ትንቢተ ኤርምያስ 40

AMHNIVአማርኛ16 ጥቅሶች4:31 አዳምጥ
አዳምጥ 4:31 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1የክብር ዘበኞች አዛዥ ናቡዘረዳን ኤርምያስን ከኢየሩሳሌምና ከይሁዳ ወደ ባቢሎን በሚወስዱት ምርኮኞች ሁሉ መካከል በራማ በሰንሰለት ታስሮ ባገኘው ጊዜ አስፈታው፤ ከዚህ በኋላ የእግዚአብሔር ቃል ወደ ኤርምያስ መጣ።

2የዘበኞቹ አዛዥ ኤርምያስን ለብቻው ወስዶ፣ እንዲህ አለው፤ “አምላክህ እግዚአብሔር በዚህች ምድር ላይ ይህን ጥፋት ተናገረ፤

3አሁንም እግዚአብሔር አመጣው፤ እንደ ተናገረውም አደረገ። ይህ ሁሉ የሆነው እናንተ በእግዚአብሔር ላይ ኀጢአት ስለ ሠራችሁና እርሱን ስላልታዘዛችሁ ነው።

4እነሆ፤ ዛሬ የእጅህን ሰንሰለት ፈታሁልህ። ከፈለግህ ከእኔ ጋር ወደ ባቢሎንና፤ እኔም እንከባ ከብሃለሁ፤ ካልፈለግህ ግን አትምጣ። እነሆ፤ አገሪቱ ሁሉ በፊትህ ናት፤ ደስ ወዳሰኘህ ሂድ።”

5ኤርምያስ ገና መልስ ሳይሰጥ ናቡዘረዳን በመቀጠል፣ “የባቢሎን ንጉሥ በይሁዳ ከተሞች ላይ ወደ ሾመው ወደ ሳፋን ልጅ ወደ አኪቃም ልጅ ወደ ጎዶልያስ ተመለስ፤ ከእርሱም ጋር በሕዝቡ መካከል ተቀመጥ፤ ወይም ደስ ወዳሰኘህ ስፍራ ሂድ” አለው። የዘበኞቹ አዛዥ ስንቅና ስጦታ ሰጥቶ አሰናበተው፤

6ኤርምያስም የአኪቃም ልጅ ጎዶልያስ ወዳለበት ወደ ምጽጳ ሄደ፤ ከእርሱም ጋር በምድሪቱ በቀረው ሕዝብ መካከል ኖረ።

7በየሜዳው የነበሩት የጦር መኰንኖችና ሰዎቻቸው ሁሉ የባቢሎን ንጉሥ የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በምድሪቱ ላይ ገዥ አድርጎ እንደ ሾመውና ወደ ባቢሎን በምርኮ ባልተወሰዱት በምድሪቱ ድኾች ወንዶች፣ ሴቶችና ልጆች ላይ ሥልጣን እንደ ሰጠው በሰሙ ጊዜ፣

8ወደ ምጽጳ፣ ጎዶልያስ ዘንድ መጡ፤ የናታንያ ልጅ እስማኤል፣ የቃሬያ ልጆች ዮሐናንና ዮናታን፣ የተንሑት ልጅ ሠራያ፤ የነጦፋዊው የዮፌ ልጆች፣ የማዕካታዊ ልጅ ያእዛንያን ሰዎቻቸውም ነበሩ።

9የሳፋን ልጅ የአኪቃም ልጅ ጎዶልያስ ለእነርሱና ለሰዎቻቸው እንዲህ ሲል ቃል ገባላቸው፤ “ለባቢሎናውያን መገዛት አትፍሩ፤ በምድሪቱ ተቀምጣችሁ የባቢሎንን ንጉሥ አገልግሉ፤ መልካም ይሆንላችኋል።

10እኔም ራሴ ወደ እኛ በሚመጡት በባቢሎናውያን ፊት ልቆምላችሁ፣ በምጽጳ እቀመጣለሁ፤ እናንተ ግን ወይን፣ የበጋ ፍሬና ዘይት አምርቱ፤ በማከማቻ ዕቃዎቻችሁ ውስጥ ክተቱ፤ በያዛችኋቸውም ከተሞች ተቀመጡ።”

11በሞዓብ፣ በአሞን፣ በኤዶምና በሌሎች አገሮች ሁሉ የነበሩ አይሁድ በሙሉ የባቢሎን ንጉሥ፣ ሰዎችን በይሁዳ እንዳስ ቀረና የሳፋን ልጅ የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በላያቸው እንደ ሾመ በሰሙ ጊዜ፣

12ሁላቸውም ከተበታተኑበት አገር ሁሉ ወደ ይሁዳ ምድር ተመለሱ፤ በምጽጳ ወደ ሚኖረውም ወደ ጎዶልያስ መጡ፤ ወይንና የበጋ ፍሬም በብዛት አከማቹ።

13የቃሬያ ልጅ ዮሐናንና ገና በየሜዳው የነበሩት የጦር መኰንኖች ሁሉ ወደ ጎዶልያስ ወደ ምጽጳ መጥተው፣

14“የአሞናውያን ንጉሥ በአሊስ አንተን ለመግደል የናታንያን ልጅ እስማኤልን እንደላከው አታውቅምን?” አሉት። የአኪቃም ልጅ ጎዶልያስ ግን አላመናቸውም።

15የቃሬያ ልጅ ዮሐናን፣ “ማንም ሳያውቅ የናታንያን ልጅ እስማኤልን ሄጄ ልግደለው፤ ሸሽተው ወደ አንተ የመጡት አይሁድ እንዲበተኑ፣ በይሁዳም የቀሩት እንዲጠፉ ለምን ይገድልሃል?” ብሎ በምጽጳ ለጎዶልያስ በምስጢር ነገረው።

16የአኪቃም ልጅ ጎዶልያስ ግን የቃሬያን ልጅ ዮሐናንን፣ “ስለ እስማኤል የምትነግረኝ ሁሉ እውነት አይደለምና ይህን ነገር አታድርግ” አለው።

ማብራሪያ

40:1-6 የጥበቃው አለቃ፣ ኤርምያስ የእግዚአብሔር መልእክተኛ ሆኖ ትንቢት የተናገረውን እርሱ የእግዚአብሔር መሳሪያ ሆኖ እንደፈጸመው የሚያመካ ይመስላል። ብዙዎች የእግዚአብሔርን ፍትህና እውነት በሌሎች ላይ ማየት ሲችሉ፣ ራሳቸውንና የራሳቸውን ኃጢአት በተመለከተ ግን ግድ የለሾችና እውሮች ናቸው። ነገር ግን፣ ፈጥኖም ይሁን ዘግይቶ፣ የመከራቸው ሁሉ መንስኤ ኃጢአታቸው እንደሆነ ሁሉም ሰዎች እንዲገነዘቡ ይደረጋሉ። ኤርምያስ ራሱን እንዲወስን ፈቃድ ተሰጥቶታል፤ ነገር ግን በባቢሎን ንጉሥ ሥር የአገሪቱ ገዥ ወደሆነው ወደ ገዳልያ እንዲሄድ ተመክሯል። ኤርምያስ በዚህ ውሳኔ ትክክል ሆኖ እንደሠራ አጠያያቂ ነው።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG ወደ ባቢሎን በተማረኩት በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ምርኮኞች መካከል የዘበኞቹ አለቃ ናቡዘረዳን በሰንሰለት አስሮ በወሰደው ጊዜ ከራማ ከለቀቀው በኋላ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣ ቃል… አማርኛ ENGNIV The word came to Jeremiah from the Lord after Nebuzaradan commander of the imperial guard had released him at Ramah. He… English BCV ኣዛዚ ሰራዊት ናቡዘረዳን ንኤርሚያስ ካብ ኢየሩሳሌምን ካብ ይሁዳን፥ ናብ ባቢሎን ናብ ዝተወሰዱ ማእኸል ኵሎም ምሩኻት፥ ብሰንሰለት ኣሲሩ ምስ ኣምፅኦ፥ ካብ ራማውን ፈቲሑ ምስ ሰደዶ፥ ካብ እ… ትግርኛ GAZBIB Nebuzaraadaan abboomaan loltuu mootichaa Raamaadhaa ana Ermiyaasin erga hiiksisee booddee, dubbiin Waaqayyoo gara koo i… Afaan Oromoo BCV GIZ ቃል ዘኮነ እምኀበ እግዚአብሔር ኀበ ኤርምያስ ነቢይ፡ እምድኅረ ተፈነወ ናቡዛርዳን ሊቀ መበስላን እምራማ፡ ሶበ ነሥኦ እንዘ እሱር በማእሰር፡ ወማእከለ ፈላስያን ዘኢየሩሳሌም ወዘይሁዳ እለ ተ… giz GAZGAZ Nebuzaraadaan abboomaan loltuu mootichaa Raamaadhaa ana Ermiyaasin erga hiiksisee booddee, dubbiin Waaqayyoo gara koo i… Afaan Oromoo BCV aksum ኣዛዚ ሰራዊት ናቡዘረዳን ንኤርሚያስ ካብ ኢየሩሳሌምን ካብ ይሁዳን፥ ናብ ባቢሎን ናብ ዝተወሰዱ ማእኸል ኵሎም ምሩኻት፥ ብሰንሰለት ኣሲሩ ምስ ኣምፅኦ፥ ካብ ራማውን ፈቲሑ ምስ ሰደዶ፥ ካብ እ… ትግርኛ SWAHSUV Neno hili ndilo lililomjia Yeremia, kutoka kwa Bwana, baada ya wakati ule Nebuzaradani, amiri wa askari walinzi, alipom… Kiswahili