የዮሐንስ ወንጌል 4

AMHEVGአማርኛ53 ጥቅሶች6:30 አዳምጥ
አዳምጥ 6:30 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1እንግዲህ፦ “ኢየሱስ ከዮሐንስ ይልቅ ደቀ መዛሙርት ያደርጋል፡ ያጠምቅማል፡” ማለትን ፈሪሳውያን እንደ ሰሙ ጌታ ባወቀ ጊዜ፥

2ይሁዳን ትቶ ወደ ገሊላ ደግሞ ሄደ፤ ዳሩ ግን ደቀ መዛሙርቱ እንጂ ኢየሱስ ራሱ አላጠመቀም።

4በሰማርያም ሊያልፍ ግድ ሆነበት።

5ስለዚህ ያዕቆብ ለልጁ ለዮሴፍ በሰጠው ስፍራ አጠገብ ወደምትሆን ሲካር ወደምትባል የሰማርያ ከተማ መጣ፤

6በዚያም የያዕቆብ ጕድጓድ ነበረ። ኢየሱስም መንገድ ከመሄድ ደክሞ በጕድጓድ አጠገብ እንዲህ ተቀመጠ፤ ጊዜውም ስድስት ሰዓት ያህል ነበረ።

7ከሰማርያ አንዲት ሴት ውኃ ልትቀዳ መጣች። ኢየሱስም፦ “ውኃ አጠጪኝ” አላት፤

8ደቀ መዛሙርቱ ምግብ ሊገዙ ወደ ከተማ ሄደው ነበርና።

9ስለዚህ ሳምራዊቲቱ፦ “አንተ የይሁዳ ሰው ስትሆን ሳምራዊት ሴት ከምሆን ከእኔ መጠጥ እንዴት ትለምናለህ?” አለችው፤ አይሁድ ከሳምራውያን ጋር አይተባበሩም ነበርና።

10ኢየሱስ መልሶ፦ “የእግዚአብሔርን ስጦታና፦ ‘ውኃ አጠጪኝ፥’ የሚልሽ ማን መሆኑንስ ብታውቂ፥ አንቺ ትለምኚው ነበርሽ፡ የሕይወትም ውኃ ይሰጥሽ ነበር፡” አላት።

11ሴቲቱ፦ “ጌታ ሆይ፥ መቅጃ የለህም፡ ጕድጓዱም ጥልቅ ነው፤ እንግዲህ የሕይወት ውኃ ከወዴት ታገኛለህ?

12በእውኑ አንተ ይህን ጕድጓድ ከሰጠን ከአባታችን ከያዕቆብ ትበልጣለህን? ራሱም ልጆቹም ከብቶቹም ከዚህ ጠጥተዋል፡” አለችው።

13ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላት፦ “ከዚህ ውኃ የሚጠጣ ሁሉ እንደ ገና ይጠማል፤

14እኔ ከምሰጠው ውኃ የሚጠጣ ሁሉ ግን ለዘላለም አይጠማም፥ እኔ የምሰጠው ውኃ በእርሱ ውስጥ ለዘላለም ሕይወት የሚፈልቅ የውኃ ምንጭ ይሆናል እንጂ።”

15ሴቲቱ፦ “ጌታ ሆይ፥ እንዳልጠማ ውኃም ልቀዳ ወደዚህ እንዳልመጣ ይህን ውኃ ስጠኝ፡” አለችው።

16ኢየሱስም፦ “ሂጂና ባልሽን ጠርተሽ ወደዚህ ነዪ” አላት።

17ሴቲቱ መልሳ፦ “ባል የለኝም” አለችው። ኢየሱስ አላት፦ “ባል የለኝም በማለትሽ መልካም ተናገርሽ፤

18አምስት ባሎች ነበሩሽና፥ አሁን ከአንቺ ጋር ያለው ባልሽ አይደለም፤ በዚህስ እውነት ተናገርሽ።”

19ሴቲቱ፦ “ጌታ ሆይ፥ አንተ ነቢይ እንደ ሆንህ አያለሁ።

20አባቶቻችን በዚህ ተራራ ሰገዱ፤ እናንተም፦ ‘ሰው ሊሰግድበት የሚገባው ስፍራ በኢየሩሳሌም ነው፡’ ትላላችሁ፡” አለችው።

21ኢየሱስም እንዲህ አላት፦ “አንቺ ሴት፥ እመኚኝ፥ በዚህ ተራራ ወይም በኢየሩሳሌም ለአብ የማትሰግዱበት ጊዜ ይመጣል።

22እናንተስ ለማታውቁት ትሰግዳላችሁ፤ እኛ መዳን ከአይሁድ ነውና ለምናውቀው እንሰግዳለን።

23ነገር ግን በእውነት የሚሰግዱ ለአብ በመንፈስና በእውነት የሚሰግዱበት ጊዜ ይመጣል አሁንም ሆኖአል፤ አብ ሊሰግዱለት እንደ እነዚህ ያሉትን ይሻልና፤

24እግዚአብሔር መንፈስ ነው፥ የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ያስፈልጋቸዋል።”

25ሴቲቱ፦ “ክርስቶስ የሚባል መሲሕ እንዲመጣ አውቃለሁ፤ እርሱ ሲመጣ ሁሉን ይነግረናል” አለችው።

26ኢየሱስ፦ “የምናገርሽ እኔ እርሱ ነኝ” አላት።

27በዚያም ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ መጡና ከሴት ጋር በመነጋገሩ ተደነቁ፤ ነገር ግን፦ “ምን ትፈልጊያለሽ?” ወይም፦ “ስለ ምን ትናገራታለህ?” ያለ ማንም አልነበረም።

28ሴቲቱም እንስራዋን ትታ ወደ ከተማ ሄደች ለሰዎችም፦

29“ያደረግሁትን ሁሉ የነገረኝን ሰው ኑና እዩ፤ እንጃ እርሱ ክርስቶስ ይሆንን?” አለች።

30ከከተማ ወጥተው ወደ እርሱ ይመጡ ነበር።

31ይህም ሲሆን ሳለ ደቀ መዛሙርቱ፦ “መምህር ሆይ፥ ብላ” ብለው ለመኑት።

32እርሱ ግን አላቸው፦ “እናንተ የማታውቁት የምበላው መብል ለእኔ አለኝ።”

33ስለዚህ ደቀ መዛሙርቱ፦ “የሚበላው አንዳች ሰው አምጥቶለት ይሆንን?” ተባባሉ።

34ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “የእኔስ መብል የላከኝን ፈቃድ አደርግ ዘንድ ሥራውንም እፈጽም ዘንድ ነው።

35እናንተ፦ ‘ገና አራት ወር ቀርቶአል መከርም ይመጣል፥’ ትሉ የለምን? እነሆ እላችኋለሁ፥ ዓይናችሁን አንሡ አዝመራውም አሁን እንደ ነጣ እርሻውን ተመልከቱ።

36የሚያጭድ ደመወዝን ይቀበላል፥ የሚዘራና የሚያጭድም አብረው ደስ እንዲላቸው ለዘላለም ሕይወት ፍሬን ይሰበስባል።

37አንዱ ይዘራል አንዱም ያጭዳል የሚለው ቃል በዚህ እውነት ሆኖአልና።

38እኔም እናንተ ያልደከማችሁበትን ታጭዱ ዘንድ ሰደድኋችሁ፤ ሌሎች ደከሙ እናንተም በድካማቸው ገባችሁ።”

39ሴቲቱም፦ “ያደረግሁትን ሁሉ ነገረኝ” ብላ ስለ መሰከረችው ቃል ከዚያች ከተማ የሰማርያ ሰዎች ብዙ አመኑበት።

40የሰማርያ ሰዎችም ወደ እርሱ በመጡ ጊዜ በእነርሱ ዘንድ እንዲኖር ለመኑት፤ በዚያም ሁለት ቀን ያህል ኖረ።

41ስለ ቃሉ ከፊተኞች ይልቅ ብዙ ሰዎች አመኑ፤

42ሴቲቱንም፦ “አሁን የምናምን ስለ ቃልሽ አይደለም፥ እኛ ራሳችን ሰምተነዋልና፤ እርሱም በእውነት ክርስቶስ የዓለም መድኃኒት እንደ ሆነ እናውቃለን፡” ይሉአት ነበር።

43ከሁለቱ ቀኖችም በኋላ ከዚያ ወጥቶ ወደ ገሊላ ሄደ።

44ነቢይ በገዛ አገሩ እንዳይከበር ኢየሱስ ራሱ መስክሮአልና።

45ወደ ገሊላም በመጣ ጊዜ፥ የገሊላ ሰዎች ራሳቸው ደግሞ ለበዓል መጥተው ነበርና በበዓል በኢየሩሳሌም ያደረገውን ሁሉ ስላዩ ተቀበሉት።

46ኢየሱስም ውኃውን የወይን ጠጅ ወዳደረገባት ወደ ገሊላ ቃና ዳግመኛ መጣ። በቅፍርናሆምም ልጁ የታመመበት ከንጉሥ ቤት አንድ ሹም ነበረ።

47እርሱም ኢየሱስ ከይሁዳ ወደ ገሊላ እንደ መጣ ሰምቶ ልጁ ሊሞት ስላለው ወደ እርሱ ሄደ ወርዶም እንዲፈውስለት ለመነው።

48ስለዚህም ኢየሱስ፦ “ምልክትና ድንቅ ነገር ካላያችሁ ከቶ አታምኑም” አለው።

49ሹሙም፦ “ጌታ ሆይ፥ ብላቴናዬ ሳይሞት ውረድ” አለው።

50ኢየሱስም፦ “ሂድ፤ ልጅህ በሕይወት አለ፡” አለው። ሰውዬውም ኢየሱስ የነገረውን ቃል አምኖ ሄደ።

51እርሱም ሲወርድ ሳለ ባሮቹ ተገናኙትና፦ “ብላቴናህ በሕይወት አለ፡” ብለው ነገሩት።

52እርሱም በጎ የሆነበትን ሰዓት ጠየቃቸው፤ እነርሱም፦ “ትናንት በሰባት ሰዓት ንዳዱ ለቀቀው፡” አሉት።

53አባቱም ኢየሱስ፦ “ልጅህ በሕይወት አለ፡” ባለው በዚያ ሰዓት እንደ ሆነ አወቀ፤ እርሱም ከቤተ ሰዎቹ ሁሉ ጋር አመነ።

54ይህም ደግሞ ኢየሱስ ከይሁዳ ወደ ገሊላ መጥቶ ያደረገው ሁለተኛ ምልክት ነው።

ማብራሪያ

4:1-3 ኢየሱስ ከማጥመቅ ይልቅ መስበክን ይበልጥ አዘወተረ፤ መስበክም በላጭ ነበርና (1ቆሮ 1:17)። ደቀ መዛሙርቱን እንዲያጠምቁ በማድረግ አከበራቸው። እርሱ የምስጢራቱ ጥቅም በሚያከናውናቸው እጅ ላይ እንደማይመካ ያስተምረናል።

4:4-26 በሰማራውያንና በአይሁድ መካከል ታላቅ ጥላቻ ነበር። የክርስቶስ ከይሁዳ ወደ ገሊላ የሚያደርገው መንገድ በሰማርያ በኩል ያልፍ ነበር። ወደ ፈተና ስፍራዎች መግባት የለብንም፣ የግድ አስፈላጊ ሲሆንብን እንጂ። በዚያን ጊዜም በውስጣቸው መዘግየት ሳይሆን በፍጥነት ማለፍ አለብን። እዚህ ላይ ጌታችን ኢየሱስ በተጓዦች የተለመደ ድካም ውስጥ ሆኖ እናገኘዋለን። በዚህም እርሱ በእውነት ሰው እንደነበር እናያለን። ድካም ከኃጢአት ጋር ገባ፤ ስለዚህም ክርስቶስ ስለእኛ እርግማን በመሆን ለድካሙ ተገዛ። እንዲሁም እርሱ ድሀ ሰው ነበር፤ ጉዞዎቹን ሁሉ በእግሩ ይሄድ ነበር። ደክሞት በዚያም በጉድጓዱ ላይ ተቀመጠ፤ የሚያርፍበት አልጋ አልነበረውም። በጉዞ ደክመው የሚቀመጡ ሰዎች እንደሚቀመጡት እርሱም እንዲሁ ተቀመጠ። በእርግጥም በእንደዚህ ባሉ ነገሮች እንደ እግዚአብሔር ልጅ ለመሆን በፍጥነት መገዛት ይገባናል።

ክርስቶስ አንዲት ሴት ውኃ ጠየቃት። የራሱ ወገን በሰማራውያን ላይ የሚያሳየውን ቁጣ እርሱ ስላላሳየች ተገረመች። ከሁሉም ወገን የሆኑ ልከኛ ሰዎች የሚደነቁ ናቸው። ክርስቶስም አጋጣሚውን ተጠቅሞ መለኮታዊ ነገሮችን አስተማራት፤ ድንቁርናዋንና ኃጢአተኝነቷን፣ እንዲሁም አዳኝ እንደሚያስፈልጋት በማሳየትም ይህችን ሴት ወደ እርሱ መለሳት። በዚህ ሕያው ውኃ መንፈስ ማለት ነው። በዚህ ንጽጽር የመሲሑ በረከት በብሉይ ኪዳን ተስፋ ተሰጥቶበት ነበር። የመንፈስ ጸጋዎች እና መጽናናቱ፣ የራሷን ባሕርይና አስፈላጊነት የምታውቀውን የተጠማች ነፍስ ያረካሉ። ኢየሱስ በምሳሌ የተናገረውን እርሷ በጥሬው ወሰደችው። ክርስቶስ የያዕቆብ የውኃ ጉድጓድ ውኃ በጣም አጭር እርካታ እንደሰጠ አሳየ። ከማንኛውም የመጽናናት ውኃ ብንጠጣም፣ እንደገና እንጠማለን። ነገር ግን የመንፈስ ጸጋን እና የወንጌልን መጽናናት የሚካፈል ሁሉ ነፍሱን ሙሉ በሙሉ የሚያረካውን ፈጽሞ አይጎድልበትም። ሥጋዊ ልቦች ከሥጋዊ ዓላማዎች ከፍ ብለው አይመለከቱም። እርሷም እንዲህ አለች፡- ስጠኝ፣ ክርስቶስ ያቀረበውን የዘላለም ሕይወት እንዳገኝ ሳይሆን፣ ወደዚህ ውኃ ለመቅዳት እንዳልመጣ። ሥጋዊ አእምሮ የሕሊናን ነቀፋዎች ለማራቅና እንዳይሰርጹ ለማድረግ በጣም ብልህ ነው። ነገር ግን ጌታችን ኢየሱስ የሕሊናን ነቀፋ እንዴት አጥብቆ ወደ ልቧ እንዳመጣው! የአሁኑን የሕይወት ሁኔታዋንም በጽኑ ወቀሳት።

ሴቲቱም ክርስቶስ ነቢይ እንደሆነ አወቀች። የቃሉ ኃይል ልብን በመመርመርና የሕሊናን ምሥጢራዊ ነገሮችን በማሳመን ለመለኮታዊ ሥልጣን ማረጋገጫ ነው። ስለምንታገልባቸው ነገሮች ሁሉ ጊዜያዊ እንደሆኑ ስናስብ ክርክሮቻችንን ማቀዝቀዝ አለበት። የአምልኮው ዓላማ አሁንም ተመሳሳይ ሆኖ ይቀጥላል፤ እግዚአብሔር፣ እንደ አባት፤ ነገር ግን ስለ አምልኮ ቦታ ያሉ ሁሉም ልዩነቶች ይቆማሉ። ምክንያት በአምልኮ ስፍራዎቻችን ውስጥ ጨዋነትንና ምቹነትን እንድናስብ ያስተምረናል፤ ነገር ግን ሃይማኖት ለአንዱ ስፍራ ከሌላው በላይ፣ ከቅድስናና ከእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት አንፃር፣ ቅድሚያ አይሰጥም። አይሁድ በእርግጥ ትክክል ነበሩ።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6