የሉቃስ ወንጌል 16

AMHNIVአማርኛ31 ጥቅሶች5:44 አዳምጥ
አዳምጥ 5:44 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አለ፤ “አንድ ሀብታም ሰው አንድ መጋቢ ነበረው፤ ይኸው መጋቢ የሀብታሙን ሰው ንብረት እንደሚያባክን ለዚሁ ሀብታም ሰው ወሬ ደረሰው።

2ስለዚህ አስጠራውና፣ ‘ይህ የምሰማብህ ምንድን ነው? ከእንግዲህ አንተ መጋቢ ልትሆነኝ ስለማትችል፣ የምታስተዳድረውን ንብረት መቈጣጠሪያ ሒሳብ አስረክበኝ’ አለው።

3“መጋቢውም በልቡ እንዲህ አለ፤ ‘ጌታዬ ከመጋቢነት ሊሽረኝ ነው፤ ለማረስ ጒልበት የለኝም፤ መለመን ደግሞ ዐፍራለሁ፤ ስለዚህ ምን ላድርግ?

4ከመጋቢነት የተሻርሁ እንደሆነ ሰዎች በቤታቸው እንዲቀበሉኝ የማደርገውን ዐውቃለሁ።’

5“ስለዚህ የጌታው ዕዳ ያለባቸውን ሰዎች እያንዳንዳቸውን ጠራ፤ የመጀመሪያውንም ሰው ‘የጌታዬ ዕዳ ምን ያህል አለብህ?’ አለው።

6“እርሱም፣ ‘አንድ መቶ ማድጋ ዘይት አለብኝ’ አለ። “መጋቢውም፣ ‘የውል ወረቀትህን እንካ፤ ቶሎ ተቀምጠህ “አምሳ ማድጋ” ብለህ ጻፍ’ አለው።

7“ከዚያም ሌላውን፣ ‘አንተስ ስንት አለብህ?’ አለው። “እርሱም፣ ‘አምሳ ዳውላ ስንዴ’ አለው። “መጋቢውም፣ ‘የብድር ደብዳቤህን እንካ፤ “አርባ ዳውላ” ብለህ ጻፍ’ አለው።

8“ጌታውም አጭበርባሪውን መጋቢ በብልኅነቱ አደነቀው፤ የዚህ ዓለም ልጆች ከመሰሎቻቸው ጋር በሚኖራቸው ግንኙነት ከብርሃን ልጆች ይልቅ ብልኆች ናቸውና።

9ስለዚህ እላችኋለሁ፤ የዚህ ዓለም ገንዘብ ባለቀ ጊዜ በዘላለም ቤት ተቀባይነት እንዲኖራችሁ፣ በዚሁ ገንዘብ ወዳጆችን ለራሳችሁ አፍሩበት።

10“በትንሽ ነገር ታማኝ የሆነ በትልቁም ይታመናል፤ በትንሽ ነገር ያልታመነ በትልቁም አይታመንም።

11እንግዲህ፣ በዚህ ዓለም ሀብት ካልታመናችሁ፣ እውነተኛው ንማ ሀብት ማን ዐደራ ብሎ ይሰጣችኋል?

12በሌላው ሰው ሀብት ካልታመናችሁ፣ የራሳችሁ የሆነውን ሀብት ማን ይሰጣችኋል?

13“በአንድ ጊዜ ሁለት ጌቶችን ማገልገል የሚችል ማንም ባሪያ የለም፤ አንዱን ጠልቶ ሌላውን ይወዳል፤ ወይም አንዱን ይጠጋል፤ ሌላውን ይንቃል። የእግዚአብሔርም የገንዘብም ባሪያ መሆን አትችሉም።”

14ገንዘብ የሚወዱ ፈሪሳውያን ይህን ሁሉ ሰምተው በኢየሱስ አፌዙበት።

15እርሱም እንዲህ አላቸው፤ “እናንተ በሰዎች ፊት ራሳችሁን የምታጸድቁ ናችሁ፤ እግዚአብሔር ግን ልባችሁን ያውቃል፤ በሰዎች ዘንድ የከበረ፣ በእግዚአብሔር ፊት የረከሰ ነውና።

16“ሕግና ነቢያት እስከ ዮሐንስ ድረስ ሲነገሩ ኖረዋል፤ ከዚያ በኋላ ግን የእግዚአብሔር መንግሥት የምሥራች ተሰብኮአል፤ ሰውም ሁሉ ወደዚያ ለመግባት ይሻማል።

17ነገር ግን ከሕግ አንዲት ነጥብ ከምትወድቅ ሰማይና ምድር ቢያልፍ ይቀላል።

18“ሚስቱን ፈቶ ሌላይቱን የሚያገባ ሁሉ ያመነዝራል፤ ከባሏ የተፋታችውንም ሴት የሚያገባ ያመነዝራል።”

19ደግሞም ኢየሱስ እንዲህ አለ፤ “ሐምራዊና ቀጭን በፍታ የለበሰ፣ በየቀኑም በተድላ ደስታ የሚኖር አንድ ሀብታም ሰው ነበረ።

20በአንጻሩም፣ መላ ሰውነቱ በቊስል የተወረረ አንድ አልዓዛር የሚባል ድኻ በዚህ ሀብታም ሰው ደጃፍ ይተኛ ነበር፤

21ከሀብታሙ ሰው ማእድ የወደቀውን ፍርፋሪ እንኳ ሊመገብ ይመኝ ነበር፤ ውሾችም ሳይቀሩ መጥተው ቊስሉን ይልሱ ነበር።

22“ይህም ድኻ ሞተ፤ መላእክትም ወደ አብርሃም ዕቅፍ ወሰዱት። ሀብታሙም ሰው ደግሞ ሞቶ ተቀበረ።

23በሲኦልም እየተሠቃየ ሳለ ቀና ብሎ ከሩቅ አብርሃምን አየ፤ አልዓዛርንም በዕቅፉ ይዞት አየ።

24እርሱም፣ ‘አብርሃም አባት ሆይ፤ ራራልኝ፤ በዚህ ነበልባል እየተሠቃየሁ ስለ ሆነ፣ አልዓዛር የጣቱን ጫፍ ውሃ ነክሮ ምላሴን እንዲያቀዘቅዝልኝ እባክህ ላክልኝ’ እያለ ጮኸ።

25“አብርሃም ግን እንዲህ አለው፤ ‘ልጄ ሆይ፤ አንተ በምድራዊ ሕይወትህ ዘመን መልካም ነገሮችን እንደ ተቀበልህ፣ አልዓዛርም ደግሞ ክፉ ነገሮችን እንደ ተቀበለ አስታውስ፤ አሁን ግን እርሱ እዚህ ሲጽናና፣ አንተ በሥቃይ ላይ ትገኛለህ።

26ከሁሉም በላይ ከዚህ ወደ እናንተ ለማለፍ የሚፈልጉ እንደማይችሉ፣ እዚያ ያሉትም ደግሞ ወደ እኛ እንዳይሻገሩ፣ በእኛና በእናንተ መካከል ትልቅ ገደል ተደርጎአል።”

27“እርሱም እንዲህ አለ፤ ‘አባት ሆይ፤ እንግዲያውስ አልዓዛርን ወደ አባቴ ቤት እንድትሰደው እለምንሃለሁ፤

28አምስት ወንድሞች ስላሉኝ፣ እነርሱም ወደዚህ የሥቃይ ስፍራ እንዳይመጡ ያስጠንቅቃቸው።’

29“አብርሃም ግን፣ ‘ሙሴና ነቢያት አሏቸው፤ እነርሱን ይስሙ’ አለው።

30“እርሱም፣ ‘አብርሃም አባት ሆይ፤ እንደዚህ አይደለም፤ አንድ ሰው ከሙታን ተነሥቶ ቢሄድላቸው ንስሓ ይገባሉ’ አለ።

31አብርሃምም፣ ‘ሙሴንና ነቢያትን የማይሰሙ ከሆነ፣ አንድ ሰው ከሙታን ቢነሣ እንኳ አያምኑም’ አለው።

ማብራሪያ

16:1-12 ያለን ሁሉ የእግዚአብሔር ንብረት ነው። እኛ የምንጠቀመው ብቻ ሲሆን፣ ይህም በታላቁ ጌታችን መመሪያ መሰረት እና ለክብሩ መሆን አለበት። ይህ መጋቢ የጌታውን ንብረት በከንቱ አጠፋ። ሁላችንም እንደዚሁ ነን፤ እግዚአብሔር በአደራ የሰጠንን በአግባቡ አላበዛነውም። መጋቢው ሊክደው አይችልም፤ ሂሳቡን አቅርቦ መሄድ አለበት። ይህ ደግሞ ሞት እንደሚመጣና አሁን ያለንን እድሎች እንደሚያሳጣን ሊያስተምረን ይችላል። መጋቢው ለጌታው ያለባቸውን ዕዳ ከፍተኛውን ክፍል በመቀነስ፣ የጌታውን ዕዳተኞች ወይም ተከራዮች ወዳጆቹ ያደርጋል። በዚህ ምሳሌ የተጠቀሰው ጌታ የመጋቢውን ማታለል ሳይሆን ጥበብ አደነቀ። በዚህ ረገድ ብቻ ነው የተጠቀሰው። የዚህ ዓለም ሰዎች ግባቸውን በመምረጥ ረገድ ሞኞች ናቸው፤ ነገር ግን በድርጊታቸውና በትጋታቸው ብዙውን ጊዜ ከምእመናን የበለጠ ጠቢባን ናቸው። ዓመፀኛው መጋቢ ጌታውን በማታለል እንደ ምሳሌ አልተቀመጠም፣ ወይም ማንኛውንም ታማኝነት የጎደለውን ድርጊት ለማጽደቅ አይደለም፤ ነገር ግን የዚህ ዓለም ሰዎችን ጥንቃቄ የተሞላበት አካሄድ ለማመልከት ነው። የብርሃን ልጆች ከዚህ ዓለም ሰዎች ጥበብን ቢማሩና የተሻለ ግባቸውን እንደዚያው በብርቱ ቢከታተሉ መልካም ነው። እውነተኛው ሀብት መንፈሳዊ በረከቶችን ያመለክታል። አንድ ሰው እግዚአብሔር በአደራ የሰጠውን (ውጫዊ ነገሮችን) በራሱ ላይ ብቻ የሚያጠፋ ወይም የሚያከማች ከሆነ፣ በክርስቶስ በኩል የእግዚአብሔር ወራሽ መሆኑን ምን ማስረጃ ሊኖረው ይችላል? የዚህ ዓለም ሀብት አታላይና ያልተረጋገጠ ነው። በእምነት የበለጸጉ፣ በእግዚአብሔር ዘንድ ሀብታም የሆኑ፣ በክርስቶስና በተስፋ ቃላት ሀብታም የሆኑ ሰዎች እውነተኛ ባለጸጋዎችና እጅግ ሀብታም እንደሆኑ እንመን። እንግዲህ ሀብታችንን በሰማይ እናከማች፣ ክፍላችንንም ከዚያ እንጠብቅ።

፲፮፥፲፫-፲፰

ለዚህ ምሳሌ ጌታችን ከባድ ማስጠንቀቂያ አክሎበታል። እግዚአብሔርንና ዓለምን ማገልገል አትችሉም፤ ምክንያቱም የሁለቱ ፍላጎቶች እርስ በእርሳቸው የተነጣጠሉ ናቸውና። ጌታችን እንዲህ ሲናገር፣ ስግብግቡ ፈሪሳውያን ትምህርቶቹን በንቀት ተመለከቱት። እርሱ ግን ያስጠነቀቃቸው፣ ሕግ ነው ብለው የያዙት የሕጉን ትርጉም ማጣመም እንደሆነ ነበር፤ ይህንንም ጌታችን በፍቺ ጉዳይ አሳይቷል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG ደግሞም ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አለ፦ “መጋቢ የነበረው አንድ ባለ ጠጋ ሰው ነበረ፥ በእርሱ ዘንድ፦ ‘ይህ ሰው ያለህን ይበትናል፡’ ብለው ከሰሱት። አማርኛ ENGNIV Jesus told his disciples: “There was a rich man whose manager was accused of wasting his possessions. English BCV ኢየሱስ መሊሱ ንደቀ መዛሙርቱ ኸምዙይ በሎም፦ “መጋቢ ዝነበሮ፥ ሓደ ሃብታም ሰብኣይ ነበረ። ንእኡ ኸዓ ገንዘብካ ይብትነልካ ኣሎ፤ እናበሉ ነገርዎ። ትግርኛ GAZBIB Yesus bartoota isaatiin immoo, ?Namni sooressi tokko, qabeenya mana isaa hundumaa irratti kan gaafatamuuf, hojii adeems… Afaan Oromoo BCV GIZ ወይቤሎሙ እግዚእ ኢየሱስ ለአርዳኢሁ፦ “አሐዱ ብእሲ ባዕል ቦቱ መጋቢ ወአስተዋደይዎ ኀቤሁ ከመ ዘይዘሩ ሎቱ ንዋዮ። giz GAZGAZ Yesus bartoota isaatiin immoo, ?Namni sooressi tokko, qabeenya mana isaa hundumaa irratti kan gaafatamuuf, hojii adeems… Afaan Oromoo BCV aksum ኢየሱስ መሊሱ ንደቀ መዛሙርቱ ኸምዙይ በሎም፦ “መጋቢ ዝነበሮ፥ ሓደ ሃብታም ሰብኣይ ነበረ። ንእኡ ኸዓ ገንዘብካ ይብትነልካ ኣሎ፤ እናበሉ ነገርዎ። ትግርኛ SWAHSUV Tena, aliwaambia wanafunzi wake, Palikuwa na mtu mmoja, tajiri, aliyekuwa na wakili wake; huyu alishitakiwa kwake kuwa … Kiswahili