የዮሐንስ ወንጌል 20

AMHNIVአማርኛ31 ጥቅሶች5:18 አዳምጥ
አዳምጥ 5:18 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን፣ በማለዳ ገና ጨለማ ሳለ፣ መግደላዊት ማርያም ወደ መቃብሩ ሄደች፤ ድንጋዩም ከመቃብሩ መግቢያ ተንከባሎ አየች።

2ስለዚህም ወደ ስምዖን ጴጥሮስና ኢየሱስ ይወደው ወደ ነበረው ሌላው ደቀ መዝሙር እየሮጠች መጥታ፣ “ጌታን ከመቃብር አውጥተው ወስደውታል፤ የት እንዳኖሩትም አናውቅም” አለቻቸው።

3“ከዚያም ጴጥሮስና ሌላው ደቀ መዝሙር ወጥተው ወደ መቃብሩ ሄዱ።

4ሁለቱም ይሮጡ ነበር፤ ሌላው ደቀ መዝሙርም ጴጥሮስን ቀድሞት ከመቃብሩ ደረሰ።

5ጐንበስ ብሎ ሲመለከት ከተልባ እግር የተሠራውን ከፈን በዚያው እንዳለ አየ፤ ወደ መቃብሩ ግን አልገባም።

6ይከተለው የነበረው ስምዖን ጴጥሮስ ደረሰና ወደ መቃብሩ ገባ፤ እርሱም ከተልባ እግር የተሠራውን ከፈን አየ፤

7እንዲሁም በኢየሱስ ራስ ላይ ተጠምጥሞ የነበረውን ጨርቅ አየ፤ ይህም ጨርቅ ከከፈኑ ተለይቶ እንደ ተጠቀለለ ነበር።

8ከዚያም አስቀድሞ ከመቃብሩ የደረሰው ሌላው ደቀ መዝሙር ወደ ውስጥ ገባ፤ አይቶም አመነ፤

9ይኸውም ኢየሱስ ከሙታን መነሣት እንዳለበት ገና ከመጽሐፍ ስላልተረዱ ነበር።

10ከዚያም በኋላ ደቀ መዛሙርቱ ተመልሰው ወደ የቤታቸው ሄዱ፤

11ማርያም ግን ከመቃብሩ ውጭ ቆማ ታለቅስ ነበር፤ እያለቀሰችም መቃብሩን ለማየት ጐንበስ አለች።

12የኢየሱስ ሥጋ በነበረበት ቦታ፣ ነጫጭ ልብስ የለበሱ ሁለት መላእክት አንዱ በራስጌ ሌላው በግርጌ ተቀምጠው አየች።

13እነርሱም፣ “አንቺ ሴት፤ ለምን ታለቅሻለሽ?” ብለው ጠየቋት። እርሷም፣ “ጌታዬን ወስደውታል፤ የት እንዳኖሩትም አላውቅም” አለች።

14ይህን ብላ ዘወር ስትል ኢየሱስ በዚያው ቆሞ አየች፤ ኢየሱስ መሆኑን ግን አላወቀችም።

15እርሱም፣ “አንቺ ሴት፤ ለምን ታለቅሻለሽ? ማንንስ ትፈልጊአለሽ?” አላት። እርሷም የአትክልቱ ቦታ ጠባቂ መስሎአት፣ “ጌታዬ፤ አንተ ወስደኸው ከሆነ፣ እባክህ እንድወስደው፣ የት እንዳኖርኸው ንገረኝ” አለችው።

16ኢየሱስም፣ “ማርያም” አላት። እርሷም፣ ወደ እርሱ ዘወር ብላ በአራማይክ ቋንቋ፣ “ረቡኒ” አለችው፤ ትርጒሙም “መምህር ሆይ” ማለት ነው።

17ኢየሱስም፣ “ገና ወደ አብ ስላላረግሁ፣ አትንኪኝ፤ ይልቁንስ ወደ ወንድሞቼ ሄደሽ፣ ‘ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ፣ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ ዐርጋለሁ’ ብሎአል ብለሽ ንገሪአቸው” አላት።

18መግደላዊት ማርያምም፣ ወደ ደቀ መዛሙርቱ መጥታ፣ “ጌታን እኮ አየሁት!” አለች፤ እርሱ ያላትንም ነገረቻቸው።

19በዚያኑ ዕለት፣ በሳምንቱ መጀመሪያ ቀን በምሽት፣ ደቀ መዛሙርቱ አይሁድን በመፍራት በሮቹን ቈልፈው ተሰብስበው ሳለ፣ ኢየሱስ መጣና በመካከላቸው ቆሞ፣ “ሰላም ለእናንተ ይሁን” አላቸው።

20ይህንም ብሎ እጆቹንና ጐኑን አሳያቸው፤ ደቀ መዛሙርትም ጌታን ባዩት ጊዜ እጅግ ደስ አላቸው።

21ኢየሱስም እንደ ገና፣ “ሰላም ለእናንተ ይሁን፤ አብ እኔን እንደ ላከኝ፣ እኔም እናንተን እልካችኋለሁ” አላቸው።

22ይህን ካለ በኋላም፣ እፍ አለባቸውና እንዲህ አላቸው፤ “መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ።

23የሰዎችን ኀጢአት ይቅር ብትሉ፣ ኀጢአታቸው ይቅር ይባልላቸዋል፤ ኀጢአታቸውን ይቅር ባትሉ ግን፣ ይቅር አይባልላቸውም።”

24በዚህ ጊዜ ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ የሆነው፣ ዲዲሞስ የተባለው ቶማስ፣ ኢየሱስ በመጣ ጊዜ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር አልነበረም።

25ሌሎች ደቀ መዛሙርትም፣ “ጌታን አየነው እኮ!” አሉት። እርሱ ግን፣ “በምስማር የተቸነከሩትን የእጆቹን ምልክቶች ካላየሁ፣ ምስማሮቹ በነበሩበት ቦታ ጣቴን ካላደረግሁ፣ በጐኑም እጄን ካላስገባሁ አላምንም” አለ።

26ከስምንት ቀን በኋላም፣ ደቀ መዛሙርቱ በቤት ውስጥ ነበሩ፤ ቶማስም ከእነርሱ ጋር ነበር፤ በሮቹ ተቈልፈው ነበር፤ ኢየሱስ ግን መጥቶ በመካከላቸው ቆመና፣ “ሰላም ለእናንተ ይሁን” አላቸው።

27ከዚያም ቶማስን፣ “ጣትህን ወደዚህ አምጣ፤ እጆቼንም ተመልከት፤ እጅህን ዘርጋና በጐኔ አስገባ፤ አትጠራጠር፤ እመን” አለው።

28ቶማስም፣ “ጌታዬ፤ አምላኬም!” አለው።

29ኢየሱስም፣ “አንተ ስላየኸኝ አምነሃል፤ ሳያዩ የሚያምኑ ግን ብፁዓን ናቸው” አለው።

30ኢየሱስ በዚህ መጽሐፍ ያልተጻፉ ሌሎች አያሌ ታምራዊ ምልክቶችን በደቀ መዛሙርቱ ፊት አድርጓል፤

31ነገር ግን ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ፣ የእግዚአብሔርም ልጅ እንደሆነ ታምኑ ዘንድ፣ አምናችሁም በስሙ ሕይወት እንዲኖራችሁ ይህ ተጽፎአል።

ማብራሪያ

20:1-10 ክርስቶስ ሕይወቱን ቤዛ አድርጎ ቢሰጥና እንደገና ባይወስዳት ኖሮ፣ መስጠቱ እንደ ካሳ ተቀባይነት እንዳገኘ መገለጥ ባልቻለም ነበር። ሥጋው በመጥፋቱ ለማርያም ታላቅ ፈተና ነበር። ደካማ አማኞች ብዙውን ጊዜ ቅሬታ የሚያቀርቡት፣ በእርግጥ የተስፋ መሰረትና የደስታ ምንጭ የሆነውን ነገር ነው። ከሌሎች ይልቅ በደቀመዝሙርነት መብቶች የከበሩት፣ በደቀመዝሙርነት ግዴታ ከሌሎች ይልቅ ንቁ ሲሆኑ፤ በጎ ሥራን ለመሥራት የበለጠ ጥረት ለማድረግና አደጋን ለመጋፈጥ ፈቃደኞች ሲሆኑ መልካም ነው። የቻልነውን ሁሉ ማድረግ አለብን፤ ከእኛ በተሻለ መሥራት የሚችሉትን ደግሞ አንቅና፤ ከኋላ የቀሩ ቢሆኑም፣ የቻሉትን ያህል የሚሠሩትን ደግሞ አንንቅ። ኢየሱስ በልዩ ሁኔታ የወደደውና በዚህም ምክንያት ኢየሱስን በልዩ ሁኔታ የወደደው ደቀ መዝሙር ቀዳሚ ነበር። የክርስቶስ ፍቅር ከሌላ ከማንኛውም ነገር በላይ በየግዴታችን እንድንበዛ ያደርገናል። ከኋላ የነበረው ክርስቶስን የካደው ጴጥሮስ ነበር። የጥፋተኝነት ስሜት በእግዚአብሔር አገልግሎት ያግደናል። እስከዚያን ጊዜ ድረስ ደቀ መዛሙርቱ ክርስቶስ ከሙታን መነሳት እንዳለበት ቅዱሳት መጻሕፍት እንደሚያስተምር አያውቁም ነበር።

ዮሐንስ 20:11-18

በፍቅር ስንፈልግ እና በእንባ ስንፈልግ መፈለግና ማግኘት እንችላለን። ነገር ግን ብዙ አማኞች በውስጣቸው ባለው ደመናና ጨለማ ያማርራሉ። እነዚህም ነፍሳቸውን የሚያዋርዱበት፣ ኃጢአታቸውን የሚገድሉበት እና ክርስቶስን በእነርሱ ዘንድ የሚያስወድዱበት የጸጋ መንገዶች ናቸው። የመላእክት እይታና ፈገግታቸው ብቻ፣ የኢየሱስን እይታ እና በእርሱ ያለውን የእግዚአብሔርን ፈገግታ ሳናይ በቂ አይደለም። በክርስቶስ የእግዚአብሔርን ፍቅር የሚያጽናና ማስረጃና የሰማይ ተስፋ የነበራት፣ አሁን ግን እነዚህን አጥታ በጨለማ የምትመላለስ የተተወች ነፍስ ሀዘንን የሞከሩት እንጂ ማንም አያውቅም። እንዲህ ያለ የቆሰለ መንፈስ ማን ሊሸከም ይችላል? ክርስቶስ ራሱን ለሚሹት ሰዎች ሲገልጥላቸው፣ ብዙ ጊዜ ከጠበቁት በላይ ያደርጋል። የማርያም ልብ ኢየሱስን ለማግኘት ምን ያህል በቅንነት እንደተነሳሳ ተመልከቱ። ክርስቶስ ራሱን ለሕዝቡ የሚገልጥበት መንገድ በቃሉ ነው። ቃሉን በነፍሳቸው ላይ በማዋል፣ በተለየ መንገድ ሲናገር ነው። ‹ጌታዬ ነውን?› ተብሎ ሊነበብ ይችላል። ኢየሱስን የሚወዱ ሰዎች በእርሱ ሥልጣን ስር ስለመሆናቸው በምን ያህል ደስታ እንደሚናገሩ ተመልከቱ። ከአሁን ባለው ሁኔታ በላይ የሆነ ነገርን በእርሱ ሥጋዊ መገኘት እንዳትጠብቅ ከለከላት። ከክርስቶስ ጋር ባለን አንድነት ከእግዚአብሔር ጋር ያለውን ግንኙነት አስተውሉ። እኛ መለኮታዊ ባህሪን ስለተካፈልን የክርስቶስ አባት አባታችን ነው። እርሱም የሰውን ባህሪ ስለተካፈለ፣ አምላካችን የእርሱ አምላክ ነው። ክርስቶስ ወደ ሰማይ ማረጉ፣ በዚያም ለእኛ ሊያማልድ፣ እንዲሁ የማይነገር መጽናናት ነው። ይህች ምድር ቤታቸውና ማረፊያቸው እንደሆነች አድርገው እንዳያስቡ። ዓይናቸውና ግባቸው፣ ጥልቅ ምኞታቸውም በሌላው ዓለም ላይ ሊሆን ይገባል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG ከሳምንቱም በፊተኛው ቀን መግደላዊት ማርያም ገና ጨለማ ሳለ ማለዳ ወደ መቃብር መጣች ድንጋዩም ከመቃብሩ ተፈንቅሎ አየች። አማርኛ ENGNIV Early on the first day of the week, while it was still dark, Mary Magdalene went to the tomb and saw that the stone had… English BCV በታ ቐዳመይቲ መዓልቲ ሰሙን፥(ሀ) ማርያም መግደላዊት፥ ገና ፀልማት እንተሎ፥ ኣንጊሃ ናብቲ መቓብር መፀት። እቲ እምኒ ኸዓ፥ ካብ ኣፍ መቓብር ተፈንቂሉ ረአየቶ። ትግርኛ GAZBIB Guyyaa jalqaba torbaniitti, [gaafa Sanbata guddaa,] utuu dukkanaa'uutti jiruu obboroodhaan, Maariyaam isheen Magdalaa g… Afaan Oromoo BCV GIZ ወበእሑድ ሰንበት መጽአት ማርያም መግደላዊት በጽባሕ ኀበ መቃብር እንዘ ዓዲሁ ጽልመት ወረከበት እብነ እቱተ እምአፈ መቃብር። giz GAZGAZ Guyyaa jalqaba torbaniitti, [gaafa Sanbata guddaa,] utuu dukkanaa'uutti jiruu obboroodhaan, Maariyaam isheen Magdalaa g… Afaan Oromoo BCV aksum በታ ቐዳመይቲ መዓልቲ ሰሙን፥(ሀ) ማርያም መግደላዊት፥ ገና ፀልማት እንተሎ፥ ኣንጊሃ ናብቲ መቓብር መፀት። እቲ እምኒ ኸዓ፥ ካብ ኣፍ መቓብር ተፈንቂሉ ረአየቶ። ትግርኛ SWAHSUV Hata siku ya kwanza ya juma Mariamu Magdalene alikwenda kaburini alfajiri, kungali giza bado; akaliona lile jiwe limeon… Kiswahili