸው፤ ቃል የገባ እርሱ የታመነ ነውና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየበለጠ ይፈጸማሉ። በመጨረሻው ዘመን፣ በመሲሑ ዘመን፣ በእግዚአብሔር ዘንድ ክብር ያላት ቤተ ክርስቲያን በዓለም ውስጥ ትመሠረታለች። ክርስቶስ ራሱ በዐለት ላይ ይገነባታልና። አሕዛብ ጣዖቶቻቸውን ያመልኩ ነበር፤ ነገር ግን በተነገረው ዘመን ሕዝቡ በሙሉ ልብ ከጌታ ጋር ይጣበቃል፣ ፈቃዱንም በማድረግ ይደሰታል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG በመጨረሻውም ዘመን የእግዚአብሔር ቤት ተራራ በተራሮች ራስ ላይ ጸንቶ ይቆማል፥ ከኮረብቶችም በላይ ከፍ ከፍ ይላል፤ አሕዛብም ወደ እርሱ ይጐርፋሉ። አማርኛ ENGNIV In the last days the mountain of the Lord's temple will be established as chief among the mountains; it will be raised … English BCV በቲ ዳሕረዋይ ዘመን፥ እቲ እምባ ቤት እግዚኣብሄር፥ ኣብ ርእሲ እምባታት ፀኒዑ ኽቐውም እዩ፤ ኣብ ልዕሊ ዀረብታታትውን ልዕል ልዕል ክብል እዩ፤ ህዝብታት ድማ ናብኡ ኽውሕዙ እዮም። ትግርኛ GAZBIB Bara booddeetti tulluun manni Waaqayyoo irra jiru, tulloota hundumaa keessaa akka isa caaluutti jabaatee in dhaabata; g… Afaan Oromoo BCV GIZ ወይከውን በደኃሪ መዋዕል ያስቲርኢ ደብረ እግዚአብሔር ድልወ ውስተ አርእስተ አድባር ወይትሌዐል መልዕልተ አውግር፤ ወይረውጹ ኀቤሁ ብዙኃን አሕዛብ። giz GAZGAZ Bara booddeetti tulluun manni Waaqayyoo irra jiru, tulloota hundumaa keessaa akka isa caaluutti jabaatee in dhaabata; g… Afaan Oromoo BCV aksum በቲ ዳሕረዋይ ዘመን፥ እቲ እምባ ቤት እግዚኣብሄር፥ ኣብ ርእሲ እምባታት ፀኒዑ ኽቐውም እዩ፤ ኣብ ልዕሊ ዀረብታታትውን ልዕል ልዕል ክብል እዩ፤ ህዝብታት ድማ ናብኡ ኽውሕዙ እዮም። ትግርኛ SWAHSUV Lakini itakuwa katika siku za mwisho, ya kwamba mlima wa nyumba ya Bwana utawekwa imara juu ya milima, nao utainuliwa j… Kiswahili