የዮሐንስ ወንጌል 5

AMHNIVአማርኛ47 ጥቅሶች6:31 አዳምጥ
አዳምጥ 6:31 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ከዚህ በኋላ የአይሁድ በዓል ነበረ፤ ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ።

2በኢየሩሳሌም፣ በበጎች በር አጠገብ፣ አምስት ባለ መጠለያ መመላለሻዎች የነበሯት፣ በአራማይክ ቋንቋ ቤተ ሳይዳ የተባለች አንዲት መጠመቂያ አለች።

3በእነዚህም መመላለሻዎች ውስጥ ብዙ አካለ ስንኩላን፣ ዐይነ ስውሮች፣ አንካሶችና ሽባዎች ይተኙ ነበር። [የውሃውንም መንቀሳቀስ እየተጠባበቁ፣

4ዐልፎ ዐልፎ የጌታ መልአክ ወርዶ ውሃውን በሚያናውጥበት ጊዜ፣ ቀድሞ ወደ መጠመቂያዪቱ የገባ ካደረበት ማንኛውም በሽታ ይፈወስ ነበር።]

5በዚያም ለሠላሳ ስምንት ዓመት ሕመምተኛ ሆኖ የኖረ አንድ ሰው ነበር።

6ኢየሱስም ይህን ሰው ተኝቶ ባገኘው ጊዜ፣ ለብዙ ጊዜ በዚህ ሁኔታ እንደ ነበር ዐውቆ “ልትድን ትፈልጋለህን?” አለው።

7ሕመምተኛውም መልሶ፣ “ጌታዬ፣ ውሃው በሚናወጥበት ጊዜ ወደ መጠመቂያዪቱ የሚያወርደኝ ሰው የለኝም፤ ለመግባትም ስሞክር ሌላው ይቀድመኛል” አለው።

8ኢየሱስም፣ “ተነሥ! መተኛህን ተሸክመህ ሂድ” አለው።

9ሰውየውም ወዲያው ተፈወሰ፤ መተኛውንም ተሸክሞ ሄደ። ይህም የሆነው በሰንበት ቀን ነበር።

10አይሁድም የተፈወሰውን ሰው፣ “ሰንበት ስለ ሆነ መተኛህን እንድትሸከም ሕጉ አይፈቅድልህም” አሉት።

11እርሱ ግን፣ “ያ የፈወሰኝ ሰው፣ ‘መተኛህን ተሸክመህ ሂድ’ ብሎኛል” ሲል መለሰላቸው።

12እነርሱም፣ “ ‘መተኛህን ተሸክመህ ሂድ’ ያለህ እርሱ ማነው?” ብለው ጠየቁት።

13ኢየሱስ ፈቀቅ ብሎ ወደ ሕዝብ መካከል ገብቶ ስለ ነበር፣ ሰውየው ማን እንደፈወሰው አላወቀም።

14ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ያን ሰው በቤተ መቅደስ አግኝቶ፣ “እነሆ፣ ተፈውሰሃል፤ ከእንግዲህ ግን ኀጢአት አትሥራ፤ ያለዚያ ከዚህ የባሰ ይደርስብሃል” አለው።

15ሰውየውም የፈወሰው ኢየሱስ መሆኑን ሄዶ ለአይሁድ ነገራቸው።

16አይሁድም፣ በሰንበት ቀን እነዚህን ድርጊቶች በመፈጸሙ፣ ኢየሱስን ያሳድዱት ነበር።

17ኢየሱስም፣ “አባቴ እስካሁን እየሠራ ነው፤ እኔም ደግሞ እሠራለሁ” አላቸው።

18እንግዲህ አይሁድ፣ ኢየሱስ ሰንበትን ስለሻረ ብቻ ሳይሆን፣ እግዚአብሔርን አባቱ በማድረግ፣ ራሱን ከእግዚአብሔር እኩል በማድረጉ፣ ሊገድሉት አጥብቀው ይፈልጉት ነበር።

19ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ “እውነት እላችኋለሁ፤ አብ ሲሠራ ያየውን ብቻ እንጂ ወልድ ከራሱ ምንም ሊያደርግ አይችልም፤ አብ የሚያደርገውን ሁሉ ወልድ ደግሞ ያደርጋልና፤

20አብ ወልድን ስለሚወድ የሚያደርገውን ሁሉ ያሳየዋል፤ ትደነቁም ዘንድ ከእነዚህም የሚበልጥ ነገር ያሳየዋል።

21ምክንያቱም አብ ሙታንን እንደሚያስነሣ፣ ሕይወትንም እንደሚሰጥ፣ ወልድም ደግሞ ለሚፈቅደው ሁሉ ሕይወትን ይሰጣል።

22አብ በማንም ላይ አይፈርድም፤ ነገር ግን ፍርድን ሁሉ ለወልድ አሳልፎ ሰጥቶታል፤

23ይኸውም፣ ሁሉ አብን እንደሚያከብሩ ወልድን ያከብሩት ዘንድ ነው፤ ወልድን የማያከብር፣ የላከውን አብንም አያከብርም።

24“እውነት እላችኋለሁ፤ ቃሌን የሚሰማ፣ በላከኝም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ ከሞት ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም።

25እውነት እላችኋለሁ፤ ሙታን የእግዚአብሔርን ልጅ ድምፅ የሚሰሙበት ጊዜ ይመጣል፤ አሁንም መጥቶአል፤ የሚሰሙትም በሕይወት ይኖራሉ።

26አብ በራሱ ሕይወት እንዳለው ሁሉ፣ ወልድም በራሱ ሕይወት እንዲኖረው ሰጥቶታልና፤

27ወልድ የሰው ልጅ ስለ ሆነም እንዲፈርድ ሥልጣን ሰጥቶታል።

28“በዚህ አትደነቁ፤ መቃብር ውስጥ ያሉ ሁሉ ድምፁን የሚሰሙበት ጊዜ ይመጣል፤

29መልካም የሠሩ ለሕይወት ትንሣኤ፣ ክፉ የሠሩ ለፍርድ ትንሣኤ ይወጣሉ።

30እኔ ብቻዬን ከራሴ ምንም ማድረግ አልችልም፤ የምፈርደው የምሰማውን ብቻ ነው፤ የላከኝን እንጂ የራሴን ፈቃድ ስለማልሻም ፍርዴ ትክክል ነው።

31“እኔ ስለ ራሴ ብመሰክር፣ ምስክርነቴ ተቀባይነት አይኖረውም።

32ስለ እኔ የሚመሰክር ሌላ አለ፤ እርሱ ስለ እኔ የሚሰጠውም ምስክርነት እውነት እንደሆነ ዐውቃለሁ።

33“ወደ ዮሐንስ ልካችሁ ነበር፤ እርሱም ስለ እውነት መስክሮአል፤

34እኔ የሰው ምስክርነት የምቀበል አይደለሁም፤ ይህን የምናገረው ግን እናንተ እንድትድኑ ነው።

35ዮሐንስ እየነደደ ብርሃን የሚሰጥ መብራት ነበረ፤ እናንተም ለጥቂት ጊዜ በብርሃኑ ደስ ልትሰኙ ወደዳችሁ።

36“እኔ ግን ከዮሐንስ ምስክርነት የላቀ ምስክር አለኝ፤ እንድፈጽመው አብ የሰጠኝ፣ እኔም የምሠራው ሥራ አብ እንደ ላከኝ ይመሰክራል።

37የላከኝ አብ ራሱ ስለ እኔ መስክሮአል፤ እናንተም ከቶ ድምፁን አልሰማችሁም፤ መልኩንም አላያችሁም፤

38የላከውንም ስላላመናችሁ ቃሉ በእናንተ አይኖርም።

39በእነርሱ የዘላለም ሕይወትን የምታገኙ እየመሰላችሁ፣ መጻሕፍትን ትመረምራላችሁ፤ እነዚሁ መጻሕፍት ስለ እኔ የሚመሰክሩ ናቸው፤

40እናንተ ግን፣ ሕይወት እንዲኖራችሁ ወደ እኔ መምጣት አትፈልጉም።

41“እኔ ከሰው ክብር አልቀበልም፤

42ነገር ግን እናንተን ዐውቃችኋለሁ፤ የእግዚአብሔርም ፍቅር በልባችሁ እንደሌለ ዐውቃለሁ።

43እኔ በአባቴ ስም መጥቼ አልተቀበላችሁኝም፤ ሌላው በራሱ ስም ቢመጣ ግን ትቀበሉታላችሁ።

44እናንተ እርስ በርሳችሁ ክብር የምትሰጣጡ፣ ነገር ግን ከአንዱ አምላክ የሚመጣውን ክብር የማትፈልጉ ከሆነ፣ እንዴት ልታምኑ ትችላላችሁ?

45“ከሳሻችሁ ተስፋ የጣላችሁበት ሙሴ እንጂ፣ እኔ በአብ ፊት የምከሳችሁ አይምሰላችሁ፤

46ሙሴን ብታምኑ ኖሮ፣ እኔን ባመናችሁ ነበር፤ ምክንያቱም እርሱ የጻፈው ስለ እኔ ነው።

47እርሱ የጻፈውን ካላመናችሁ፣ እኔ የምናገረውን እንዴት ታምናላችሁ?”

ማብራሪያ

፭፥፩-፱ ሁላችንም በተፈጥሮአችን በመንፈሳዊ ነገሮች አቅመ ቢሶች፣ ዓይነ ስውሮች፣ አንካሶችና የሰለልን ሰዎች ነን፤ ነገር ግን እሱን በትኩረት የምንከታተል ከሆነ፣ ለፈውሳችን ሙሉ ዝግጅት ተደርጓል። አንድ መልአክ ወርዶ ውኃውን ያናውጥ ነበር፤ ያም ውኃ ማንኛውንም ዓይነት በሽታ ይፈውስ ነበር፣ ነገር ግን መጀመሪያ የገባው ብቻ ነበር የሚጠቀመው። ይህ የሚያስተምረን ዳግመኛ የማይመለስን ዕድል እንዳናባክን ጥንቃቄ ማድረግን ነው። ያ ሰው ለሠላሳ ስምንት ዓመታት የሰውነቱን አካላት መጠቀም አቅቶት ነበር። እኛስ ምናልባት ለብዙ ዓመታት የአንድ ቀን ሕመም ምን እንደሆነ የማናውቅ፣ አንድ አድካሚ ምሽት ስላሳለፍን እናማርራለንን? ከእኛ የተሻሉ ብዙዎች የአንድ ቀን ደህንነት ምን እንደሆነ የማያውቁ ሲሆኑ? ክርስቶስም ይህን ሰው ከሌሎቹ ለየው። በስቃይ ውስጥ ለረጅም ጊዜ የቆዩ ሰዎች፣ እግዚአብሔር የቆይታ ጊዜያቸውን በሙሉ እንደሚያውቅ በማሰብ ራሳቸውን ማጽናናት ይችላሉ። ልብ በሉ፣ ይህ ሰው ስለጎረቤቶቹ ደግነት የጎደለው ድርጊት ይናገራል እንጂ ምንም ዓይነት የቅሬታ ነጸብራቅ አልነበረበትም። አመስጋኞች መሆን እንደሚያስፈልገን ሁሉ፣ ታጋሾችም መሆን አለብን። ጌታችን ኢየሱስም እርሱ ባይጠይቀውም ሆነ ባያስበውም ፈወሰው። ‹ተነሳና ሂድ!› የእግዚአብሔር ትእዛዝ – ‹ተመለሱና ኑሩ፤ አዲስ ልብ ፍጠሩ› – የራሱን ልዩ ጸጋ ሳይጨምር በእኛ ውስጥ ኃይል አለ ብሎ አያስብም፤ ልክ ይህ ትእዛዝ በዚያ አቅመ ቢስ ሰው ውስጥ እንዲህ ያለ ኃይል አለ ብሎ እንዳላሰበው። ይህ የሆነው በክርስቶስ ኃይል ነውና፣ ክብር ሁሉ ለእርሱ መሆን አለበት። ለዚያ ምስኪን አንካሳ በድንገት ራሱን ቀላል፣ ብርቱና ራሱን መርዳት የሚችል ሆኖ ሲያገኝ ምንኛ ደስ የሚያሰኝ ድንገተኛ ነገር ነው! የመንፈሳዊ ፈውስ ማረጋገጫችን መነሣታችንና መሄዳችን ነው። ክርስቶስ መንፈሳዊ ደዌዎቻችንን ከፈወሰልን፣ በላከን ሁሉ እንሂድ፣ በእኛ ላይ የጣለውን ሁሉ እናንሣ፣ በፊቱም እንመላለስ።

5:10-16 ከኃጢአት ቅጣት የተገላገሉ ሰዎች ፍርሃትና መገደብ ካለፈ በኋላ፣ መለኮታዊ ጸጋ ምንጩን ካላደረቀው በቀር፣ እንደገና ወደ ኃጢአት የመመለስ አደጋ ውስጥ ናቸው። ምእመናን ከበሽታው የዳኑበት መከራ፣ የኃጢአትን ምሬት ስለተሰማን፣ ከእንግዲህ ወዲያ ኃጢአት እንዳንሠራ ያስጠነቅቀናል። ይህም የእያንዳንዱ የአምላክ እንክብካቤ ድምፅ ነው፤ 'ሂድ፥ ከእንግዲህም ወዲያ ኃጢአት አትሥራ።' ክርስቶስ ይህንን ማስጠንቀቂያ መስጠት አስፈላጊ እንደሆነ አየ፤ ሰዎች ሲታመሙ ብዙ እንደሚобеስሱ፤ አዲስ ሲፈወሱ ጥቂት ብቻ እንደሚፈጽሙ፤ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ግን ሁሉንም እንደሚረሱ የተለመደ ነውና። ክርስቶስ ስለሚመጣው ቁጣ ተናገረ፤ እርሱም አንዳንድ ክፉ ሰዎች ከሕገ ወጥ ፍላጎቶቻቸው የተነሳ ሊቀበሉት ከሚገባቸው ከብዙ ሰዓታት፣ እንዲያውም ከሳምንታትና ከዓመታት ሥቃይ አወዳድሮ የማይገኝለት እጅግ የከፋ ነው። እንዲህ ያሉት መከራዎች ከባድ ከሆኑ ደግሞ፣ የክፉዎች የዘላለም ቅጣት ምን ያህል አስፈሪ ይሆን!

5:17-23 የተአምራቱ መለኮታዊ ኃይል ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን አረጋግጧል፤ እርሱም እንደ ፈቃዱ ከአባቱ ጋር እንደሚሠራና እንደ እርሱም እንደሚሠራ አወጀ።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6