ትንቢተ ኤርምያስ 44

AMHNIVአማርኛ30 ጥቅሶች7:47 አዳምጥ
አዳምጥ 7:47 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1በግብፅ ሰሜናዊ ክፍል በሚግዶል፣ በጣፍናስና በሜምፎስ እንዲሁም በግብፅ ደቡባዊ ክፍል ስለሚኖሩት የአይሁድ ሕዝብ እንዲህ የሚል ቃል ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ መጣ፤

2“የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ከተሞች ሁሉ ላይ ያመጣሁትን ታላቅ ጥፋት አይታችኋል፤ ዛሬ ማንም የማይኖርባቸው ባድማ ሆነው ይታያሉ፤

3ይህም የሆነው ስላደረጉት ክፋት ነው። እነርሱም ሆኑ እናንተ ወይም አባቶቻችሁ ላላወቋቸው ለሌሎች አማልክት በማጠንና በማምለክ አስቈጥተውኛል።

4እኔም፣ ‘ይህን የምጠላውን አስጸያፊ ነገር አታድርጉ’ በማለት አገልጋዮቼን ነቢያትን ደጋግሜ ላክሁባቸው።

5እነርሱ ግን አልሰሙም፤ ልብም አላሉም፤ ከክፋታቸው አልተመለሱም፤ ለሌሎችም አማልክት ማጠን አልተውም።

6ስለዚህ መዓቴና ቍጣዬ ፈሰሰ በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም መንገዶች ላይ ነደደ፤ ዛሬ እንደሚታ ዩትም ማንም የማይኖርባቸው ፍርስራሾች አደረጋቸው።

7“አሁንም የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ዘር እንዳይቀርላችሁ ወንዶችና ሴቶች፣ ልጆችና ሕፃናት በይሁዳ እንዳይገኙ ለምን እንዲህ ዐይነት ታላቅ ጥፋት በራሳችሁ ላይ ታመጣላችሁ?

8ልትኖሩባት በመጣችሁባት በግብፅ ምድር ለሌሎች አማልክት በማጠን፣ እጆቻችሁ ባበጇቸው ነገሮች ለምን ታስቈጡኛላችሁ? በምድር ባሉት ሕዝቦች ሁሉ ዘንድ የርግማንና የመዘባበቻ ምልክት ለመሆን ራሳችሁን ታጠፋላችሁን?

9በይሁዳ ምድርና በኢየሩሳሌም መንገዶች አባቶቻችሁ የይሁዳ ነገሥታትና ሚስቶቻቸው፣ እንዲሁም እናንተና ሚስቶቻችሁ ያደረጋችሁትን ክፋት ረስታችሁታልን?

10እስከ ዛሬ ድረስ ራሳቸውን ዝቅ በማድረግ ክብርን አልሰጡኝም፤ በእናንተና በአባቶቻችሁ ፊት ያኖርሁትንም ሕጌንና ሥርዐቴን አልተከተሉም።’

11“ስለዚህ የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘በእናንተ ላይ ጥፋት ለማምጣትና ይሁዳን ሁሉ ለመደምሰስ ቈርጬ ተነሥቻለሁ።

12ሄደው በግብፅ ለመቀመጥ የወሰኑትን የይሁዳ ቅሬታዎች ሁሉ እነጥቃለሁ፤ ሁሉም ይጠፋሉ፤ በግብፅ ምድር በሰይፍ ይወድቃሉ፤ በራብ ያልቃሉ፤ ከትንሽ እስከ ትልቅ በሰይፍና በራብ ይሞታሉ፤ የመነቀፊያና የድንጋጤ፣ የመረገሚያና የመዘባበቻ ምልክት ይሆናሉ።

13ኢየሩሳሌምን እንደቀጣሁ፣ በግብፅ የሚኖሩትን በሰይፍ፣ በራብና በቸነፈር እቀጣለሁ፤

14ወደ ግብፅ የመጡት የይሁዳ ቅሬታዎች ወደ ይሁዳ ለመመለስ ቢመኙም ከጥቂት ስደተኞች በስተቀር አምልጦ ወይም ተርፎ ወደ ይሁዳ የሚመለስ አንድም ሰው አይኖርም።’ ”

15ሚስቶቻቸው ለሌሎች አማልክት ማጠናቸውን ያወቁ ወንዶች ሁሉና በዚያ የነበሩት ሴቶች ሁሉ ይህም ማለት በሰሜንና በደቡብ ግብፅ የሚኖረው ሕዝብ ሁሉ ታላቅ ጉባኤ ሆነው ለኤርምያስ እንዲህ አሉት፤

16“አንተ በእግዚአብሔር ስም የነገርኸንን መልእክት አንሰማም፤

17እናደርጋለን ያልነውን ሁሉ እናደርጋለን፤ አባቶቻችን፣ ነገሥታታችንና ባለሥልጣኖቻችን በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም መንገዶች እንዳደረጉት ሁሉ እኛም ለሰማይዋ ንግሥት እናጥናለን፤ የመጠጥ ቍርባን እናፈስላታለን። በዚያን ጊዜ የተትረፈረፈ ምግብ ነበረን፤ በመልካም ሁኔታ እንገኝ ነበር እንጂ ምንም ክፉ ነገር አልገጠመንም።

18ነገር ግን ለሰማይዋ ንግሥት ማጠንና የመጠጥ ቍርባን ማፍሰስ ከተውን ወዲህ፣ ሁሉን ነገር አጥተናል፤ በሰይፍና በራብም እያለቅን ነው።

19ሴቶቹም፣ “ለሰማይዋ ንግሥት በምናጥንበትና የመጠጥ ቍርባን በምናፈስበት ጊዜ፣ በምስሏ ዕንጐቻ ስንጋግርና የመጠጥ ቍርባን ስናፈስላት ባሎቻችን አያውቁም ነበርን?” አሉ።

20ኤርምያስ ይህን መልስ ለሰጠው ሕዝብ፣ ለወንዶችና ለሴቶች ሁሉ እንዲህ አለ፤

21“እናንተና አባቶቻችሁ፣ ነገሥታታችሁና ባለሥልጣኖቻችሁ እንዲሁም የምድሪቱ ሕዝብ በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም መንገዶች ያጠናችሁትን እግዚአብሔር የማያስታውሰውና የዘነጋው ይመስላችኋልን?

22እግዚአብሔር ክፉ አድራጎታችሁንና አስጸያፊ ተግባራችሁን ሊታገሥ ባለመቻሉ፣ ዛሬ እንደሆነው ምድራችሁ የርግማን ምልክት፣ ሰው የማይኖርበት ባዶ ምድረ በዳ ሆኖአል።

23ዕጣን በማጠን በእግዚአብሔር ላይ ኀጢአት ስለ ሠራችሁና ቃሉን ስላልጠበቃችሁ ሕጉን፣ ሥርዐቱንና ትእዛዙን ስላላከበራችሁ ዛሬ እንደምታዩት ጥፋት መጥቶባችኋል።”

24ኤርምያስም ለሕዝቡና ለሴቶቹ ሁሉ እንዲህ አለ፤ “በግብፅ የምትኖሩ የይሁዳ ሕዝብ ሁሉ፤ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ።

25የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ እናንተና ሚስቶቻችሁ፣ ‘ለሰማይዋ ንግሥት ለማጠንና የመጠጥ ቍርባን ለማፍሰስ የተሳልነውን ስእለታችንን በእርግጥ እንፈጽማለን’ ብላችሁ የገባችሁትን ቃል በተግባር አሳይታችኋል።’ “እንግዲያውስ ወደ ኋላ አትበሉ፤ ቃል የገባችሁትን፤ ስእለታችሁንም ፈጽሙ።

26በግብፅ የምትኖሩ አይሁድ ሁሉ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ ‘እግዚአብሔር እንዲህ ይላል “ከእንግዲህ ወዲህ በየትኛውም የግብፅ ክፍል የሚኖር ማንኛውም አይሁዳዊ፣ ‘ሕያው እግዚአብሔርን!’ ብሎ ስሜን እንዳይጠራ፣ እንዳይምልም በታላቁ ስሜ ምያለሁ፤

27ለመልካም ሳይሆን ለክፉ እተጋባቸዋለሁና፤ በግብፅ የሚኖሩ አይሁድ ፈጽሞ እስኪጠፉ ድረስ በሰይፍና በራብ ይደመሰሳሉ።

28ከሰይፍ አምልጠው፣ ከግብፅ ወደ ይሁዳ ምድር የሚመለሱት በጣም ጥቂት ሰዎች ይሆናሉ። በግብፅ ምድር ለመኖር የመጡት የይሁዳ ቅሬታ ሁሉ፣ ከእኔ ወይም ከእነርሱ የማንኛችን ቃል እንደሚጸና ያውቃሉ።

29“ ‘በእናንተ ላይ አመጣለሁ ያልሁትን ክፉ ነገር እንደሚፈጸም ታውቁ ዘንድ በዚህ ስፍራ እንደምቀጣችሁ ይህ ምልክት ይሁናችሁ’ ይላል እግዚአብሔር።

30እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ‘የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስን ሊገድለው ለፈለገው ጠላቱ ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደናፆር አሳልፌ እንደ ሰጠሁ፣ እንዲሁ የግብፅን ንጉሥ ፈርዖን ሖፍራን ሊገድሉት ለሚፈልጉ ጠላቶቹ አሳልፌ እሰጠዋለሁ።’ ”

ማብራሪያ

፵፬:፩-፲፬ እግዚአብሔር በይሁዳ ላይ ውድመትን ስላመጡት ኃጢአቶች አይሁድን ያስታውሳቸዋል። ሰዎችን ስለ ኃጢአት አደገኛነት በሙሉ ቁም ነገር ማስጠንቀቅ ይገባናል። 'ወይ! ይህን አታድርጉት!' ልንል ይገባል። እግዚአብሔርን የምትወዱ ከሆነ፣ እርሱን ያስቆጣዋልና አታድርጉት፤ የራሳችሁን ነፍሳት የምትወዱ ከሆነ ደግሞ፣ ያጠፋታልና አታድርጉት። በፈተና ሰዓት ሕሊናችን ይህንን ለእኛ ያድርግልን።

እግዚአብሔር ወደ ከለዳውያን ምድር የላካቸው አይሁድ እዚያ በእግዚአብሔር ጸጋ ኃይል ከጣዖት አምልኮ ተገፈፉ፤ ነገር ግን በገዛ ጠማማ ፈቃዳቸው ወደ ግብፅ ምድር የሄዱት፣ እዚያ ከምንጊዜውም በላይ ከጣዖት አምልኳቸው ጋር ይበልጥ ተጣበቁ። ምክንያት ሳይኖርብን ወይም ጥሪ ሳናገኝ ራሳችንን ወደ ፈተና ስፍራዎች ስንወረውር፣ እግዚአብሔር ለራሳችን ሊተወን ፍትሐዊ ነው። እኛ በእግዚአብሔር ላይ ብንሄድ እርሱም እኛ ላይ ይሄዳል። ሰዎች የሚጋለጡባቸው እጅግ አስከፊ መከራዎች የሚከሰቱት የቀረበውን ድነት ችላ በማለታቸው ነው።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG በግብፅ ምድር በሚግዶልና በጣፍናስ በሜምፎስም በጳትሮስም አገር ስለ ተቀመጡ አይሁድ ሁሉ ወደ ኤርምያስ የመጣ ቃል ይህ ነው። አማርኛ ENGNIV This word came to Jeremiah concerning all the Jews living in Lower Egypt–in Migdol, Tahpanhes and Memphis– and in Upper… English BCV እግዚኣብሄር ብዛዕባ እቶም ኣብ ሃገር ግብፂ ዝነበሩ፥ ብዛዕባ እቶም ኣብ ከተማታት ሚግዶል፥ ጣፍናስ፥ ሜምፎስ፥ ጳትሮስ ተቐሚጦም ዝነበሩ ኣይሁድ ናብ ኤርሚያስ ዝመፀ ቓል እዙይ እዩ፦ ትግርኛ GAZBIB Waa'ee Yihudoota warra biyya Gibxii keessa mandara Miigdol, Taahafenee, Nofii fi Phaaxros keessa jiraatan hundumaaf dub… Afaan Oromoo BCV GIZ ቃል ዘኮነ ኀበ ኤርምያስ እምኀበ እግዚአብሔር ከመ ይትነበይ ወኀበ ኵሎሙ አይሁድ እለ ይነብሩ ውስተ ግብፅ ወእለ ይነብሩ ውስተ ጣፍናስ ወመግደሎ ወውስተ ሜምፎስ ወውስተ ምድር ፋቱራ፤ giz GAZGAZ Waa'ee Yihudoota warra biyya Gibxii keessa mandara Miigdol, Taahafenee, Nofii fi Phaaxros keessa jiraatan hundumaaf dub… Afaan Oromoo BCV aksum እግዚኣብሄር ብዛዕባ እቶም ኣብ ሃገር ግብፂ ዝነበሩ፥ ብዛዕባ እቶም ኣብ ከተማታት ሚግዶል፥ ጣፍናስ፥ ሜምፎስ፥ ጳትሮስ ተቐሚጦም ዝነበሩ ኣይሁድ ናብ ኤርሚያስ ዝመፀ ቓል እዙይ እዩ፦ ትግርኛ SWAHSUV Neno lililomjia Yeremia, katika habari za Wayahudi wote waliokaa katika nchi ya Misri, waliokaa Migdoli, na Tahpanesi, … Kiswahili