የሉቃስ ወንጌል 11

AMHEVGአማርኛ53 ጥቅሶች8:24 አዳምጥ
አዳምጥ 8:24 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1እርሱም በአንድ ስፍራ ይጸልይ ነበር፥ በጨረሰም ጊዜ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ፦ “ጌታ ሆይ፥ ዮሐንስ ደቀ መዛሙርቱን እንዳስተማረ እንጸልይ ዘንድ አስተምረን” አለው።

2አላቸውም፦ “ስትጸልዩ እንዲህ በሉ፦ ‘በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ፤ ስምህ ይቀደስ፤ መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን፤

3የዕለት እንጀራችንን ዕለት ዕለት ስጠን፤

4ኃጢአታችንንም ይቅር በለን፥ እኛ ደግሞ የበደሉንን ሁሉ ይቅር ብለናልና፤ ከክፉ አድነን እንጂ ወደ ፈተና አታግባን’።”

5እንዲህም አላቸው፦ “ከእናንተ ማናቸውም ወዳጅ ያለው፥ በእኩል ሌሊትስ ወደ እርሱ ሄዶ፦ ‘ወዳጄ ሆይ፥ ሦስት እንጀራ አበድረኝ፥

6አንድ ወዳጄ ከመንገድ ወደ እኔ መጥቶ የማቀርብለት የለኝምና’ ይላልን?

7“ያም ከውስጥ መልሶ፦ ‘አታድክመኝ፤ አሁን ደጁ ተቈልፎአል ልጆቼም ከእኔ ጋር በአልጋ ላይ አሉ፤ ተነሥቼ ልሰጥህ አልችልም፡’ ይላልን?

8“እላችኋለሁ፥ ወዳጅ ስለ ሆነ ተነሥቶ ባይሰጠው እንኳ፥ ስለ ንዝነዛው ተነስቶ የሚፈልገውን ሁሉ ይሰጠዋል።

9እኔም እላችኋለሁ፦ ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፍትላችሁማል።

10የሚለምን ሁሉ ይቀበላልና፥ የሚፈልግም ያገኛል፥ መዝጊያውንም ለሚያንኳኳው ይከፈትለታል።

11“አባት ከሆናችሁ ከእናንተ ከማንኛችሁም ልጁ እንጀራ ቢለምነው፥ እርሱም ድንጋይ ይሰጠዋልን? ዓሣ ደግሞ ቢለምነው በዓሣ ፋንታ እባብ ይሰጠዋልን?

12ወይስ እንቍላል ቢለምነው ጊንጥ ይሰጠዋልን?

13“እንኪያስ እናንተ ክፉዎች ስትሆኑ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠት ካወቃችሁ፥ በሰማይ ያለው አባት ለሚለምኑት እንዴት አብልጦ መንፈስ ቅዱስን ይሰጣቸው?”

14ዲዳውንም ጋኔን ያወጣ ነበር፤ ጋኔኑም ከወጣ በኋላ ዲዳው ተናገረ ሕዝቡም ተደነቁ፤

15ነገር ግን ከእነርሱ አንዳንዱ፦ “በብዔል ዜቡል በአጋንንት አለቃ አጋንንትን ያወጣል፡” አሉ።

16ሌሎችም ሲፈትኑት ከሰማይ ምልክት ከእርሱ ይፈልጉ ነበር።

17እርሱ ግን አሳባቸውን አውቆ እንዲህ አላቸው፦ “እርስ በርስዋ የምትለያይ መንግሥት ሁሉ ትጠፋለች፤ ቤትም በቤት ላይ ይወድቃል።

18እኔ አጋንንትን በብዔል ዜቡል እንዳወጣ ትላላችሁና ሰይጣን ደግሞ እርስ በርሱ ከተለያየ መንግሥቱ እንዴት ትቆማለች?

19እኔስ በብዔል ዜቡል አጋንንትን የማወጣ ከሆንሁ፥ ልጆቻችሁ በማን ያወጡአቸዋል? ስለዚህ እነርሱ ፈራጆች ይሆኑባችኋል።

20እኔ ግን በእግዚአብሔር ጣት አጋንንትን የማወጣ ከሆንሁ፥ እንግዲህ የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ እናንተ ደርሳለች።

21ኃይለኛ ሰው ጋሻና ጦር ይዞ የራሱን ግቢ ቢጠብቅ፥ ያለው ገንዘቡ በሰላም ይሆናል፤

22ከእርሱ ይልቅ የሚበረታ መጥቶ ሲያሸንፈው ግን፥ ታምኖበት የነበረውን ጋሻና ጦር ይወስድበታል ምርኮውንም ያካፍላል።

23ከእኔ ጋር ያልሆነ ይቃወመኛል፥ ከእኔ ጋርም የማያከማች ይበትናል።”

24“ርኵስ መንፈስ ከሰው በወጣ ጊዜ ዕረፍትን እየፈለገ ውኃ በሌለበት ቦታ ያልፋል፤ ባያገኝም፦ ‘ወደ ወጣሁበት ቤቴ እመለሳለሁ’ ይላል፤

25ሲመጣም ተጠርጎ አጊጦም ያገኘዋል።

26ከዚያ ወዲያ ይሄድና ከእርሱ የከፉትን ሌሎችን ሰባት አጋንንት ከእርሱ ጋር ይይዛል፥ ገብተውም በዚያ ይኖራሉ፤ ለዚያም ሰው ከፊተኛው ይልቅ የኋለኛው ይብስበታል።”

27ይህንም ሲናገር፥ ከሕዝቡ አንዲት ሴት ድምፅዋን ከፍ አድርጋ፦ “የተሸከመችህ ማኅፀንና የጠባሃቸው ጡቶች ብፁዓን ናቸው፡” አለችው።

28እርሱ ግን፦ አ“ዎን፥ ብፁዓንስ የእግዚአብሔርን ቃል ሰምተው የሚጠብቁት ናቸው፡” አለ።

29ብዙ ሕዝብም በተሰበሰቡ ጊዜ እንዲህ ይል ጀመር፦ “ይህ ትውልድ ክፉ ነው፤ ምልክት ይፈልጋል፥ ከነቢዩም ከዮናስ ምልክት በቀር ምልክት አይሰጠውም።

30ዮናስ ለነነዌ ሰዎች ምልክት እንደ ሆናቸው፥ እንዲሁ ደግሞ የሰው ልጅ ለዚህ ትውልድ ምልክት ይሆናል።

31ንግሥተ አዜብ በፍርድ ከዚህ ትውልድ ሰዎች ጋር ተነሥታ ትፈርድባቸዋለች፤ የሰሎሞንን ጥበብ ለመስማት ከምድር ዳር መጥታለችና፥ እነሆም፥ ከሰሎሞን የሚበልጥ ከዚህ አለ።

32የነነዌ ሰዎች በፍርድ ከዚህ ትውልድ ጋር ተነሥተው ይፈርዱበታል፤ በዮናስ ስብከት ንስሐ ገብተዋልና፥ እነሆም፥ ከዮናስ የሚበልጥ ከዚህ አለ።”

33“መብራትንም አብርቶ በስውር ወይም በእንቅብ በታች የሚያኖረው የለም፥ የሚገቡ ሰዎች ብርሃኑን እንዲያዩ በመቅረዝ ላይ ያኖረዋል እንጂ።

34የሰውነትህ መብራት ዓይንህ ናት። ዓይንህ ጤናማ በሆነች ጊዜ ሰውነትህ ሁሉ ደግሞ ብሩህ ይሆናል። ዓይንህ ታማሚ በሆነች ጊዜ ግን ሰውነትህ ደግሞ የጨለመ ይሆናል።

35እንግዲህ በአንተ ያለው ብርሃን ጨለማ እንዳይሆን ተመልከት።

36እንግዲህ ሰውነትህ ሁሉ የጨለማ ቍራጭ የሌለበት ብሩህ ቢሆን፥ መብራት በደመቀ ብርሃን እንደሚያበራልህ በጭራሽ ብሩህ ይሆናል።”

37ይህንንም ሲናገር አንድ ፈሪሳዊ ከእርሱ ጋር ምሳ ይበላ ዘንድ ለመነው ገብቶም ተቀመጠ።

38ከምሳም በፊት አስቀድሞ እንዳልታጠበ ባየው ጊዜ ፈሪሳዊው ተደነቀ።

39ጌታም እንዲህ አለው፦ “አሁን እናንተ ፈሪሳውያን የጽዋውንና የወጭቱን ውጭ ታጠራላችሁ፥ ውስጣችሁ ግን ቅሚያና ክፋት ሞልቶበታል።

40እናንት ደንቆሮዎች፥ የውጭውን የፈጠረ የውስጡን ደግሞ አልፈጠረምን?

41ነገር ግን በውስጥ ያለውን ምጽዋት አድርጋችሁ ስጡ፥ እነሆም፥ ሁሉ ንጹሕ ይሆንላችኋል።

42ነገር ግን እናንተ ፈሪሳውያን፥ ከአዝሙድና ከጤና አዳም ከአትክልትም ሁሉ አሥራት ስለምታወጡ፥ ፍርድንና እግዚአብሔርን መውደድ ስለምትተላለፉ፥ ወዮላችሁ፤ ነገር ግን ሌላውን ሳትተዉ ይህን ልታደርጉት ይገባችሁ ነበር።

43እናንተ ፈሪሳውያን፥ በምኵራብ የከበሬታ ወንበር በገበያም ሰላምታ ስለምትወዱ፥ ወዮላችሁ።

44እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ ሰዎች ሳያውቁ በላዩ የሚሄዱበት የተሰወረ መቃብር ስለምትመስሉ፥ ወዮላችሁ።”

45ከሕግ አዋቂዎችም አንዱ መልሶ፦ “መምህር ሆይ፥ ይህን ማለትህ እኛን ደግሞ መስደብህ ነው፡” አለው።

46እርሱም እንዲህ አለ፦ “እናንተ ደግሞ ሕግ አዋቂዎች፥ አስቸጋሪ ሸክም ለሰዎች ስለምታሸክሙ፥ ራሳችሁም በአንዲት ጣታችሁ ስንኳ ሸክሙን ስለማትነኩት፥ ወዮላችሁ።

47አባቶቻችሁ የገደሉአቸውን የነቢያትን መቃብር ስለምትሠሩ፥ ወዮላችሁ።

48እንግዲህ ለአባቶቻችሁ ሥራ ትመሰክራላችሁ ትስማማላችሁም፤ እነርሱ ገድለዋቸዋልና፥ እናንተም መቃብራቸውን ትሠራላችሁ።

49ስለዚህ ደግሞ የእግዚአብሔር ጥበብ እንዲህ አለች፦ ‘ወደ እነርሱ ነቢያትንና ሐዋርያትን እልካለሁ፥ ከእነርሱም ይገድላሉ ያሳድዱማል’፥

50ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የፈሰሰው የነቢያት ሁሉ ደም፥

51ከአቤል ደም ጀምሮ በመሠዊያውና በቤተ መቅደስ መካከል እስከ ጠፋው እስከ ዘካርያስ ደም ድረስ፥ ከዚህ ትውልድ እንዲፈለግ አዎን እላችኋለሁ፥ ከዚህ ትውልድ ይፈለጋል።

52እናንተ ሕግ አዋቂዎች፥ የእውቀትን መክፈቻ ስለ ወሰዳችሁ፥ ወዮላችሁ ራሳችሁ አልገባችሁም የሚገቡትንም ከለከላችሁ።”

53ይህንም ሲናገራቸው፥ ጻፎችና ፈሪሳውያን በአፉ የተናገረውን ሊነጥቁ ሲያደቡ፥ እጅግ ይቃወሙና ስለ ብዙ ነገር እንዲናገር ያነሣሡ ጀመር።

ማብራሪያ

11:1-4 ጌታ ሆይ፣ እንድንጸልይ አስተምረን የሚለው ጥያቄ ጥሩ ጸሎትና እጅግ የሚያስፈልግ ነው፤ ምክንያቱም ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ በመንፈሱና በቃሉ እንዴት መጸለይ እንዳለብን ሊያስተምረን ይችላልና። ጌታ ሆይ፣ መጸለይ ምን እንደሆነ አስተምረኝ፤ ጌታ ሆይ፣ ለዚህ ግዴታ አንቃኝና አነቃቃኝ፤ ጌታ ሆይ፣ ምን መጸለይ እንዳለብኝ ምራኝ፤ ምን መናገር እንዳለብኝ አስተምረኝ። ክርስቶስ ጸሎትን አስተማራቸው፤ ይህ ጸሎትም በተራራው ስብከቱ ላይ ቀደም ብሎ ከሰጠው ጋር እጅግ ተመሳሳይ ነው። በማቴዎስና በሉቃስ ወንጌል ላይ በሚገኘው የጌታ ጸሎት ቃላት ላይ ጥቂት ልዩነቶች አሉ፤ እነዚህ ግን ምንም ፋይዳ የላቸውም። እኛም በምንለምንበት ጊዜ፣ ለሌሎችም ሆነ ለራሳችን በምናቀርባቸው ጥያቄዎች ሁሉ፣ በኃይሉና በቸርነቱ እየታመንን ወደ ሰማያዊ አባታችን እንቅረብ።

ሉቃስ 11:5-13 ክርስቶስ በጸሎት ቅንዓትንና ጽናትን ያበረታታል። የምንፈልገውን ለማግኘት ወደ እግዚአብሔር መቅረብ አለብን፤ ልክ አንድ ሰው ደግ ወደሆነለት ጎረቤቱ ወይም ወዳጁ እንደሚቀርበው። እንጀራን ለማግኘት፤ ማለትም አስፈላጊ የሆነውን ሁሉ ለማግኘት መቅረብ አለብን። እግዚአብሔር ጸሎታችንን በፍጥነት ባይመልስም እንኳን፣ መጸለያችንን ከቀጠልን ግን በተገቢው ጊዜ ይፈጽመዋል።

ምን እንደምንለምን አስተውሉ፤ መንፈስ ቅዱስን መጠየቅ አለብን። ይህም በሚገባ ለመጸለይ ብቻ እንደሚያስፈልግ ሳይሆን፣ ሁሉም መንፈሳዊ በረከቶች በዚያ ውስጥ የተካተቱ በመሆናቸው ነው። ምክንያቱም በመንፈስ ቅዱስ ተጽዕኖ እግዚአብሔርንና ራሳችንን እንድናውቅ፣ ንስሐ እንድንገባ፣ ክርስቶስን እንድናምንና እንድንወድድ እንደረጋለን። በዚህም ዓለም ምቾት እንዲሰማን፣ እንዲሁም በሚመጣውም ዓለም ለደስታ ብቁ እንሆናለን። የሰማይ አባታችንም እነዚህን ሁሉ በረከቶች ለሚለምነው ሁሉ፣ ከተራበ ልጅ ምግብ ከመስጠት ከማይሰስር ወላጅ ይልቅ እጅግ ለመስጠት ዝግጁ ነው። ይህም የእምነት ጸሎት ጥቅም ነው፤ እርሱም ልብን በእግዚአብሔር እንዲረጋጋና እንዲጸና ማድረጉ ነው።

11:14-26 ክርስቶስ አጋንንትን በዚህ መልኩ ማውጣቱ በእርግጥም የሥልጣናቸውን ሙሉ በሙሉ ማጥፋት ነበር። የእያንዳንዱ ያልተለወጠ ኃጢአተኛ ልብ የሰይጣን ቤተ መንግሥት ነው፤ እርሱ የሚኖርበትና የሚገዛበት።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV One day Jesus was praying in a certain place. When he finished, one of his disciples said to him, “Lord, teach us to pr… English BCV ኢየሱስ ኣብ ሓንቲ ስፍራ ኽፅሊ ፀኒሑ ምስ ወድአ፥ ሓደ ኻብ ደቀ መዛሙርቱ፥ “ኦ ጐይታ! ከምቲ ዮሃንስ ንደቀ መዛሙርቱ ፀሎት ዝመሃሮም፥ ፀሎት መሃረና” በሎ። ትግርኛ GAZBIB Yesus iddoo tokkotti in kadhata ture; kadhannaa isaa erga dhaabee booddee, bartoota isaa keessaa tokko, ?Yaa gooftaa, Y… Afaan Oromoo BCV GIZ ወእምዝ ጸለየ በአሐቲ መካን ወፈጺሞ ጸሎተ ይቤሎ አሐዱ እምአርዳኢሁ እግዚኦ መሀረነ ጸሎተ በከመ መሀሮሙ ዮሐንስ ለአርዳኢሁ። giz GAZGAZ Yesus iddoo tokkotti in kadhata ture; kadhannaa isaa erga dhaabee booddee, bartoota isaa keessaa tokko, ?Yaa gooftaa, Y… Afaan Oromoo BCV aksum ኢየሱስ ኣብ ሓንቲ ስፍራ ኽፅሊ ፀኒሑ ምስ ወድአ፥ ሓደ ኻብ ደቀ መዛሙርቱ፥ “ኦ ጐይታ! ከምቲ ዮሃንስ ንደቀ መዛሙርቱ ፀሎት ዝመሃሮም፥ ፀሎት መሃረና” በሎ። ትግርኛ AMHNIV አንድ ቀን ኢየሱስ በአንድ ስፍራ ይጸልይ ነበር፤ ጸሎቱንም እንደ ጨረሰ፣ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ፣ “ጌታ ሆይ፤ ዮሐንስ ደቀ መዛሙርቱን ጸሎት እንዳስተማራቸው አንተም መጸለይን አስተምረን” አለ… አማርኛ SWAHSUV Ikawa alipokuwa mahali fulani akiomba, alipokwisha, mmoja katika wanafunzi wake alimwambia, Bwana, tufundishe sisi kusa… Kiswahili