ትንቢተ ኤርምያስ 41

AMHEVGአማርኛ18 ጥቅሶች3:59 አዳምጥ
አዳምጥ 3:59 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1በሰባተኛውም ወር ከመንግሥት ወገንና ከንጉሡ ዋና ዋና አለቆች አንዱ የኤሊሳማ ልጅ የናታንያ ልጅ እስማኤል ከአሥር ሰዎች ጋር ወደ ምጽጳ ወደ አኪቃም ልጅ ወደ ጎዶልያስ መጣ፤ በዚያም በምጽጳ በአንድ ላይ እንጀራ በሉ።

2የናታንያም ልጅ እስማኤል ከእርሱም ጋር የነበሩት አሥሩ ሰዎች ተነሥተው የሳፋንን ልጅ የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በሰይፍ መቱ፥ የባቢሎንም ንጉሥ በአገሩ ላይ የሾመውን ገደሉ።

3እስማኤልም ከጎዶልያስ ጋር በምጽጳ የነበሩትን አይሁድ ሁሉ፥ በዚያም የተገኙትን የከለዳውያንን ሰልፈኞች ሁሉ ገደላቸው።

4ጎዶልያስን ከገደለ በኋላ ማንም ሳያውቅ በሁለተኛው ቀን፥

5ጢማቸውን ላጭተው ልብሳቸውንም ቀድደው ገላቸውንም ነጭተው፥ ወደ እግዚአብሔር ቤት ያቀርቡ ዘንድ የእህል ቍርባንና ዕጣን በእጃቸው እየያዙ፥ ሰማንያ ሰዎች ከሴኬምና ከሴሎ ከሰማርያም መጡ።

6የናታንያም ልጅ እስማኤል ከምጽጳ ወጥቶ እያለቀሰ ሊገናኛቸው ሄደ፤ በተገናኛቸውም ጊዜ፦ ወደ አኪቃም ልጅ ወደ ጎዶልያስ ኑ፡ አላቸው።

7ወደ ከተማም መካከል በመጡ ጊዜ የናታንያ ልጅ እስማኤል ከእርሱም ጋር የነበሩ ሰዎች ገደሉአቸው፥ በጕድጓድም መካከል ጣሉአቸው።

8በመካከላቸውም እስማኤልን፦ በሜዳ የተሸሸገ ስንዴና ገብስ ዘይትና ማርም አለንና አትግደለን፡ የሚሉት አሥር ሰዎች ተገኙ። እርሱም ተዋቸው፥ ከወንድሞቻቸውም ጋር አልገደላቸውም።

9እስማኤልም ከጎዶልያስ ጋር የገደላቸውን የሰዎች ሬሳ ሁሉ የጣለበት ጕድጓድ ንጉሡ አሳ የእስራኤልን ንጉሥ ባኦስን ስለ ፈራ የሠራው ጕድጓድ ነበረ፤ የናታንያም ልጅ እስማኤል የገደላቸውን ሞላበት።

10እስማኤልም በምጽጳ የነበረውን የሕዝቡን ቅሬታ ሁሉ፥ የንጉሡን ሴቶች ልጆች የዘበኞቹም አለቃ ናቡዘረዳን ለአኪቃም ልጅ ለጎዶልያስ የሰጠውን በምጽጳ የቀሩትን ሕዝብ ሁሉ ማረካቸው፤ የናታንያም ልጅ እስማኤል ማርኮ ወደ አሞን ልጆች ይሄድ ዘንድ ተነሣ።

11የቃሬያም ልጅ ዮሐናን ከእርሱም ጋር የነበሩ የጭፍራ አለቆች ሁሉ የናታንያ ልጅ እስማኤል ያደረገውን ክፋት ሁሉ በሰሙ ጊዜ፥

12ሰዎቹን ሁሉ ይዘው ከናታንያ ልጅ ከእስማኤል ጋር ሊዋጉ ሄዱ፥ በገባዖንም ባለው በታላቁ ውኃ አጠገብ አገኙት።

13ከእስማኤልም ጋር የነበሩት ሕዝብ ሁሉ የቃሬያን ልጅ ዮሐናንን ከእርሱም ጋር የነበሩትን የጭፍራ አለቆችን ሁሉ ባዩ ጊዜ ደስ አላቸው።

14እስማኤልም ከምጽጳ የማረካቸው ሕዝብ ሁሉ ዘወር ብለው ተመለሱ፥ ወደ ቃሬያም ልጅ ወደ ዮሐናን ሄዱ።

15የናታንያ ልጅ እስማኤል ግን ከስምንት ሰዎች ጋር ከዮሐናን አመለጠ ወደ አሞንም ልጆች ሄደ።

16የቃሬያም ልጅ ዮሐናን ከእርሱም ጋር የነበሩት የጭፍራ አለቆች ሁሉ የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በምጽጳ ከገደለው በኋላ ከናታንያ ልጅ ከእስማኤል ያስመለሱአቸውን የሕዝቡን ቅሬታ ሁሉ፥ ከገባዖን ያስመለሱአቸውን ሰልፈኞች፥ ሴቶችንም፥ ልጆችንም፥ ጃንደረቦችንም፥ ወሰዱ፤

17ተነሥተውም ወደ ግብፅ ይሄዱ ዘንድ በቤተልሔም አጠገብ ባለው በጌሮት ከመዓም ተቀመጡ፤

18እስማኤል የባቢሎን ንጉሥ በአገሩ ላይ የሾመውን የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን ስለ ገደለው ከለዳውያንን ፈርተዋልና።

ማብራሪያ

፵፩:፩-፲ እግዚአብሔርን የሚያመልኩትን የሚጠሉ ሰዎች በቀላሉ ሊጎዷቸው እንዲችሉ ብዙውን ጊዜ የሃይማኖተኝነት መልክ ይይዛሉ። ሞት ብዙ ጊዜ ሰዎች ባልጠበቁት ስፍራ ስለሚያገኛቸው፣ በዳኛችን ፊት ለመቅረብ ስንጠራ ልንገኝበት በምንመኘው ዓይነት ሁኔታና የአእምሮ ዝግጅት ውስጥ መሆናችንን ዘወትር ልንመረምር ይገባናል። አንዳንድ ጊዜ የአንድ ሰው ሕይወት ቤዛ ሀብቱ ነው።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV In the seventh month Ishmael son of Nethaniah, the son of Elishama, who was of royal blood and had been one of the king… English BCV ኣብ ሻውዓይ ወርሒ ናይታ ዓመት፥ እቲ ኻብ ዘርኢ ንጉስን ካብ መኳንንቲ ንጉስን ዝነበረ እስማኤል፥ ወዲ ናታንያ ወዲ ኤሊሳማ፥ ዓሰርተ ሰብ ሒዙ ናብ ጎዶልያስ ወዲ ኣኪቃም ናብ ምፅጳ መፀ። ኣ… ትግርኛ GAZBIB Wagguma sana keessa ji'a torbaffaatti sanyii warra moototaa keessaa Ishmaa'el ilmi Nataaniyaa akaakayyuun Eliishaamaa a… Afaan Oromoo BCV GIZ ወኮነ በሳብዕ ወርኅ መጽአ እስማኤል ወልደ ናታንዩ ወልደ ኤልስማ እምዘመደ ነገሥት ወመገብተ ንጉሥ ወዓሠርቱ ሰብእ ምስሌሁ ኀበ ጎዶልያስ ወልደ አኪቃም በመሴፋ፤ ወበልዑ ህየ እያለ ኅቡረ በመ… giz GAZGAZ Wagguma sana keessa ji'a torbaffaatti sanyii warra moototaa keessaa Ishmaa'el ilmi Nataaniyaa akaakayyuun Eliishaamaa a… Afaan Oromoo BCV aksum ኣብ ሻውዓይ ወርሒ ናይታ ዓመት፥ እቲ ኻብ ዘርኢ ንጉስን ካብ መኳንንቲ ንጉስን ዝነበረ እስማኤል፥ ወዲ ናታንያ ወዲ ኤሊሳማ፥ ዓሰርተ ሰብ ሒዙ ናብ ጎዶልያስ ወዲ ኣኪቃም ናብ ምፅጳ መፀ። ኣ… ትግርኛ AMHNIV ከንጉሣዊ ቤተ ሰብ የሆነው ከንጉሡ የጦር መኰንንኖች አንዱ የነበረው የኤሊሳማ ልጅ የናታንያ ልጅ እስማኤል፣ በሰባተኛው ወር ከዐሥር ሰዎች ጋር ወደ ምጽጳ ወደ አኪቃም ልጅ ወደ ጎዶልያስ መጣ… አማርኛ SWAHSUV Basi ikawa katika mwezi wa saba, Ishmaeli, mwana wa Nethania, mwana wa Elishama, mmoja wa wazao wa kifalme, tena ni mmo… Kiswahili