የማቴዎስ ወንጌል 16

AMHEVGአማርኛ28 ጥቅሶች4:00 አዳምጥ
አዳምጥ 4:00 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያንም ቀርበው ሲፈትኑት ከሰማይ ምልክት እንዲያሳያቸው ለመኑት።

2እርሱ ግን መልሶ እንዲህ አላቸው፦ “በመሸ ጊዜ፦ ‘ሰማዩ ቀልቶአልና ብራ ይሆናል’ ትላላችሁ፤

3ማለዳም፦ ‘ሰማዩ ደምኖ ቀልቶአልና ዛሬ ይዘንባል’ ትላላችሁ። የሰማዩን ፊትማ መለየት ታውቃላችሁ፥ የዘመኑንስ ምልክት መለየት አትችሉምን?

4“ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይሻል፥ ከነቢዩም ከዮናስ ምልክት በቀር ምልክት አይሰጠውም።” ትቶአቸውም ሄደ።

5ደቀ መዛሙርቱም ወደ ማዶ በመጡ ጊዜ እንጀራ መያዝን ረሱ።

6ኢየሱስም፦ “ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን እርሾ ተጠንቀቁና ተጠበቁ” አላቸው።

7እነርሱም፦ “እንጀራ ባንይዝ ነው” ብለው እርስ በርሳቸው ተነጋገሩ።

8ኢየሱስም አውቆ እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ እምነት የጐደላችሁ፥ እንጀራ ስለ ሌላችሁ ስለ ምን እርስ በርሳችሁ ትነጋገራላችሁ?

9ገና አታስተውሉምን? ለአምስቱ ሺህ አምስቱ እንጀራ፥ ስንት መሶብም እንዳነሣችሁ ትዝ አይላችሁምን?

10ወይስ ለአራቱ ሺህ ሰባቱ እንጀራ፥ ስንት ቅርጫትም እንዳነሣችሁ ትዝ አይላችሁምን?

11‘ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን እርሾ እንድትጠበቁ’ ብዬ ስለ እንጀራ እንዳልተናገርኋችሁ እንዴት አታስተውሉምን?”

12እነርሱም ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን ትምህርት እንጂ ከእንጀራ እርሾ እንዲጠበቁ እንዳላላቸው ያን ጊዜ አስተዋሉ።

13ኢየሱስም ወደ ፊልጶስ ቂሣርያ አገር በደረሰ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን፦ “ሰዎች የሰውን ልጅ ማን እንደ ሆነ ይሉታል?” ብሎ ጠየቀ።

14እነርሱም፦ “አንዳንዱ መጥምቁ ዮሐንስ፥ ሌሎችም ኤልያስ፥ ሌሎችም ኤርምያስ ወይም ከነቢያት አንዱ ነው፥ ይላሉ” አሉት።

15እርሱም፦ “እናንተስ እኔን ማን እንደ ሆንሁ ትላላችሁ?” አላቸው።

16ስምዖን ጴጥሮስም መልሶ፦ “አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ፡” አለ።

17ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፦ “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና ብፁዕ ነህ።

18እኔም እልሃለሁ፥ አንተ ጴጥሮስ ነህ፥ በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም።

19የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፤ በምድር የምታስረው ሁሉ በሰማያት የታሰረ ይሆናል፥ በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል”።

20ያን ጊዜም እርሱ ክርስቶስ እንደ ሆነ ለማንም እንዳይነግሩ ደቀ መዛሙርቱን አዘዛቸው።

21ከዚያን ቀን ጀምሮ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ይሄድ ዘንድ ከሽማግሎችና ከካህናት አለቆች ከጻፎችም ብዙ መከራ ይቀበልና ይገደል ዘንድ በሦስተኛውም ቀን ይነሣ ዘንድ እንዲገባው ለደቀ መዛሙርቱ ይገልጥላቸው ጀመር።

22ጴጥሮስም ወደ እርሱ ወስዶ፦ “አይሁንብህ ጌታ ሆይ፤ ይህ ከቶ አይደርስብህም፡” ብሎ ሊገሥጸው ጀመረ።

23እርሱ ግን ዘወር ብሎ ጴጥሮስን፦ “ወደ ኋላዬ ሂድ፥ አንተ ሰይጣን፤ የሰውን እንጂ የእግዚአብሔርን አታስብምና ዕንቅፋት ሆነህብኛል፡” አለው።

24በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አለ፦ “እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ።

25ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ሁሉ ያጠፋታል፤ ስለ እኔ ግን ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ያገኛታል።

26ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል? ወይስ ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል?

27“የሰው ልጅ ከመላእክቱ ጋር በአባቱ ክብር ይመጣ ዘንድ አለውና፤ ያን ጊዜም ለሁሉ እንደ ሥራው ያስረክበዋል።

28እውነት እላችኋለሁ፥ የሰው ልጅ በመንግሥቱ ሲመጣ እስኪያዩ ድረስ እዚህ ከሚቆሙት ሞትን የማይቀምሱ አንዳንድ አሉ።”

ማብራሪያ

፲፮፥፩-፬ ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያን በመርሆዎቻቸውና በምግባራቸው እርስ በርሳቸው ተቃዋሚዎች ነበሩ፤ ሆኖም በክርስቶስ ላይ ተባበሩ። እነሱ ግን የራሳቸውን የመረጡትን ምልክት ፈለጉ፤ የታመሙትንና ኀዘንተኞችን ፍላጎት የሚያቃልሉትን ምልክቶች ንቀው፣ የትዕቢተኞችን የማወቅ ጉጉት የሚያረካ ሌላ ነገር ጠየቁ። የእግዚአብሔርን የተደነገጉ ምልክቶች እየናቅን፣ የራሳችንን የፈጠርናቸውን ምልክቶች መፈለግ ታላቅ ግብዝነት ነው።

16:5-12 ክርስቶስ ስለ መንፈሳዊ ነገሮች በምሳሌ ይናገራል፣ ደቀ መዛሙርቱም ሥጋዊ ነገሮችን በመገመት ተሳሳቱት። እነርሱ ስለ እንጀራ እንደሚያስቡት እርሱም እንደሚያስብ ማሰባቸው፣ የትምህርቱንም መንገድ እምብዛም አለማወቃቸው አሳዝኖታል። በዚያን ጊዜም ምን ማለቱ እንደሆነ ተረዱ። ክርስቶስ በልብ ውስጥ ባለው የጥበብ መንፈስ ያስተምራል፤ ይህም ማስተዋልን በቃሉ ውስጥ ላለው የመገለጥ መንፈስ ይከፍታል።

16:13-20 ጴጥሮስ፣ እርሱም ሆነ ወንድሞቹ፣ ጌታችን የተስፋው መሲሕ፣ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ መሆኑን እርግጠኞች እንደሆኑ ተናገረ። ይህም ኢየሱስ ከሰው በላይ እንደሆነ እንዳመኑ አሳየ። ጌታችንም ጴጥሮስን እንደተባረከ አወጀ፤ የእግዚአብሔር ትምህርት ከማያምኑት ወገኖቹ የተለየ ስላደረገው። ክርስቶስም እውነትን በመናገር ባለው ጽናት ወይም ጽኑነት ምክንያት ጴጥሮስ ብሎ እንደሰየመው ጨመረ። ዐለት ተብሎ የተተረጎመው ቃል ከጴጥሮስ የሚለው ቃል ጋር አንድ አይደለም፣ ነገር ግን ተመሳሳይ ትርጉም አለው። ክርስቶስ የጴጥሮስን ማንነት ዐለት ማለቱ ነው ብሎ ከማሰብ የበለጠ ስህተት ሊኖር አይችልም። ያለ ጥርጥር ክርስቶስ ራሱ ዐለቱ፣ የቤተ ክርስቲያን የተፈተነ መሠረት ነው፤ ሌላ መሠረት ለመጣል ለሚሞክርም ወዮለት! የጴጥሮስ መናዘዝ ከትምህርቱ አንጻር ይህ ዐለት ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ ካልሆነ፣ በእርሱ የሚያምኑት ከቤተ ክርስቲያን አይደሉም፤ ነገር ግን አታላዮችና የታለሉ ናቸው። ጌታችን ቀጥሎ ጴጥሮስ የሚጎናጸፈውን ሥልጣን አወጀ። እርሱ የወንድሞቹን ስም ይዞ ተናገረ፣ ይህ ደግሞ ለእርሱም ሆነ ለወንድሞቹ የሚመለከት ነበር።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6