ትንቢተ ኤርምያስ 41

AMHNIVአማርኛ18 ጥቅሶች4:30 አዳምጥ
አዳምጥ 4:30 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ከንጉሣዊ ቤተ ሰብ የሆነው ከንጉሡ የጦር መኰንንኖች አንዱ የነበረው የኤሊሳማ ልጅ የናታንያ ልጅ እስማኤል፣ በሰባተኛው ወር ከዐሥር ሰዎች ጋር ወደ ምጽጳ ወደ አኪቃም ልጅ ወደ ጎዶልያስ መጣ፣ በዚያም በአንድነት ሊበሉ በማእድ ተቀምጠው ሳለ፣

2የናታንያ ልጅ እስማኤልና አብረውት የነበሩ ዐሥሩ ሰዎች ተነሥተው፣ የባቢሎን ንጉሥ በምድሪቱ ላይ ገዥ አድርጎ የሾመውን የሳፋንን ልጅ የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በሰይፍ መቱት፤ ገደሉትም።

3ደግሞም እስማኤል በምጽጳ ከጎዶልያስ ጋር የነበሩትን አይሁድ ሁሉ፣ በዚያም የተገኙትን የባቢሎን ወታደሮች ገደላቸው።

4ጎዶልያስ በተገደለ ማግስት፣ ማንም ስለ ሁኔታው ከማወቁ በፊት፣

5ሰማንያ ሰዎች ጢማቸውን ተላጭተው፣ ልበሳቸውን ቀደው፣ ገላቸውን ነጭተው የእህል ቍርባንና ዕጣን በመያዝ ከሴኬም፣ ከሴሎና ከሰማርያ ወደ እግዚአብሔር ቤት ለማቅረብ መጡ።

6የናታንያ ልጅ እስማኤል ሊገናኛቸው እያለቀሰ ከምጽጳ ወጣ፣ ሲያገኛቸውም፣ “ወደ አኪቃም ልጅ ወደ ጎዶልያስ ኑቃ አላቸው።

7ወደ ከተማዪቱ በገቡ ጊዜ፣ የናታንያ ልጅ እስማኤልና አብረውት የነበሩ ሰዎች ዐረዷቸው፤ በውሃ ማጠራቀሚያ ጒድጓድ ውስጥም ጣሏቸው።

8ከተገደሉት ጋር የነበሩ ዐሥር ሰዎች ግን እስማኤልን፣ “እባክህ አትግደለን! በዕርሻችን ውስጥ የሸሸግነው ስንዴና ገብስ፣ የወይራ ዘይትና ማር ስላለን እባክህን አትግደለን” አሉት። እርሱም ተዋቸው፤ ከሌሎቹም ጋር አልገደላቸውም።

9እስማኤል ከጎዶልያስ በተጨማሪ የገደላቸው ሰዎች ሁሉ ሬሳ የተጣለበት የውሃ ማጠራቀሚያ ጒድጓድ ንጉሡ አሳ የእስራኤልን ንጉሥ ባኦስን ስለ ፈራ ለመከላከል ያሠራው ነበር፤ ይህን ጒድጓድ፤ የናታንያ ልጅ እስማኤል በሬሳ ሞላው።

10እስማኤል በምጽጳ የቀረውን ሕዝብ ሁሉ ምርኮኛ አደረገ፤ እነርሱም የባቢሎን የክብር ዘበኞች አዛዥ ናቡዘረዳን የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በላያቸው ገዥ አድርጎ የሾመባቸው የንጉሡ ሴቶች ልጆችና በዚያ የቀሩት ሌሎች ሰዎች ሁሉ ነበሩ። የናታንያ ልጅ እስማኤል እነዚህን ማርኮ ወደ አሞናውያን ለመሻገር ተነሣ።

11የቃሬያ ልጅ ዮሐናና ከእርሱ ጋር የነበሩት የጦር መኰንኖች ሁሉ የናታንያ ልጅ እስማኤል የፈጸመውን ግፍ ሁሉ በሰሙ ጊዜ፣

12የናታንያን ልጅ እስማኤልን ሊወጉ ሰዎቻቸውን ሁሉ ይዘው ሄዱ፤ በገባዖንም ባለው በታላቁ ኵሬ አጠገብ ደረሱበት።

13እስማኤል የያዛቸው ሰዎች ሁሉ የቃሬያን ልጅ ዮሐናንንና አብረውት የነበሩትን የጦር መኰንኖች ባዩ ጊዜ ደስ አላቸው።

14እስማኤል ከምጽጳ ማርኮ የወሰዳቸው ሰዎች ሁሉ አምልጠው ወደ ቃሬያ ልጅ ወደ ዮሐናን ገቡ።

15የናታንያ ልጅ እስማኤል ግን አብረውት ከነበሩት ስምንት ሰዎች ጋር ከዮሐናን አመለጠ፤ ሸሽቶም ወደ አሞናውያን ገባ።

16የቃሬያ ልጅ ዮሐናንና ከእርሱ ጋር የነበሩት የጦር መኰንንኖች ሁሉ የናታንያ ልጅ እስማኤል የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን ከገደለ በኋላ፣ በምጽጳ ከማረካቸው የተረፉትን ሰዎች በማስመለስ ይዘው ሄዱ፤ እነዚህም፦ ወታደሮች፣ ሴቶች ሕፃናትና ከገባዖን ያመጧቸው የቤተ መንግሥት ባለ ሥልጣኖች ነበሩ።

17ከዚያም ተነሥተው ሄዱ፤ ወደ ግብፅም በማምራት በቤተልሔም አጠገብ ባለችው በጌሮት ከመዓም ዐረፉ፤

18ወደ ግብፅም የሄዱት ከባቢሎናውያን ለማምለጥ ነበር፤ ባቢሎናውያንንም የፈሩት የናታንያ ልጅ እስማኤል የባቢሎን ንጉሥ የምድሪቱ ገዥ አድርጎ የሾመውን የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በመግደሉ ነው።

ማብራሪያ

፵፩:፩-፲ እግዚአብሔርን የሚያመልኩትን የሚጠሉ ሰዎች በቀላሉ ሊጎዷቸው እንዲችሉ ብዙውን ጊዜ የሃይማኖተኝነት መልክ ይይዛሉ። ሞት ብዙ ጊዜ ሰዎች ባልጠበቁት ስፍራ ስለሚያገኛቸው፣ በዳኛችን ፊት ለመቅረብ ስንጠራ ልንገኝበት በምንመኘው ዓይነት ሁኔታና የአእምሮ ዝግጅት ውስጥ መሆናችንን ዘወትር ልንመረምር ይገባናል። አንዳንድ ጊዜ የአንድ ሰው ሕይወት ቤዛ ሀብቱ ነው።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG በሰባተኛውም ወር ከመንግሥት ወገንና ከንጉሡ ዋና ዋና አለቆች አንዱ የኤሊሳማ ልጅ የናታንያ ልጅ እስማኤል ከአሥር ሰዎች ጋር ወደ ምጽጳ ወደ አኪቃም ልጅ ወደ ጎዶልያስ መጣ፤ በዚያም በምጽጳ… አማርኛ ENGNIV In the seventh month Ishmael son of Nethaniah, the son of Elishama, who was of royal blood and had been one of the king… English BCV ኣብ ሻውዓይ ወርሒ ናይታ ዓመት፥ እቲ ኻብ ዘርኢ ንጉስን ካብ መኳንንቲ ንጉስን ዝነበረ እስማኤል፥ ወዲ ናታንያ ወዲ ኤሊሳማ፥ ዓሰርተ ሰብ ሒዙ ናብ ጎዶልያስ ወዲ ኣኪቃም ናብ ምፅጳ መፀ። ኣ… ትግርኛ GAZBIB Wagguma sana keessa ji'a torbaffaatti sanyii warra moototaa keessaa Ishmaa'el ilmi Nataaniyaa akaakayyuun Eliishaamaa a… Afaan Oromoo BCV GIZ ወኮነ በሳብዕ ወርኅ መጽአ እስማኤል ወልደ ናታንዩ ወልደ ኤልስማ እምዘመደ ነገሥት ወመገብተ ንጉሥ ወዓሠርቱ ሰብእ ምስሌሁ ኀበ ጎዶልያስ ወልደ አኪቃም በመሴፋ፤ ወበልዑ ህየ እያለ ኅቡረ በመ… giz GAZGAZ Wagguma sana keessa ji'a torbaffaatti sanyii warra moototaa keessaa Ishmaa'el ilmi Nataaniyaa akaakayyuun Eliishaamaa a… Afaan Oromoo BCV aksum ኣብ ሻውዓይ ወርሒ ናይታ ዓመት፥ እቲ ኻብ ዘርኢ ንጉስን ካብ መኳንንቲ ንጉስን ዝነበረ እስማኤል፥ ወዲ ናታንያ ወዲ ኤሊሳማ፥ ዓሰርተ ሰብ ሒዙ ናብ ጎዶልያስ ወዲ ኣኪቃም ናብ ምፅጳ መፀ። ኣ… ትግርኛ SWAHSUV Basi ikawa katika mwezi wa saba, Ishmaeli, mwana wa Nethania, mwana wa Elishama, mmoja wa wazao wa kifalme, tena ni mmo… Kiswahili