ትንቢተ ኤርምያስ 40

AMHEVGአማርኛ16 ጥቅሶች4:17 አዳምጥ
አዳምጥ 4:17 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ወደ ባቢሎን በተማረኩት በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ምርኮኞች መካከል የዘበኞቹ አለቃ ናቡዘረዳን በሰንሰለት አስሮ በወሰደው ጊዜ ከራማ ከለቀቀው በኋላ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣ ቃል ይህ ነው።

2የዘበኞቹም አለቃ ኤርምያስን ወሰደው፥ እንዲህም አለው፦ አምላክህ እግዚአብሔር ይህን ክፉ ነገር በዚህ ስፍራ ላይ ተናገረ፤

3እግዚአብሔርም አመጣው እንደ ተናገረውም አደረገ፤ በእግዚአብሔርም ላይ ኃጢአት ሠርታችኋልና፥ ቃሉንም አልሰማችሁምና ይህ ነገር ሆነባችሁ።

4አሁንም፥ እነሆ፥ በእጅህ ካለችው ሰንሰለት ዛሬ ፈታሁህ። ከእኔ ጋር ወደ ባቢሎን መምጣት መልካም መስሎ ቢታይህ፥ ና፥ እኔም በመልካም አይሃለሁ፤ ከእኔ ጋር ወደ ባቢሎን መምጣት መልካም መስሎ ባይታይህ ግን፥ ተቀመጥ፤ እነሆ፥ አገሪቱ ሁሉ በፊትህ ናት፤ ትሄድ ዘንድ መልካም መስሎ ወደሚታይህ ደስ ወደሚያሰኝህም ስፍራ ሂድ።

5እርሱም ገና ሳይመለስ፦ የባቢሎን ንጉሥ በይሁዳ ከተሞች ላይ ወደ ሾመው ወደ ሳፋን ልጅ ወደ አኪቃም ልጅ ወደ ጎዶልያስ ተመለስ፥ ከእርሱም ጋር በሕዝቡ መካከል ተቀመጥ፤ ወይም ትሄድ ዘንድ ደስ ወደሚያሰኝህ ስፍራ ሂድ፡ አለው። የዘበኞቹም አለቃ ስንቅና ስጦታ ሰጥቶ አሰናበተው።

6ኤርምያስም የአኪቃም ልጅ ጎዶልያስ ወዳለበት ወደ ምጽጳ ሄደ፥ ከእርሱም ጋር በአገሩ ውስጥ በቀሩት ሕዝብ መካከል ተቀመጠ።

7በየሜዳውም የነበሩት የጭፍራ አለቆችና ሰዎቻቸው ሁሉ የባቢሎን ንጉሥ የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በምድር ላይ እንደ ሾመ፥ ወንዶችንና ሴቶችን ልጆችንም፥ ወደ ባቢሎን ያልተማረኩትን የምድርን ድሆች፥ እንዳስጠበቀ በሰሙ ጊዜ የናታንያ ልጅ እስማኤል፥

8የቃሬያም ልጅ ዮሐናንና ዮናታን፥ የተንሑሜትም ልጅ ሠራያ፥ የነጦፋዊውም የዮፌ ልጆች የማዕካታዊውም ልጅ ያእዛንያ ከሰዎቻቸው ጋር ወደ ጎዶልያስ ወደ ምጽጳ መጡ።

9የሳፋንም ልጅ የአኪቃም ልጅ ጎዶልያስ ለእነርሱና ለሰዎቻቸው እንዲህ ብሎ ማለ፦ ለከለዳውያን ትገዙ ዘንድ አትፍሩ፤ በምድር ተቀመጡ ለባቢሎንም ንጉሥ ተገዙ፥ መልካምም ይሆንላችኋል።

10እኔም፥ እነሆ፥ ወደ እኛ በሚመጡት ከለዳውያን ፊት እቆም ዘንድ በምጽጳ እኖራለሁ፤ እናንተ ግን ወይንንና የበጋ ፍሬ ዘይትንም አከማቹ፥ በየዕቃችሁም ውስጥ ክተቱ፥ በያዛችኋቸውም ከተሞቻችሁ ተቀመጡ።

11በሞዓብም በአሞንም ልጆች መካከል በኤዶምያስም በምድርም ሁሉ ላይ የነበሩ አይሁድ ሁሉ የባቢሎን ንጉሥ የይሁዳን ቅሬታ እንዳስቀረ፥ የሳፋንንም ልጅ የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በላያቸው እንደ ሾመው በሰሙ ጊዜ፥

12አይሁድ ሁሉ ከተሰደዱበት ስፍራ ሁሉ ተመለሱ፥ ወደ ይሁዳም አገር ጎዶልያስ ወዳለበት ወደ ምጽጳ መጡ፥ ወይንና የበጋንም ፍሬ እጅግ ብዙ አከማቹ።

13የቃሬያም ልጅ ዮሐናን በየሜዳውም የነበሩ የጭፍራ አለቆች ሁሉ ወደ ጎዶልያስ ወደ ምጽጳ መጥተው፦

14የአሞን ልጆች ንጉሥ በኣሊስ ይገድልህ ዘንድ የናታንያን ልጅ እስማኤልን እንደ ሰደደ ታውቃለህን? አሉት። የአኪቃም ልጅ ጎዶልያስ ግን አላመናቸውም።

15የቃሬያም ልጅ ዮሐናን፦ እባክህ፥ ልሂድ፤ ማንም ሳያውቅ የናታንያን ልጅ እስማኤልን ልግደለው፤ ወደ አንተ የተሰበሰቡ አይሁድ ሁሉ እንዲበተኑ የይሁዳም ቅሬታ እንዲጠፋ ነፍስህን ስለ ምን ይገድላል? ብሎ በምጽጳ በቆይታ ለጎዶልያስ ተናገረ።

16የአኪቃም ልጅ ጎዶልያስ ግን የቃሬያን ልጅ ዮሐናንን፦ በእስማኤል ላይ ሐሰት ተናግረሃልና ይህን ነገር አታድርግ፡ አለው።

ማብራሪያ

40:1-6 የጥበቃው አለቃ፣ ኤርምያስ የእግዚአብሔር መልእክተኛ ሆኖ ትንቢት የተናገረውን እርሱ የእግዚአብሔር መሳሪያ ሆኖ እንደፈጸመው የሚያመካ ይመስላል። ብዙዎች የእግዚአብሔርን ፍትህና እውነት በሌሎች ላይ ማየት ሲችሉ፣ ራሳቸውንና የራሳቸውን ኃጢአት በተመለከተ ግን ግድ የለሾችና እውሮች ናቸው። ነገር ግን፣ ፈጥኖም ይሁን ዘግይቶ፣ የመከራቸው ሁሉ መንስኤ ኃጢአታቸው እንደሆነ ሁሉም ሰዎች እንዲገነዘቡ ይደረጋሉ። ኤርምያስ ራሱን እንዲወስን ፈቃድ ተሰጥቶታል፤ ነገር ግን በባቢሎን ንጉሥ ሥር የአገሪቱ ገዥ ወደሆነው ወደ ገዳልያ እንዲሄድ ተመክሯል። ኤርምያስ በዚህ ውሳኔ ትክክል ሆኖ እንደሠራ አጠያያቂ ነው።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV The word came to Jeremiah from the Lord after Nebuzaradan commander of the imperial guard had released him at Ramah. He… English BCV ኣዛዚ ሰራዊት ናቡዘረዳን ንኤርሚያስ ካብ ኢየሩሳሌምን ካብ ይሁዳን፥ ናብ ባቢሎን ናብ ዝተወሰዱ ማእኸል ኵሎም ምሩኻት፥ ብሰንሰለት ኣሲሩ ምስ ኣምፅኦ፥ ካብ ራማውን ፈቲሑ ምስ ሰደዶ፥ ካብ እ… ትግርኛ GAZBIB Nebuzaraadaan abboomaan loltuu mootichaa Raamaadhaa ana Ermiyaasin erga hiiksisee booddee, dubbiin Waaqayyoo gara koo i… Afaan Oromoo BCV GIZ ቃል ዘኮነ እምኀበ እግዚአብሔር ኀበ ኤርምያስ ነቢይ፡ እምድኅረ ተፈነወ ናቡዛርዳን ሊቀ መበስላን እምራማ፡ ሶበ ነሥኦ እንዘ እሱር በማእሰር፡ ወማእከለ ፈላስያን ዘኢየሩሳሌም ወዘይሁዳ እለ ተ… giz GAZGAZ Nebuzaraadaan abboomaan loltuu mootichaa Raamaadhaa ana Ermiyaasin erga hiiksisee booddee, dubbiin Waaqayyoo gara koo i… Afaan Oromoo BCV aksum ኣዛዚ ሰራዊት ናቡዘረዳን ንኤርሚያስ ካብ ኢየሩሳሌምን ካብ ይሁዳን፥ ናብ ባቢሎን ናብ ዝተወሰዱ ማእኸል ኵሎም ምሩኻት፥ ብሰንሰለት ኣሲሩ ምስ ኣምፅኦ፥ ካብ ራማውን ፈቲሑ ምስ ሰደዶ፥ ካብ እ… ትግርኛ AMHNIV የክብር ዘበኞች አዛዥ ናቡዘረዳን ኤርምያስን ከኢየሩሳሌምና ከይሁዳ ወደ ባቢሎን በሚወስዱት ምርኮኞች ሁሉ መካከል በራማ በሰንሰለት ታስሮ ባገኘው ጊዜ አስፈታው፤ ከዚህ በኋላ የእግዚአብሔር ቃ… አማርኛ SWAHSUV Neno hili ndilo lililomjia Yeremia, kutoka kwa Bwana, baada ya wakati ule Nebuzaradani, amiri wa askari walinzi, alipom… Kiswahili