የሉቃስ ወንጌል 17

AMHEVGአማርኛ37 ጥቅሶች4:34 አዳምጥ
አዳምጥ 4:34 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ለደቀ መዛሙርቱም እንዲህ አለ፦ “መሰናክል ግድ ሳይመጣ አይቀርም፥ ነገር ግን መሰናክሉን ለሚያመጣው ወዮለት፤

2ከእነዚህ ከታናናሾች አንዱን ከማሰናከል ይልቅ የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ወደ ባሕር ቢጣል ይጠቅመው ነበር።

3ለራሳችሁ ተጠንቀቁ። ወንድምህ ቢበድልህ ገሥጸው፥ ቢጸጸትም ይቅር በለው።

4በቀንም ሰባት ጊዜ እንኳ ቢበድልህ በቀንም ሰባት ጊዜ፦ ‘ተጸጸትሁ፥’ እያለ ወደ አንተ ቢመለስ፥ ይቅር በለው።”

5ሐዋርያትም ጌታን፦ “እምነት ጨምርልን” አሉት።

6ጌታም አለ፦ “የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያህል እምነት ቢኖራችሁ፥ ይህን ሾላ፦ ‘ተነቅለህ ወደ ባሕር ተተከል’ ብትሉት፥ ይታዘዝላችሁ ነበር።

7ከእናንተም የሚያርስ ወይም ከብትን የሚጠብቅ ባሪያ ያለው፥ ከእርሻ ሲመለስ፦ ‘ወዲያው ቅረብና በማዕድ ተቀመጥ’ የሚለው ማን ነው?

8‘የምበላውን እራቴን አሰናዳልኝ፥ እስክበላና እስክጠጣ ድረስ ታጥቀህ አገልግለኝ፥ በኋላም አንተ ብላና ጠጣ’ የሚለው አይደለምን?

9“ያንን ባሪያ ያዘዘውን ስላደረገ ያመሰግነዋልን?

10እንዲሁ እናንተ ደግሞ የታዘዛችሁትን ሁሉ ባደረጋችሁ ጊዜ፦ የማንጠቅም ባሪያዎች ነን፥ ልናደርገው የሚገባንን አድርገናል፡ በሉ።”

11ወደ ኢየሩሳሌምም ሲሄድ በገሊላና በሰማርያ መካከል አለፈ።

12ወደ አንዲት መንደርም ሲገባ በሩቅ የቆሙት አሥር ለምጻሞች ተገናኙት፤

13እነርሱም እየጮኹ፦ “ኢየሱስ ሆይ፥ አቤቱ፥ ማረን፡” አሉ።

14አይቶም፦ “ሂዱ፥ ራሳችሁን ለካህናት አሳዩ፡” አላቸው። እነሆም፥ ሲሄዱ ነጹ።

15ከእነርሱም አንዱ እንደ ተፈወሰ ባየ ጊዜ በታላቅ ድምፅ እግዚአብሔርን እያከበረ ተመለሰ፥

16እያመሰገነውም በእግሩ ፊት በግንባሩ ወደቀ፤ እርሱም ሳምራዊ ነበረ።

17ኢየሱስም መልሶ፦ “አሥሩ አልነጹምን? ዘጠኙስ ወዴት አሉ?

18ከዚህ ከልዩ ወገን በቀር እግዚአብሔርን ሊያከብሩ የተመለሱ አልተገኙም፡” አለ።

19እርሱንም፦ “ተነሣና ሂድ፤ እምነትህ አድኖሃል” አለው።

20ፈሪሳውያንም፦ “የእግዚአብሔር መንግሥት መቼ ትመጣለች፡” ብለው ቢጠይቁት፥ መልሶ፦ “የእግዚአብሔር መንግሥት በመጠባበቅ አትመጣም፤

21ደግሞም፦ ‘እንኋት በዚህ፡’ ወይም፦ ‘እንኋት በዚያ፡’ አይሉአትም። እነሆ፥ የእግዚአብሔር መንግሥት በመካከላችሁ ናትና፡” አላቸው።

22ለደቀ መዛሙርቱም እንዲህ አለ፦ “ከሰው ልጅ ቀኖች አንዱን ልታዩ የምትመኙበት ወራት ይመጣል፡ አታዩትምም።

23እነርሱም፦ ‘እነሆ በዚህ፥’ ወይም፦ ‘እነሆ በዚያ፡’ ይሉአችኋል፤ አትሂዱ፡ አትከተሉአቸውም።

24“መብረቅ በርቆ ከሰማይ በታች ካለ ከአንድ አገር ከሰማይ በታች ወዳለው ወደ ሌላ አገር እንደሚያበራ፥ የሰው ልጅ በቀኑ እንዲህ ይሆናል።

25አስቀድሞ ግን ብዙ መከራ እንዲቀበል ከዚህም ትውልድ እንዲጣል ይገባዋል።

26“በኖኅ ዘመንም እንደ ሆነ፥ በሰው ልጅ ዘመን ደግሞ እንዲሁ ይሆናል።

27ኖኅ ወደ መርከብ እስከ ገባበት ቀን ድረስ፥ ይበሉና ይጠጡ ያገቡና ይጋቡም ነበር፥ የጥፋት ውኃም መጣ ሁሉንም አጠፋ።

28“እንዲሁ በሎጥ ዘመን እንደ ሆነ፤ ይበሉ ይጠጡም ይገዙም ይሸጡም ይተክሉም ቤትም ይሠሩ ነበር፤

29ሎጥ ከሰዶም በወጣበት ቀን ግን ከሰማይ እሳትና ዲን ዘነበ ሁሉንም አጠፋ።

30“የሰው ልጅ በሚገለጥበት ቀን እንዲሁ ይሆናል።

31በዚያም ቀን በሰገነት ያለ በቤቱ ያለውን ዕቃ ሊወስድ አይውረድ፥ እንዲሁም በእርሻ ያለ ወደ ኋላው አይመለስ።

32የሎጥን ሚስት አስቡአት።

33“ነፍሱን ሊያድን የሚፈልግ ሁሉ ያጠፋታል፥ ነፍሱንም የሚያጠፋ ሁሉ በሕይወት ይጠብቃታል።

34እላችኋለሁ፥ በዚያች ሌሊት ሁለት ሰዎች በአንድ አልጋ ይሆናሉ፤ አንዱ ይወሰዳል ሁለተኛውም ይቀራል።

35ሁለት ሴቶች በአንድ ወፍጮ ይፈጫሉ፤ አንዲቱ ትወሰዳለች ሁለተኛይቱም ትቀራለች።

36ሁለት ሰዎች በእርሻ ይሆናሉ፤ አንዱ ይወሰዳል ሁለተኛውም ይቀራል።”

37መልሰውም፦ “ጌታ ሆይ፥ ወዴት ነው?” አሉት። እርሱም፦ “ሥጋ ወዳለበት በዚያ አሞራዎች ይሰበሰባሉ፡” አላቸው።

ማብራሪያ

፲፯:፩-፲ በደል በምንም መንገድ ቢመጣ የበደሉን አምጪዎች ጥፋት አያቀልም፤ በደሎች መምጣታቸውም ቅጣታቸውን አይቀንስም። በወንድሞቻችን ይቅርታ መንገድ ላይ የሚገጥሙንን ታላላቅ አስቸጋሪ ነገሮች እንድናልፍ የሚያስችለን በእግዚአብሔር ይቅር ባይ ምሕረት ላይ ያለ እምነት ነው። በእግዚአብሔር ዘንድ የማይቻል ነገር እንደሌለ ሁሉ፣ ለሚያምን ሁሉ ሁሉም ነገር ይቻላል። ጌታችን ደቀ መዛሙርቱን የጥልቅ ትሕትናን አስፈላጊነት አሳያቸው። ጌታ በየፍጥረቱ ሁሉ ላይ ማንም ሰው በሌላ ሰው ላይ ሊኖረው ከማይችለው በላይ የሆነ ባለቤትነት አለው፤ ለአገልግሎታቸው ዕዳ አይሆንበትም፣ ከእርሱም ምንም ዓይነት ምንዳ ሊከፈላቸው አይገባውም።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6