የሉቃስ ወንጌል 11

AMHNIVአማርኛ54 ጥቅሶች8:50 አዳምጥ
አዳምጥ 8:50 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1አንድ ቀን ኢየሱስ በአንድ ስፍራ ይጸልይ ነበር፤ ጸሎቱንም እንደ ጨረሰ፣ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ፣ “ጌታ ሆይ፤ ዮሐንስ ደቀ መዛሙርቱን ጸሎት እንዳስተማራቸው አንተም መጸለይን አስተምረን” አለው።

2እርሱም እንዲህ አላቸው፤ “ስትጸልዩ እንዲህ በሉ፤ “ ‘አባታችን ሆይ፤ ስምህ ይቀደስ፤ መንግሥትህ ትምጣ፤

3የዕለት እንጀራችንን በየዕለቱ ስጠን፤

4በደላችንን ይቅር በለን፤ እኛም የበደሉንን ሁሉ ይቅር ብለናልና። ወደ ፈተናም አታግባን፤ ከክፉው አድነን እንጂ።”

5ደግሞም እንዲህ አላቸው፤ “ከእናንተ አንዱ ወዳጅ ቢኖረውና በእኩለ ሌሊት ወደ እርሱ ሄዶ፣ ‘ወዳጄ ሆይ፤ ሦስት እንጀራ አበድረኝ፤

6አንድ ባልንጀራዬ ከመንገድ መጥቶብኝ የማቀርብለት ምንም ነገር የለኝምና’ ብሎ ለመነው እንበል።

7“በቤት ውስጥ ያለውም፣ ‘አታስቸግረኝ፤ በሩ ተቈልፎአል፤ ልጆቼም አብረውኝ ተኝተዋል፤ ከእንግዲህ ተነሥቼ ልሰጥህ አልችልም’ ይለዋልን?

8እላችኋለሁ፤ ወዳጁ በመሆኑ ተነሥቶ ባይሰጠው እንኳ፣ ስለ ንዝነዛው ብቻ የሚፈልገውን ሁሉ ይሰጠዋል።

9“ስለዚህ እላችኋለሁ፤ ለምኑ ይሰጣችኋል፤ ፈልጉ ታገኛላችሁ፤ በር አንኳኩ ይከፈትላችኋል፤

10ምክንያቱም የሚለምን ሁሉ ይቀበላል፤ የሚፈልግም ያገኛል፤ በር ለሚያንኳኳም ይከፈትለታል።

11“ከእናንተ መካከል አባት ሆኖ ሳለ ልጁ ዓሣ ቢለምነው እባብ የሚሰጠው ይኖራልን?

12ወይስ ዕንቊላል ቢለምነው ጊንጥ ይሰጠዋልን?

13እናንተ ክፉዎች ሆናችሁ ሳላችሁ፣ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታን መስጠት ካወቃችሁበት፣ የሰማዩ አባታችሁ ታዲያ ለሚለምኑት መንፈስ ቅዱስን እንዴት አብልጦ አይሰጥ!”

14አንድ ቀን ኢየሱስ ድዳ ጋኔን ያወጣ ነበር፤ ጋኔኑም ከወጣለት በኋላ ድዳው ሰው ተናገረ፤ ሕዝቡም ተገረመ።

15አንዳንዶቹ ግን፣ “በአጋንንት አለቃ፣ በብዔልዜቡል፣ አጋንንትን ያወጣል” አሉ፤

16አንዳንዶቹ ደግሞ ሊፈታተኑት ከሰማይ ምልክት እንዲያሳያቸው ከእርሱ ይፈልጉ ነበር።

17ኢየሱስ ግን ሐሳባቸውን ዐውቆ እንዲህ አላቸው፤ “እርስ በርሱ የሚከፋፈል መንግሥት ሁሉ ይጠፋል፤ የሚለያይ ቤትም ይወድቃል።

18ሰይጣንም እርስ በርሱ ከተከፋፈለ፣ መንግሥቱ እንዴት ይጸናል? አጋንንትን በብዔልዜቡል እንደማወጣ ትናገራላችሁና።

19እንግዲህ እኔ አጋንንትን የማወጣው በብዔልዜቡል ከሆነ፣ ልጆቻችሁ በማን ያወጧቸው ይሆን? ስለዚህ እነርሱ ፈራጆች ይሆኑባችኋል።

20እኔ ግን አጋንንትን የማወጣው በእግዚአብሔር ጣት ከሆነ፣ የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ እናንተ እንደ መጣች ዕወቁ።

21“ብርቱ ሰው በሚገባ ታጥቆ ቤቱን ከጠበቀ፣ ንብረቱ በሰላም ይቀመጣል።

22ነገር ግን ይበልጥ ብርቱ የሆነ ሰው መጥቶ ካጠቃውና ካሸነፈው ታምኖበት የነበረውን ትጥቁን ያስፈታዋል፤ ምርኮውንም ወስዶ ለሌሎች ያካፍላል።

23“ከእኔ ጋር ያልሆነ ይቃወመኛል፤ ከእኔ ጋር የማይሰበስብም ይበትናል።

24“ርኵስ መንፈስ ከሰው ሲወጣ ዕረፍት ፍለጋ ውሃ በሌለበት ስፍራ ይንከራተታል፤ ሳያገኝም ሲቀር፣ ወደ ወጣሁበት ቤቴ እመለሳለሁ ይላል፤

25ሲመለስም ቤቱ ተጠራርጐና ተስተካክሎ ያገኘዋል።

26ከዚያም በኋላ ሄዶ ሌሎች ከእርሱ የከፉ ሰባት አጋንንት ይዞ ይመጣል፤ ገብተውበትም በዚያ ይኖራሉ፤ ለዚያ ሰው ከመጀመሪያው ይልቅ የኋለኛው ሁኔታ የከፋ ይሆንበታል።

27ኢየሱስ ይህን እየተናገረ እያለ፣ ከሕዝቡ መካከል አንዲት ሴት ድምፅዋን ከፍ አድርጋ፣ “የተሸከመችህ ማሕፀንና የጠባሃቸው ጡቶች ብፁዓን ናቸው” አለችው።

28እርሱ ግን፣ “ብፁዓንስ የእግዚአብሔርን ቃል ሰምተው የሚታዘዙት ናቸው” አለ።

29ብዙ ሕዝብ እየተሰበሰበ በሄደ ጊዜ ኢየሱስ እንዲህ ይል ጀመር፤ “ይህ ትውልድ ክፉ ነው፤ ታምራዊ ምልክት ይፈልጋል፤ ነገር ግን ከዮናስ ምልክት በስተቀር ሌላ አይሰጠውም።

30ምክንያቱም ዮናስ ለነነዌ ሰዎች ምልክት እንደሆናቸው የሰው ልጅም ለዚህ ትውልድ ምልክት ይሆናል።

31የደቡቧ ንግሥት በፍርድ ጊዜ ከዚህ ትውልድ ጋር ተነሥታ ትፈርድባቸዋለች፤ እርሷ የሰሎሞንን ጥበብ ለመስማት ከምድር ዳርቻ መጥታለችና፤ እነሆ፤ ከሰሎሞን የሚበልጥ እዚህ አለ።

32የነነዌ ሰዎችም በፍርድ ጊዜ ከዚህ ትውልድ ጋር ተነሥተው ይፈርዱበታል፤ እነርሱ የዮናስን ስብከት ሰምተው ንስሓ ገብተዋልና፤ እነሆ፣ ከዮናስ የሚበልጥ እዚህ አለ።

33“መብራት አብርቶ በስውር ቦታ ወይም ከእንቅብ በታች የሚያስቀምጥ ማንም የለም፤ ይልቁን የሚገቡ ሰዎች ብርሃኑን እንዲያዩ በመቅረዝ ላይ ያስቀምጠዋል።

34የሰውነትህ ብርሃን ዐይንህ ናት፤ ዐይንህ ጤናማ ስትሆን መላ ሰውነትህ ብሩህ ይሆናል፤ ዐይንህ ታማሚ ከሆነች ግን መላ ሰውነትህ የጨለመ ይሆናል።

35ስለዚህ በውስጥህ ያለው ብርሃን ጨለማ እንዳይሆን ተጠንቀቅ።

36እንግዲህ ሰውነትህ ሁሉ ብሩህ ከሆነና የጨለመ የሰውነት ክፍል ከሌለበት፣ የሰውነትህ ሁለንተና መብራት በወገግታው ያበራልህ ያህል ይደምቃል።”

37ኢየሱስ ንግግሩን እንደ ጨረሰ፣ አንድ ፈሪሳዊ ከእርሱ ጋር ምግብ እንዲበላ ጋበዘው፤ እርሱም አብሮት ገብቶ በማእድ ተቀመጠ።

38ፈሪሳዊውም ኢየሱስ ከምግብ በፊት እጁን እንዳልታጠበ ባየ ጊዜ ተደነቀ።

39ጌታም እንዲህ አለው፤ “አሁን እናንተ ፈሪሳውያን የጽዋውንና የወጭቱን ውጫዊ ክፍል ታጸዳላችሁ፤ ውስጣችሁ ግን በስስትና በክፋት የተሞላ ነው።

40እናንት ሞኞች፤ የውጪውን የፈጠረ የውስጡንም አልፈጠረምን?

41ነገር ግን በውስጥ ያለውን ምጽዋት አድርጋችሁ ስጡ፤ በዚህ ጊዜ ሁሉም ንጹሕ ይሆንላችኋል።

42“እናንት ፈሪሳውያን ግን ወዮላችሁ፤ ከአዝሙድና ከጤና አዳም እንዲሁም ከአትክልት ሁሉ ዐሥራት ታወጣላችሁ፤ ሆኖም ፍትሕንና እግዚአብሔርን መውደድ ቸል ትላላችሁ፤ ነገር ግን ያንን ሳትተዉ ይኸኛውን ማድረግ በተገባችሁ ነበር።

43“እናንት ፈሪሳውያን ወዮላችሁ፤ በምኵራብ የክብር መቀመጫ፣ በገበያ መካከልም እጅ መነሣትን ትወዳላችሁና።

44“ሰዎች ሳያውቁ በላዩ የሚሄዱበትን የተሰወረ መቃብር ስለምትመስሉ፣ ወዮላችሁ።”

45ከሕግ ዐዋቂዎች አንዱ መልሶ “መምህር ሆይ፤ እንዲህ ስትናገር እኮ እኛንም መስደብህ ነው” ሲል መለሰለት።

46ኢየሱስም እንዲህ አለ፤ “እናንት ሕግ ዐዋቂዎችም ደግሞ ወዮላችሁ፤ ሰዎች ሊሸከሙ የማይችሉትን ከባድ ሸክም ታሸክማላችሁ፤ እናንተ ራሳችሁ ግን በጣታችሁ እንኳ አትነኵትም።

47“አባቶቻችሁ የገደሏቸውን የነቢያትን መቃብር ስለምታበጃጁ፣ ወዮላችሁ፤

48እንግዲህ የአባቶቻችሁን ሥራ የምታጸኑ ምስክሮች ናችሁ፤ እነርሱ ነቢያትን ገደሉ፣ እናንተም መቃብራቸውን ታበጃጃላችሁ።

49ስለዚህም የእግዚአብሔር ጥበብ እንዲህ አለች፤ ‘ነቢያትንና ሐዋርያትን እልክላቸዋለሁ፤ እነርሱ አንዳንዶቹን ይገድላሉ፤ ሌሎችንም ያሳድዳሉ።’

50ስለዚህ ይህ ትውልድ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ስለ ፈሰሰው፣ ስለ ነቢያት ሁሉ ደም ተጠያቂ ነው፤

51ከአቤል ደም ጀምሮ፣ በመሠዊያውና በቤተ መቅደሱ መካከል እስከ ፈሰሰው እስከ ዘካርያስ ደም ድረስ ይፈለግበታል፤ አዎን፣ እላችኋለሁ፤ ይህ ትውልድ ለዚህ ተጠያቂ ነው።

52“እናንት ሕግ ዐዋቂዎች ወዮላችሁ፤ የዕውቀትን መክፈቻ ነጥቃችሁ ወስዳችኋልና፤ እናንተ ራሳችሁ አልገባችሁበትም፤ የሚገቡትንም ከልክላችኋል።”

53ኢየሱስ ከዚያ ከወጣ በኋላ፣ ጸሐፍትና ፈሪሳውያን ክፉኛ ይቃወሙትና በጥያቄም ያዋክቡት ጀመር፤

54ከአፉ በሚወጣውም ቃል ሊያጠምዱት ያደቡ ነበር።

ማብራሪያ

11:1-4 ጌታ ሆይ፣ እንድንጸልይ አስተምረን የሚለው ጥያቄ ጥሩ ጸሎትና እጅግ የሚያስፈልግ ነው፤ ምክንያቱም ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ በመንፈሱና በቃሉ እንዴት መጸለይ እንዳለብን ሊያስተምረን ይችላልና። ጌታ ሆይ፣ መጸለይ ምን እንደሆነ አስተምረኝ፤ ጌታ ሆይ፣ ለዚህ ግዴታ አንቃኝና አነቃቃኝ፤ ጌታ ሆይ፣ ምን መጸለይ እንዳለብኝ ምራኝ፤ ምን መናገር እንዳለብኝ አስተምረኝ። ክርስቶስ ጸሎትን አስተማራቸው፤ ይህ ጸሎትም በተራራው ስብከቱ ላይ ቀደም ብሎ ከሰጠው ጋር እጅግ ተመሳሳይ ነው። በማቴዎስና በሉቃስ ወንጌል ላይ በሚገኘው የጌታ ጸሎት ቃላት ላይ ጥቂት ልዩነቶች አሉ፤ እነዚህ ግን ምንም ፋይዳ የላቸውም። እኛም በምንለምንበት ጊዜ፣ ለሌሎችም ሆነ ለራሳችን በምናቀርባቸው ጥያቄዎች ሁሉ፣ በኃይሉና በቸርነቱ እየታመንን ወደ ሰማያዊ አባታችን እንቅረብ።

ሉቃስ 11:5-13 ክርስቶስ በጸሎት ቅንዓትንና ጽናትን ያበረታታል። የምንፈልገውን ለማግኘት ወደ እግዚአብሔር መቅረብ አለብን፤ ልክ አንድ ሰው ደግ ወደሆነለት ጎረቤቱ ወይም ወዳጁ እንደሚቀርበው። እንጀራን ለማግኘት፤ ማለትም አስፈላጊ የሆነውን ሁሉ ለማግኘት መቅረብ አለብን። እግዚአብሔር ጸሎታችንን በፍጥነት ባይመልስም እንኳን፣ መጸለያችንን ከቀጠልን ግን በተገቢው ጊዜ ይፈጽመዋል።

ምን እንደምንለምን አስተውሉ፤ መንፈስ ቅዱስን መጠየቅ አለብን። ይህም በሚገባ ለመጸለይ ብቻ እንደሚያስፈልግ ሳይሆን፣ ሁሉም መንፈሳዊ በረከቶች በዚያ ውስጥ የተካተቱ በመሆናቸው ነው። ምክንያቱም በመንፈስ ቅዱስ ተጽዕኖ እግዚአብሔርንና ራሳችንን እንድናውቅ፣ ንስሐ እንድንገባ፣ ክርስቶስን እንድናምንና እንድንወድድ እንደረጋለን። በዚህም ዓለም ምቾት እንዲሰማን፣ እንዲሁም በሚመጣውም ዓለም ለደስታ ብቁ እንሆናለን። የሰማይ አባታችንም እነዚህን ሁሉ በረከቶች ለሚለምነው ሁሉ፣ ከተራበ ልጅ ምግብ ከመስጠት ከማይሰስር ወላጅ ይልቅ እጅግ ለመስጠት ዝግጁ ነው። ይህም የእምነት ጸሎት ጥቅም ነው፤ እርሱም ልብን በእግዚአብሔር እንዲረጋጋና እንዲጸና ማድረጉ ነው።

11:14-26 ክርስቶስ አጋንንትን በዚህ መልኩ ማውጣቱ በእርግጥም የሥልጣናቸውን ሙሉ በሙሉ ማጥፋት ነበር። የእያንዳንዱ ያልተለወጠ ኃጢአተኛ ልብ የሰይጣን ቤተ መንግሥት ነው፤ እርሱ የሚኖርበትና የሚገዛበት።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG እርሱም በአንድ ስፍራ ይጸልይ ነበር፥ በጨረሰም ጊዜ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ፦ “ጌታ ሆይ፥ ዮሐንስ ደቀ መዛሙርቱን እንዳስተማረ እንጸልይ ዘንድ አስተምረን” አለው። አማርኛ ENGNIV One day Jesus was praying in a certain place. When he finished, one of his disciples said to him, “Lord, teach us to pr… English BCV ኢየሱስ ኣብ ሓንቲ ስፍራ ኽፅሊ ፀኒሑ ምስ ወድአ፥ ሓደ ኻብ ደቀ መዛሙርቱ፥ “ኦ ጐይታ! ከምቲ ዮሃንስ ንደቀ መዛሙርቱ ፀሎት ዝመሃሮም፥ ፀሎት መሃረና” በሎ። ትግርኛ GAZBIB Yesus iddoo tokkotti in kadhata ture; kadhannaa isaa erga dhaabee booddee, bartoota isaa keessaa tokko, ?Yaa gooftaa, Y… Afaan Oromoo BCV GIZ ወእምዝ ጸለየ በአሐቲ መካን ወፈጺሞ ጸሎተ ይቤሎ አሐዱ እምአርዳኢሁ እግዚኦ መሀረነ ጸሎተ በከመ መሀሮሙ ዮሐንስ ለአርዳኢሁ። giz GAZGAZ Yesus iddoo tokkotti in kadhata ture; kadhannaa isaa erga dhaabee booddee, bartoota isaa keessaa tokko, ?Yaa gooftaa, Y… Afaan Oromoo BCV aksum ኢየሱስ ኣብ ሓንቲ ስፍራ ኽፅሊ ፀኒሑ ምስ ወድአ፥ ሓደ ኻብ ደቀ መዛሙርቱ፥ “ኦ ጐይታ! ከምቲ ዮሃንስ ንደቀ መዛሙርቱ ፀሎት ዝመሃሮም፥ ፀሎት መሃረና” በሎ። ትግርኛ SWAHSUV Ikawa alipokuwa mahali fulani akiomba, alipokwisha, mmoja katika wanafunzi wake alimwambia, Bwana, tufundishe sisi kusa… Kiswahili