ትንቢተ ሚክያስ 2

AMHNIVአማርኛ13 ጥቅሶች2:45 አዳምጥ
አዳምጥ 2:45 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ክፉ ለመሥራት ለሚያቅዱ፣ በመኝታቸው ሳሉ ተንኰል ለሚያውጠነጥኑ ወዮላቸው! ሲነጋ በማለዳ ይፈጽሙታል፤ የሚያደርጉበት ኀይል በእጃቸው ነውና።

2ዕርሻ ይመኛሉ፤ ይይዙታልም፤ ቤት ይመኛሉ፤ ይወስዱታልም፤ የሰውን ቤት፣ የባልንጀራን ርስት አታልለው ይወስዳሉ።

3ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እነሆ፤ በዚያ ሕዝብ ላይ ጥፋት ላመጣ ዐቅጃለሁ፤ ከዚህም ለማምለጥ አትችሉም። ከእንግዲህ በትዕቢት አትመላለሱም፤ የመከራ ጊዜ ይሆናልና።

4በዚያ ቀን ሰዎች ይሣለቁባችኋል፤ በሐዘን እንጒርጒሮ እንዲህ እያሉ ያፌዙባችኋል፤ ‘እኛ ፈጽሞ ጠፍተናል፤ የወገኔ ርስት ተከፋፍሎአል። ከእኔ ነጥቆ ወስዶ፣ ዕርሻዎቻችንን ላሸነፉን አከፋፈለ።’

5ስለዚህ በእግዚአብሔር ጉባኤ ውስጥ፣ መሬት በዕጣ የሚያካፍል ማንም አይኖርም።

6ነቢያቶቻቸው፣ “ትንቢት አትናገርብን፤ ስለ እነዚህ ነገሮች ትንቢት አትናገር፤ ውርደት አይደርስብንም” ይላሉ።

7የያዕቆብ ቤት ሆይ፤ እንዲህ ሊባል ይገባልን? “የእግዚአብሔር መንፈስ የማይታገሥ ነውን? እንዲህ ያሉት ነገሮችንስ ያደርጋልን?” “መንገዱ ቀና ለሆነ፣ ቃሌ መልካም አያደርግምን?

8በመጨረሻ በሕዝቤ ላይ ጠላት ሆናችሁ ተነሣችሁ፤ የጦርነት ሐሳብ ሳይኖራቸው፣ በሰላም ከሚያልፉ ሰዎች ላይ፣ ማለፊያ መጐናጸፊያ ገፈፋችሁ።

9ከሚወዱት ቤታቸው፣ የሕዝቤን ሴቶች አስወጣችኋቸው፤ ክብሬን ከልጆቻቸው፣ ለዘላለም ወሰዳችሁ።

10ተነሡና፤ ከዚያ ሂዱ፤ ይህ ማረፊያ ቦታችሁ አይደለምና፤ ምክንያቱም ረክሶአል፤ ክፉኛም ተበላሽቶአል።

11ሐሰተኛና አታላይ ሰው መጥቶ፣ ‘ስለ ብዙ የወይን ጠጅና ስለሚያሰክር መጠጥ ትንቢት እነግራችኋለሁ’ ቢል፣ ለዚህ ሕዝብ ተቀባይነት ያለው ነቢይ ይሆናል።

12“ያዕቆብ ሆይ፤ በእርግጥ ሁላችሁንም እሰበስባለሁ፤ የእስራኤልንም ትሩፍ በአንድነት አመጣለሁ፤ በጒረኖ ውስጥ እንዳሉ በጎች በመሰማሪያ ላይ እንዳለ መንጋ በአንድነት እሰበስባቸዋለሁ፤ ቦታውም በሕዝብ ይሞላል።

13የሚሰብረው ወጥቶ በፊታቸው ይሄዳል፤ እነርሱም በሩን በመስበር ወጥተው ይሄዳሉ፤ እግዚአብሔር እየመራቸው፣ ንጉሣቸው ቀድሞአቸው ይሄዳል።

ማብራሪያ

ምዕራፍ 2:1-5 በሌሊት ክፋትን ለሚያስቡና በማለዳም ወደ ተግባር ለማዋል ለሚነሡ ሰዎች ወዮላቸው! ክፋትን በድንገተኛ ሐሳብ መፈጸም መጥፎ ነው፤ ነገር ግን በዕቅድና በቅድሚያ በማሰብ ማድረግ ደግሞ እጅግ የከፋ ነው። የብቸኝነትና የእረፍት ጊዜያትን በአግባቡ መጠቀም ትልቅ ፋይዳ አለው። በልብ ውስጥ ስግብግብነት የሚነግሥ ከሆነ ምሕረት ይባረራል፤ ልብ በዚህ ሲጠመድም ዓመፅና ማታለል በተለምዶ እጅን ይቆጣጠራሉ። በብልጽግና ውስጥ እጅግ ትዕቢተኞችና ደኅና ነን ብለው የሚታበዩት ሰዎች፣ በችግር ጊዜ ደግሞ ተስፋ ለመቁረጥ እጅግ ፈጣኖች ናቸው። እግዚአብሔር ፊቱን ከሚያዞርባቸው ሰዎች ወዮላቸው! ከጌታ ጉባኤ የሚያርቁን ወይም ከጥቅሞቹ/ከበረከቶቹ ሙሉ በሙሉ እንዳንጠቀም የሚያደርጉን እነዚህ እጅግ ከባድ መከራዎች ናቸው።

2:6-11 ‹ትንቢት አትናገሩ› ስለሚሉ፣ እግዚአብሔርም ቃላቸውን ተቀብሎ ኃጢአታቸው ቅጣታቸው ይሆናል። የማይድን በሽተኛን ሐኪም ከእንግዲህ አይጎብኘው።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6