ትንቢተ ኤርምያስ 5

AMHNIVአማርኛ31 ጥቅሶች6:39 አዳምጥ
አዳምጥ 6:39 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1“በኢየሩሳሌም መንገዶች እስቲ ውጡ፤ ወደ ላይ ወደታችም ውረዱ፤ ዙሪያውን ተመልከቱ ቃኙ፤ በአደባባይዋም ፈልጉ፤ እውነትን የሚሻና በቅንነት የሚሄድ፣ አንድ ሰው እንኳ ብታገኙ፣ እኔ ይህቺን ከተማ እምራታለሁ።

2‘ሕያው እግዚአብሔርን! ቢሉም፣ የሚምሉት በሐሰት ነው።”

3እግዚአብሔር ሆይ፤ ዐይኖችህ እውነትን አይመለከቱምን? አንተ መታሃቸው፤ እነርሱ ግን አልተሰማቸውም፤ አደቀቅሃቸው፤ እነርሱ ግን አልታረሙም፤ ፊታቸውን ከድንጋይ ይልቅ አጠነከሩ በንስሓ ለመመለስም አልፈለጉም።

4እኔም በልቤ እንዲህ አልሁ፤ “እነዚህ ድኾች ናቸው፤ ሞኞች ናቸው፤ የእግዚአብሔርን መንገድ፣ የአምላካቸውን ሕግ አላወቁምና።

5ስለዚህ ወደ ታላላቆቹ እሄዳለሁ፤ ለእነርሱም እናገራለሁ፤ በእርግጥ እነርሱ የእግዚአብሔርን መንገድ፣ የአምላካቸውንም ሕግ ያውቃሉና።” ነገር ግን እነርሱም ቢሆኑ ያው እንደዚያው ቀንበሩን ሰብረዋል፤ እስራቱንም በጥሰዋል።

6ስለዚህ አንበሳ ከዱር ወጥቶ ይሰባብራቸዋል፣ የበረሓ ተኵላም ይቦጫጭቃቸዋል፤ ብቅ የሚለውን ሰው ሁሉ ለመገነጣጠል፣ ነብር በከተሞቻቸው ዙሪያ ያደባል፤ ዐመፃቸው ታላቅ፣ ክሕደታቸው ብዙ ነውና።

7“ታዲያ፣ እንዴት ይቅር ልልሽ እችላለሁ? ልጆችሽ ትተውኛል፤ እውነተኛውን አምላክ ትተው አማልክት ባልሆኑት ምለዋል፤ እስኪጠግቡ ድረስ መገብኋቸው፤ እነርሱ ግን አመነዘሩ፤ ወደ ጋለሞቶችም ቤት ተንጋጉ።

8እንደ ተቀለበ ብርቱ ድንጒላ ፈረስ ሆኑ፤ እያንዳንዱም የሌላውን ሚስት ተከትሎ አሽካካ።

9ስለ እነዚህ ነገሮች አልቀጣቸውምን?” ይላል እግዚአብሔር። “እኔ ራሴ እንደዚህ ዐይነቱን ሕዝብ፣ አልበቀልምን?

10“ወደ ወይን አትክልቷ ስፍራ ገብታችሁ አበላሹት፤ ነገር ግን ፈጽማችሁ አታጥፉት፤ ቅርንጫፎቿን ገነጣጥሉ፤ የእግዚአብሔር አይደሉምና፤

11የእስራኤል ቤትና የይሁዳ ቤት፣ ፈጽመው ከድተውኛል፤” ይላል እግዚአብሔር።

12በእግዚአብሔር ላይ ሐሰትን ተናገሩ፤ እንዲህም አሉ፤ “እሱ ምንም አያደርግም! ክፉ ነገር አይደርስብንም፤ ሰይፍም ራብም አናይም፤

13ነቢያቱ ነፋስ እንጂ ሌላ ነገር አይደሉም፤ ቃሉም በውስጣቸው የለም፤ ያሉት ሁሉ በእነርሱ ላይ ይመለስ።”

14ስለዚህ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ሕዝቡ ይህን ቃል ስለ ተናገረ፣ ቃሌን በአፍህ ውስጥ የሚፋጅ እሳት፣ ይህንም ሕዝብ ማገዶ አደርጋለሁ፤ እሳቱም ይበላቸዋል።

15የእስራኤል ቤት ሆይ፣” ይላል እግዚአብሔር፤ “ከሩቅ ሕዝብን አመጣባችኋለሁ፤ ጥንታዊና ብርቱ፣ ቋንቋውን የማታውቁት፣ ንግግሩንም የማትረዱት ሕዝብ ነው።

16የፍላጻቸው ሰገባ እንደ ተከፈተ መቃብር ነው፤ ሁሉም ብርቱ ተዋጊዎች ናቸው።

17ሰብልህንና ምግብህን ጠራርገው ይበሉብሃል፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህን ይውጣሉ፣ በጎችህንና ከብቶችህን ይፈጃሉ፤ የወይን ተክሎችህንና የበለስ ዛፎችህን ያወድማሉ፤ የታመንህባቸውንም የተመሸጉ ከተሞች፣ በሰይፍ ያጠፉአቸዋል።

18“ይሁን እንጂ፣ በዚያን ዘመን እንኳ” ይላል እግዚአብሔር፤ “ፈጽሜ አላጠፋችሁም።

19ሕዝቡ፣ ‘እግዚአብሔር አምላካችን ይህን ሁሉ ነገር ለምን አደረገብን?’ ብለው ቢጠይቁ ‘እኔን፣ እንደ ተዋችሁኝና በራሳችሁ ምድር ባዕዳን አማልክትን እንዳገለገላችሁ፣ እንደዚሁ የእናንተ ባልሆነ ምድር ባዕዳንን ታገለግላላችሁ’ ትላቸዋለህ።

20“በያዕቆብ ቤት ይህን አሰሙ፣ በይሁዳም እንዲህ ብላችሁ ዐውጁ፤

21እናንት ዐይን እያላችሁ የማታዩ፣ ጆሮ እያላችሁ የማትሰሙ፣ ሞኞችና የማታስተውሉ ሰዎች ይህን ስሙ፤

22ልትፈሩኝ አይገባችሁምን?” ይላል እግዚአብሔር፤ “በእኔ ፊት ልትንቀጠቀጡስ አይገባምን? ለዘላለም ዐልፎት መሄድ እንዳይችል፣ አሸዋን ለባሕር ድንበር አደረግሁ፤ ማዕበሉ እየጋለበ ቢመጣ ከዚያ አያልፍም፤ ሞገዱ ቢጮኽም ሊያቋርጠው አይችልም።

23ይህ ሕዝብ ግን የሸፈተና እልከኛ ልብ አለው፤ መንገድ ለቆ ሄዶአል፤

24በልባቸውም፣ ‘የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ በጊዜው የሚያዘንበውን፣ መከርን በወቅቱ የሚያመጣልንን፣ አምላካችንን እግዚአብሔርን እንፍራ’ አላሉም።

25በደላችሁ እነዚህን አስቀርቶባችኋል። ኀጢአታችሁ መልካሙን ነገር ከልክሎአችኋል።

26“በሕዝቤ መካከል ክፉ ሰዎች አሉና፤ ወፍ እንደሚያጠምዱ ሰዎች፣ ወጥመድ ዘርግተው ሰው እንደሚይዙ ሰዎችም ያደባሉ።

27ወፎች እንደሞሉት ጐጆ፣ ቤታቸው በማጭበርበር የተሞላ ነው፤ ባለጠጎችና ኀያላን ሆነዋል፤

28ወፍረዋል፤ ሰብተዋልም። ክፋታቸው ገደብ የለውም፤ ወላጅ የሌላቸው ፍትሕ እንዲያገኙ አልቆሙላቸውም፤ ለድኾችም መብት አልተከራከሩም።

29ስለ እነዚህ ነገሮች ልቀጣቸው አይገባኝምን?” ይላል እግዚአብሔር። እንዲህ ዐይነቶቹን ሕዝብ፣ እኔ ራሴ ልበቀላቸው አይገባኝምን?

30“የሚያስፈራና የሚያስደነግጥ ነገር፣ በምድሪቱ ላይ ሆኖአል፤

31ነቢያት በሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፤ ካህናት በነቢያቱ ምክር ያስተዳድራሉ፤ ሕዝቤም እንዲህ ያለውን ይወዳሉ፤ ፍጻሜው ሲደርስ ግን ምን ታደርጉ ይሆን?

ማብራሪያ

5:1-9 እንደ ቅንና እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው የሚመላለስ ማንም ሊገኝ አልቻለም። ነገር ግን ጌታ ሁሉንም አስመሳይነታቸውን አልፎ የሰዎችን እውነተኛ ባሕርይ አየ። ድሆቹ አላዋቂዎች ነበሩ፣ ስለዚህም ክፉዎች ነበሩ። ስለ እግዚአብሔርና ስለ ሃይማኖት ምንም ከማያውቁ ሰዎች ከጨለማ ሥራዎች ሌላ ምን ይጠበቃል? የእግዚአብሔር ድሆች አሉ፤ እነዚህም ድህነት ቢኖርባቸውም የጌታን መንገድ ያውቃሉ፣ በእርሱም ይጓዛሉ፣ ግዴታቸውንም ይፈጽማሉ። ነገር ግን እነዚህ በገዛ ፈቃዳቸው አላዋቂዎች ነበሩ፣ አለማወቃቸውም ሰበብ አይሆናቸውም። ባለጠጎቹ እብሪተኞችና ትዕቢተኞች ነበሩ፤ የእግዚአብሔርን በጎነት አላግባብ መጠቀማቸውም ኃጢአታቸውን ይበልጥ አባባሰው።

5:10-18 ብዙዎች እግዚአብሔር ቃሉ እንደሚለው ጥብቅ እንደማይሆን በማመን ይጠፋሉ፤ በዚህ ተንኮል ሰይጣን የሰውን ዘር አጠፋ። ኃጢአተኞች ከኃጢአታቸው የሚለያቸውን ወይም በኃጢአታቸው የሚያስጨንቃቸውን ነገር የእግዚአብሔር ቃል እንደሆነ ለመቀበል ፍቃደኞች አይደሉም። የጌታን መልእክተኞች መሳደብና አላግባብ መጠቀም የክፋታቸውን መጠን ሞላ።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG በኢየሩሳሌም መንገድ እየተመላለሳችሁ ሩጡ፥ ተመልከቱም፥ እወቁም፥ በአደባባይዋም ፈልጉ፤ ፍርድን የሚያደርገውን እውነትንም የሚሻውን ሰው ታገኙ እንደሆነ ይቅር እላታለሁ። አማርኛ ENGNIV “Go up and down the streets of Jerusalem, look around and consider, search through her squares. If you can find but one… English BCV ኣብ መንገድታት ኢየሩሳሌም ዙሩሞ፥ ረአዩን ተመልከቱን፤ ኣብ ዕዳጋታታ ኸዓ ድለዩ፤ ሓደ፥ እወ ሓደ እኳ ፍትሒ ዝገብር፥ ሓቂ ኸዓ ዝደሊ እንተ ረኸብኩም፥ ኣነውን ክምሕራ እየ። ትግርኛ GAZBIB Karaa mandara Yerusaalem irra asii fi achi adeemaatii hubadhaatii ilaalaa! Karaa ishee isa guddaa irras adeemaatii barb… Afaan Oromoo BCV GIZ ሩጹ ውስተ ፍናዊሃ ለኢየሩሳሌም ወርእዩ ወአእምሩ፡ ወኀሡ ውስት መርኅባ እመቦ ዘይገብር ፍትሐ ወየኃሥሥ ጽድቀ። giz GAZGAZ Karaa mandara Yerusaalem irra asii fi achi adeemaatii hubadhaatii ilaalaa! Karaa ishee isa guddaa irras adeemaatii barb… Afaan Oromoo BCV aksum ኣብ መንገድታት ኢየሩሳሌም ዙሩሞ፥ ረአዩን ተመልከቱን፤ ኣብ ዕዳጋታታ ኸዓ ድለዩ፤ ሓደ፥ እወ ሓደ እኳ ፍትሒ ዝገብር፥ ሓቂ ኸዓ ዝደሊ እንተ ረኸብኩም፥ ኣነውን ክምሕራ እየ። ትግርኛ SWAHSUV Pigeni mbio huku na huku katika njia za Yerusalemu, mkaone sasa, na kujua, na kutafuta katika viwanja vyake, kwamba mwa… Kiswahili