ትንቢተ ኤርምያስ 5

AMHEVGአማርኛ31 ጥቅሶች5:50 አዳምጥ
አዳምጥ 5:50 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1በኢየሩሳሌም መንገድ እየተመላለሳችሁ ሩጡ፥ ተመልከቱም፥ እወቁም፥ በአደባባይዋም ፈልጉ፤ ፍርድን የሚያደርገውን እውነትንም የሚሻውን ሰው ታገኙ እንደሆነ ይቅር እላታለሁ።

2እነርሱም፦ ሕያው እግዚአብሔርን! ቢሉ፥ የሚምሉት በሐሰት ነው።

3አቤቱ፥ ዓይንህ እውነትን የምትመለከት አይደለችምን? አንተ ቀሥፈሃቸዋል ነገር ግን አላዘኑም፥ ቀጥቅጠሃቸውማል ነገር ግን ተግሣጽን እንቢ አሉ፤ ፊታቸውን ከድንጋይ ይልቅ አጠንክረዋል፤ ይመለሱ ዘንድ እንቢ አሉ።

4እኔም፦ የእግዚአብሔርን መንገድና የአምላካቸውን ሕግ አላወቁምና እነዚህ በእውነት ድሆችና ሰነፎች ናቸው፤

5ወደ ታላላቆቹ እሄዳለሁ እናገራቸውማለሁ፤ የእግዚአብሔርን መንገንድና የአምላካቸውን ሕግ ያውቃሉና፡ አልሁ። እነዚህ ግን ቀንበሩን በአንድነት ሰብረዋል፥ እስራቱንም ቈርጠዋል።

6ስለዚህ ኃጢአታቸው በዝቶአልና፥ የክዳታቸውም ብዛት ጸንቶአልና ስለዚህ አንበሳ ከዱር ወጥቶ ይሰብራቸዋል፥ የበረሀም ተኵላ ያጠፋቸዋል፥ ነብርም በከተሞቻቸው ላይ ይተጋል፥ ከዚያም የሚወጣ ሁሉ ይነጠቃል።

7በእነዚህ ነገሮች ይቅር የምልሽ እንዴት አድርጌ ነው? ልጆችሽ ትተውኛል አማልክትም ባልሆኑ ምለዋል፤ ካጠገብኋቸውም በኋላ አመነዘሩ በጋለሞቶቹም ቤት ተሰበሰቡ።

8እንደ ተቀለቡ ፈረሶች ሆኑ፤ እያንዳንዳቸውም ከባልንጀሮቻቸው ሚስቶች ኋላ አሽካኩ።

9በውኑ ስለ እነዚህ ነገሮች አልቀሥፍምን? ይላል እግዚአብሔር፤ ነፍሴስ እንደዚህ ባለ ሕዝብ ላይ አትበቀልምን?

10ወደ ቅጥርዋ ወጥታችሁ አፍርሱ፥ ነገር ግን ፈጽማችሁ አታጥፉ፤ ለእግዚአብሔር አይደሉምና ቅርንጫፍዋን ውሰዱ።

11የእስራኤል ቤትና የይሁዳ ቤት በእኔ ላይ እጅግ ወንጅለዋል ይላል እግዚአብሔር።

12እነርሱም፦ እርሱ አይደለም፥ ክፉ ነገርም አይመጣብንም ሰይፍንና ራብንም አናይም፤ ነቢያትም ነፋስ ይሆናሉ፥

13የእግዚአብሔርም ቃል በእነርሱ ዘንድ የለም፥ እንዲህም ይደረግባቸዋል፡ ብለው እግዚአብሔርን ክደዋል።

14ስለዚህም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዚህ ቃል ተናግራችኋልና እነሆ፥ በአፍህ ውስጥ ቃሌን እሳት ይህንም ሕዝብ እንጨት አደርጋለሁ፥ ትበላቸውማለች።

15የእስራኤል ቤት ሆይ፥ እነሆ፥ ሕዝብን ከሩቅ አመጣባችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ኃያል ጥንታዊ ሕዝብ ነው፥ ቋንቋቸውንም የማታውቀው የሚናገሩትንም የማታስተውለው ሕዝብ ነው።

16የፍላጻቸውም ሰገባ እንደ ተከፈተ መቃብር ነው፥ ሁሉም ኃያላን ናቸው።

17መከርህንና እንጀራህን ይበላሉ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህንም ይበሉአቸዋል፤ በጎችህንና ላሞችህንም ይበላሉ፤ ወይንህንና በለስህንም ይበላሉ፤ የምትታመናቸውን የተመሸጉ ከተሞችን በሰይፍ ይደበድባሉ።

18ነገር ግን በዚያ ዘመን፥ ይላል እግዚአብሔር፥ ፈጽሜ አላጠፋችሁም።

19እንዲህም ይሆናል፤ እናንተ፦ አምላካችን እግዚአብሔር ይህን ነገር ሁሉ ስለምን አደረገብን? ብትሉ፥ አንተ፦ እንደ ተዋችሁኝ በአገራችሁም ሌሎችን አማልክት እንዳመለካችሁ፥ እንዲሁ ለእናንተ ባልሆነ አገር ለሌሎች ሰዎች ትገዛላችሁ፡ ትላቸዋለህ።

20ይህን በያዕቆብ ቤት አውሩ፥ በይሁዳም አሰሙ፦

21እናንተ ሰነፎች ልበ ቢሶች፥ ዓይን እያላችሁ የማታዩ፥ ጆሮም እያላችሁ የማትሰሙ ሕዝብ ሆይ፥ ይህን ስሙ።

22በውኑ እኔን አትፈሩምን? ከፊቴስ አትደነግጡምን? ይላል እግዚአብሔር፤ እንዳያልፍ አሸዋን በዘላለም ትእዛዝ ለባሕር ዳርቻ አድርጌአለሁ፤ ሞገዱም ቢናወጥ አያሸንፍም፥ ቢጮኽም አያልፍበትም።

23ለዚህ ሕዝብ ግን የሸፈተና ያመፀ ልብ አላቸው፤ ዐምፀዋል ሄደውማል።

24በልባቸውም፦ የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ በጊዜው የሚሰጠውን፥ ለመከርም የተመደቡትን ወራት የሚጠብቅልንን አምላካችንን እግዚአብሔርን እንፍራ፡ አላሉም።

25በደላችሁ እነዚህን አስቀርታለች፥ ኃጢአታችሁም መልካምን ነገር ከለከለቻችሁ።

26በሕዝቤ መካከል ክፉዎች ሰዎች ተገኝተዋል፤ እንደ አጥማጆችም ያደባሉ፥ ወጥመድንም ይዘረጋሉ ሰዎችንም ያጠምዳሉ።

27ቀፎ ወፎችን እንደሚሞላ፥ እንዲሁ ቤታቸው ሽንገላን ሞልታለች፤ እንዲሁም ከብረዋል ባለ ጠጎችም ሆነዋል።

28ወፍረዋል ሰብተውማል፥ ክፋታቸውንም ያለ ልክ አብዝተዋል፤ የድሀ አደጎች ነገር መልካም እንዲሆን አልተምዋገቱላቸውም፥ የችግረኞችንም ፍርድ አልፈረዱላቸውም።

29በውኑ ስለ እነዚህ ነገሮች አልቀሥፍምን? ይላል እግዚአብሔር፤ ነፍሴስ እንደዚህ ባለ ሕዝብ ላይ አትበቀልምን?

30የምታስደንቅና የምታስደነግጥ ነገር በምድር ላይ ሆናለች፤

31ነቢያት በሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፥ ካህናትም በእነዚህ እጅ ይገዛሉ፥ ሕዝቤም እንዲህ ያለውን ነገር ይወድዳሉ፤ በፍጻሜውስ ምን ታደርጋላችሁ?

ማብራሪያ

5:1-9 እንደ ቅንና እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው የሚመላለስ ማንም ሊገኝ አልቻለም። ነገር ግን ጌታ ሁሉንም አስመሳይነታቸውን አልፎ የሰዎችን እውነተኛ ባሕርይ አየ። ድሆቹ አላዋቂዎች ነበሩ፣ ስለዚህም ክፉዎች ነበሩ። ስለ እግዚአብሔርና ስለ ሃይማኖት ምንም ከማያውቁ ሰዎች ከጨለማ ሥራዎች ሌላ ምን ይጠበቃል? የእግዚአብሔር ድሆች አሉ፤ እነዚህም ድህነት ቢኖርባቸውም የጌታን መንገድ ያውቃሉ፣ በእርሱም ይጓዛሉ፣ ግዴታቸውንም ይፈጽማሉ። ነገር ግን እነዚህ በገዛ ፈቃዳቸው አላዋቂዎች ነበሩ፣ አለማወቃቸውም ሰበብ አይሆናቸውም። ባለጠጎቹ እብሪተኞችና ትዕቢተኞች ነበሩ፤ የእግዚአብሔርን በጎነት አላግባብ መጠቀማቸውም ኃጢአታቸውን ይበልጥ አባባሰው።

5:10-18 ብዙዎች እግዚአብሔር ቃሉ እንደሚለው ጥብቅ እንደማይሆን በማመን ይጠፋሉ፤ በዚህ ተንኮል ሰይጣን የሰውን ዘር አጠፋ። ኃጢአተኞች ከኃጢአታቸው የሚለያቸውን ወይም በኃጢአታቸው የሚያስጨንቃቸውን ነገር የእግዚአብሔር ቃል እንደሆነ ለመቀበል ፍቃደኞች አይደሉም። የጌታን መልእክተኞች መሳደብና አላግባብ መጠቀም የክፋታቸውን መጠን ሞላ።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV “Go up and down the streets of Jerusalem, look around and consider, search through her squares. If you can find but one… English BCV ኣብ መንገድታት ኢየሩሳሌም ዙሩሞ፥ ረአዩን ተመልከቱን፤ ኣብ ዕዳጋታታ ኸዓ ድለዩ፤ ሓደ፥ እወ ሓደ እኳ ፍትሒ ዝገብር፥ ሓቂ ኸዓ ዝደሊ እንተ ረኸብኩም፥ ኣነውን ክምሕራ እየ። ትግርኛ GAZBIB Karaa mandara Yerusaalem irra asii fi achi adeemaatii hubadhaatii ilaalaa! Karaa ishee isa guddaa irras adeemaatii barb… Afaan Oromoo BCV GIZ ሩጹ ውስተ ፍናዊሃ ለኢየሩሳሌም ወርእዩ ወአእምሩ፡ ወኀሡ ውስት መርኅባ እመቦ ዘይገብር ፍትሐ ወየኃሥሥ ጽድቀ። giz GAZGAZ Karaa mandara Yerusaalem irra asii fi achi adeemaatii hubadhaatii ilaalaa! Karaa ishee isa guddaa irras adeemaatii barb… Afaan Oromoo BCV aksum ኣብ መንገድታት ኢየሩሳሌም ዙሩሞ፥ ረአዩን ተመልከቱን፤ ኣብ ዕዳጋታታ ኸዓ ድለዩ፤ ሓደ፥ እወ ሓደ እኳ ፍትሒ ዝገብር፥ ሓቂ ኸዓ ዝደሊ እንተ ረኸብኩም፥ ኣነውን ክምሕራ እየ። ትግርኛ AMHNIV “በኢየሩሳሌም መንገዶች እስቲ ውጡ፤ ወደ ላይ ወደታችም ውረዱ፤ ዙሪያውን ተመልከቱ ቃኙ፤ በአደባባይዋም ፈልጉ፤ እውነትን የሚሻና በቅንነት የሚሄድ፣ አንድ ሰው እንኳ ብታገኙ፣ እኔ ይህቺን ከ… አማርኛ SWAHSUV Pigeni mbio huku na huku katika njia za Yerusalemu, mkaone sasa, na kujua, na kutafuta katika viwanja vyake, kwamba mwa… Kiswahili