የሉቃስ ወንጌል 16

AMHEVGአማርኛ31 ጥቅሶች4:30 አዳምጥ
አዳምጥ 4:30 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ደግሞም ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አለ፦ “መጋቢ የነበረው አንድ ባለ ጠጋ ሰው ነበረ፥ በእርሱ ዘንድ፦ ‘ይህ ሰው ያለህን ይበትናል፡’ ብለው ከሰሱት።

2ጠርቶም፦ ‘ይህ የምሰማብህ ምንድር ነው? ወደ ፊት ለእኔ መጋቢ ልትሆን አትችልምና የመጋቢነትህን ሂሳብ አስረክበኝ’ አለው።

3“መጋቢውም በልቡ፦ ‘ጌታዬ መጋቢነቱን ከእኔ ይወስዳልና ምን ላድርግ? ለመቈፈር ኃይል የለኝም፥ መለመንም አፍራለሁ።

4ከመጋቢነቱ ብሻር በቤታቸው እንዲቀበሉኝ የማደርገውን አውቃለሁ፡’ አለ።

5“የጌታውንም ባለ ዕዳዎች እያንዳንዳቸውን ጠርቶ የፊተኛውን፦ ‘ለጌታዬ ምን ያህል ዕዳ አለብህ?’ አለው።

6እርሱም፦ ‘መቶ ማድጋ ዘይት’ አለ። ‘ደብዳቤህን እንካ ፈጥነህም ተቀምጠህ አምሳ ብለህ ጻፍ’ አለው።

7በኋላም ሌላውን፦ ‘አንተስ ስንት ዕዳ አለብህ?’ አለው። እርሱም፦ ‘መቶ ጫን ስንዴ’ አለ። ‘ደብዳቤህን እንካ ሰማንያ ብለህም ጻፍ’ አለው።

8“ጌታውም ዓመፀኛውን መጋቢ በልባምነት ስላደረገ አመሰገነው የዚህ ዓለም ልጆች ለትውልዳቸው ከብርሃን ልጆች ይልቅ ልባሞች ናቸውና።

9እኔም እላችኋለሁ፥ የዓመፃ ገንዘብ ሲያልቅ በዘላለም ቤቶች እንዲቀበሉአችሁ፥ በእርሱ ወዳጆችን ለራሳችሁ አድርጉ።

10ከሁሉ በሚያንስ የታመነ በብዙ ደግሞ የታመነ ነው፥ ከሁሉ በሚያንስም የሚያምፅ በብዙ ደግሞ ዓመፀኛ ነው።

11“እንግዲያስ በዓመፃ ገንዘብ ካልታመናችሁ፥ እውነተኛውን ገንዘብ ማን አደራ ይሰጣችኋል?

12በሌላ ሰው ገንዘብ ካልታመናችሁ፥ የእናንተን ማን ይሰጣችኋል?

13“ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ባርያ ማንም የለም፤ ወይም አንዱን ይጠላልና ሁለተኛውንም ይወዳል፥ ወይም ወደ አንዱ ይጠጋል ሁለተኛውንም ይንቃል። ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም።”

14ገንዘብንም የሚወዱ ፈሪሳውያን ይህን ሁሉ ሰምተው ያፌዙበት ነበር።

15እንዲህም አላቸው፦ “ራሳችሁን በሰው ፊት የምታጸድቁ እናንተ ናችሁ፥ ነገር ግን እግዚአብሔር ልባችሁን ያውቃል፤ በሰው ዘንድ የከበረ በእግዚአብሔር ፊት ርኵሰት ነውና።

16ሕግና ነቢያት እስከ ዮሐንስ ነበሩ፤ ከዚያ ጀምሮ የእግዚአብሔር መንግሥት ይሰበካል፤ ሁሉም ወደ እርስዋ በኃይል ይገቡባታል።

17ነገር ግን ከሕግ አንዲት ነጥብ ከምትወድቅ ሰማይና ምድር ሊያልፍ ይቀላል።

18ሚስቱንም የሚፈታ ሁሉ ሌላይቱንም የሚያገባ ያመነዝራል፥ ከባልዋም የተፈታችውን የሚያገባ ያመነዝራል።”

19“ቀይ ልብስና ቀጭን የተልባ እግር የለበሰ አንድ ባለ ጠጋ ሰው ነበረ፥ ዕለት ዕለትም እየተመቸው በደስታ ይኖር ነበር።

20አልዓዛርም የሚባል አንድ ድሀ በቍስል ተወርሶ በደጁ ተኝቶ ነበር፥

21ከባለ ጠጋውም ማዕድ ከሚወድቀው ፍርፋሪ ሊጠግብ ይመኝ ነበር፤ ውሾች እንኳ መጥተው ቍስሎቹን ይልሱ ነበር።

22ድሀውም ሞተ፥ መላእክትም ወደ አብርሃም እቅፍ ወሰዱት፤ ባለ ጠጋው ደግሞ ሞተና ተቀበረ።

23“በሲኦልም በሥቃይ ሳለ አሻቅቦ አብርሃምን በሩቅ አየ፡ አልዓዛርንም በእቅፉ።

24እርሱም እየጮኸ፦ ‘አብርሃም አባት ሆይ፥ ማረኝ፥ በዚህ ነበልባል እሣቀያለሁና የጣቱን ጫፍ በውኃ ነክሮ መላሴን እንዲያበርድልኝ አልዓዛርን ስደድልኝ፡’ አለ።

25አብርሃም ግን፦ ‘ልጄ ሆይ፥ አንተ በሕይወትህ ሳለህ መልካም እንደ ተቀበልህ አስብ አልዓዛርም እንዲሁ ክፉ፤ አሁን ግን እርሱ በዚህ ይጽናናል አንተም ትሣቀያለህ።

26ከዚህም ሁሉ ጋር ከዚህ ወደ እናንተ ሊያልፉ የሚፈልጉ እንዳይችሉ፥ ወዲያ ያሉ ደግሞ ወደ እኛ እንዳይሻገሩ በእኛና በእናንተ መካከል ታላቅ ገደል ተደርጎአል፡’ አለ።

27“እርሱም፦ ‘እንኪያስ፥ አባት ሆይ፥ ወደ አባቴ ቤት እንድትሰደው እለምንሃለሁ፤ አምስት ወንድሞች አሉኝና፤

28እነርሱ ደግሞ ወደዚህ ሥቃይ ስፍራ እንዳይመጡ ይመስክርላቸው፡’ አለ።

29አብርሃም ግን፦ ‘ሙሴና ነቢያት አሉአቸው፤ እነርሱን ይስሙ’ አለው።

30“እርሱም፦ ‘አይደለም፥ አብርሃም አባት ሆይ፥ ነገር ግን ከሙታን አንዱ ቢሄድላቸው ንስሐ ይገባሉ’ አለ።

31‘ሙሴንና ነቢያትንም የማይሰሙ ከሆነ፥ ከሙታንም እንኳ አንድ ቢነሣ አያምኑም፡’ አለው።”

ማብራሪያ

16:1-12 ያለን ሁሉ የእግዚአብሔር ንብረት ነው። እኛ የምንጠቀመው ብቻ ሲሆን፣ ይህም በታላቁ ጌታችን መመሪያ መሰረት እና ለክብሩ መሆን አለበት። ይህ መጋቢ የጌታውን ንብረት በከንቱ አጠፋ። ሁላችንም እንደዚሁ ነን፤ እግዚአብሔር በአደራ የሰጠንን በአግባቡ አላበዛነውም። መጋቢው ሊክደው አይችልም፤ ሂሳቡን አቅርቦ መሄድ አለበት። ይህ ደግሞ ሞት እንደሚመጣና አሁን ያለንን እድሎች እንደሚያሳጣን ሊያስተምረን ይችላል። መጋቢው ለጌታው ያለባቸውን ዕዳ ከፍተኛውን ክፍል በመቀነስ፣ የጌታውን ዕዳተኞች ወይም ተከራዮች ወዳጆቹ ያደርጋል። በዚህ ምሳሌ የተጠቀሰው ጌታ የመጋቢውን ማታለል ሳይሆን ጥበብ አደነቀ። በዚህ ረገድ ብቻ ነው የተጠቀሰው። የዚህ ዓለም ሰዎች ግባቸውን በመምረጥ ረገድ ሞኞች ናቸው፤ ነገር ግን በድርጊታቸውና በትጋታቸው ብዙውን ጊዜ ከምእመናን የበለጠ ጠቢባን ናቸው። ዓመፀኛው መጋቢ ጌታውን በማታለል እንደ ምሳሌ አልተቀመጠም፣ ወይም ማንኛውንም ታማኝነት የጎደለውን ድርጊት ለማጽደቅ አይደለም፤ ነገር ግን የዚህ ዓለም ሰዎችን ጥንቃቄ የተሞላበት አካሄድ ለማመልከት ነው። የብርሃን ልጆች ከዚህ ዓለም ሰዎች ጥበብን ቢማሩና የተሻለ ግባቸውን እንደዚያው በብርቱ ቢከታተሉ መልካም ነው። እውነተኛው ሀብት መንፈሳዊ በረከቶችን ያመለክታል። አንድ ሰው እግዚአብሔር በአደራ የሰጠውን (ውጫዊ ነገሮችን) በራሱ ላይ ብቻ የሚያጠፋ ወይም የሚያከማች ከሆነ፣ በክርስቶስ በኩል የእግዚአብሔር ወራሽ መሆኑን ምን ማስረጃ ሊኖረው ይችላል? የዚህ ዓለም ሀብት አታላይና ያልተረጋገጠ ነው። በእምነት የበለጸጉ፣ በእግዚአብሔር ዘንድ ሀብታም የሆኑ፣ በክርስቶስና በተስፋ ቃላት ሀብታም የሆኑ ሰዎች እውነተኛ ባለጸጋዎችና እጅግ ሀብታም እንደሆኑ እንመን። እንግዲህ ሀብታችንን በሰማይ እናከማች፣ ክፍላችንንም ከዚያ እንጠብቅ።

፲፮፥፲፫-፲፰

ለዚህ ምሳሌ ጌታችን ከባድ ማስጠንቀቂያ አክሎበታል። እግዚአብሔርንና ዓለምን ማገልገል አትችሉም፤ ምክንያቱም የሁለቱ ፍላጎቶች እርስ በእርሳቸው የተነጣጠሉ ናቸውና። ጌታችን እንዲህ ሲናገር፣ ስግብግቡ ፈሪሳውያን ትምህርቶቹን በንቀት ተመለከቱት። እርሱ ግን ያስጠነቀቃቸው፣ ሕግ ነው ብለው የያዙት የሕጉን ትርጉም ማጣመም እንደሆነ ነበር፤ ይህንንም ጌታችን በፍቺ ጉዳይ አሳይቷል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV Jesus told his disciples: “There was a rich man whose manager was accused of wasting his possessions. English BCV ኢየሱስ መሊሱ ንደቀ መዛሙርቱ ኸምዙይ በሎም፦ “መጋቢ ዝነበሮ፥ ሓደ ሃብታም ሰብኣይ ነበረ። ንእኡ ኸዓ ገንዘብካ ይብትነልካ ኣሎ፤ እናበሉ ነገርዎ። ትግርኛ GAZBIB Yesus bartoota isaatiin immoo, ?Namni sooressi tokko, qabeenya mana isaa hundumaa irratti kan gaafatamuuf, hojii adeems… Afaan Oromoo BCV GIZ ወይቤሎሙ እግዚእ ኢየሱስ ለአርዳኢሁ፦ “አሐዱ ብእሲ ባዕል ቦቱ መጋቢ ወአስተዋደይዎ ኀቤሁ ከመ ዘይዘሩ ሎቱ ንዋዮ። giz GAZGAZ Yesus bartoota isaatiin immoo, ?Namni sooressi tokko, qabeenya mana isaa hundumaa irratti kan gaafatamuuf, hojii adeems… Afaan Oromoo BCV aksum ኢየሱስ መሊሱ ንደቀ መዛሙርቱ ኸምዙይ በሎም፦ “መጋቢ ዝነበሮ፥ ሓደ ሃብታም ሰብኣይ ነበረ። ንእኡ ኸዓ ገንዘብካ ይብትነልካ ኣሎ፤ እናበሉ ነገርዎ። ትግርኛ AMHNIV ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አለ፤ “አንድ ሀብታም ሰው አንድ መጋቢ ነበረው፤ ይኸው መጋቢ የሀብታሙን ሰው ንብረት እንደሚያባክን ለዚሁ ሀብታም ሰው ወሬ ደረሰው። አማርኛ SWAHSUV Tena, aliwaambia wanafunzi wake, Palikuwa na mtu mmoja, tajiri, aliyekuwa na wakili wake; huyu alishitakiwa kwake kuwa … Kiswahili