ትንቢተ ኤርምያስ 19

AMHNIVአማርኛ15 ጥቅሶች3:39 አዳምጥ
አዳምጥ 3:39 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ሄደህ፣ ከሸክላ ሠሪ ገምቦ ግዛ፤ ከሕዝቡና ከካህናቱ መካከል ታላላቅ የሆኑትን አንዳንዶቹን ይዘህ፣

2በገል በር መግቢያ አጠገብ ወዳለው ወደ ሄኖም ልጅ ሸለቆ ውጣ። በዚያም የምነግርህን ቃል ተናገር፤

3እንዲህም በል፤ ‘የይሁዳ ነገሥታትና በኢየሩሳሌም የምትኖሩ ሆይ፤ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ለሰሚው ሁሉ ጆሮ የሚዘገንን ክፉ ነገር እነሆ በዚህ ስፍራ አመጣለሁ፤

4እኔን ትተውኝ፣ ይህን ስፍራ የባዕድ አማልክት ቦታ አድርገውታልና። እነርሱም ሆኑ አባቶቻቸው፣ የይሁዳ ነገሥታትም ለማያውቋቸው አማልክት ሠውተዋል፤ ይህንም ስፍራ በንጹሓን ደም ሞልተውታል፤

5እኔም ያላዘዝኋቸውን፣ ያልተናገርኋቸውን፣ ፈጽሞም ያላሰብሁትን፣ ወንዶች ልጆቻቸውን በእሳት ሊሠውለት ለበኣል መስገጃ ኰረብታዎች ሠርተዋል።

6ስለዚህ ሰዎች ይህን ስፍራ የዕርድ ሸለቆ እንጂ ከእንግዲህ ቶፌት ወይም የሄኖም ልጅ ሸለቆ ብለው የማይጠሩበት ዘመን ይመጣል፤ ይላል እግዚአብሔር።

7“ ‘በዚህ ስፍራ የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ዕቅድ አፈርሳለሁ፤ በጠላቶቻቸው ፊት ሕይወታቸውን በሚሹት እጅ በሰይፍ እንዲወድቁ አደርጋለሁ፤ ሬሳቸውንም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት ምግብ አድርጌ እሰጣለሁ።

8ይህችን ከተማ ድምጥማጧን አጠፋለሁ፤ ለመሣለቂያም አደርጋታለሁ፤ በዚያም የሚያልፉ ሁሉ ከደረሰባት ጒዳት የተነሣ ወይ ጒድ! ይላሉ ያሾፋሉም።

9የወንዶችና የሴቶች ልጆቻቸውን ሥጋ እንዲበሉ አደርጋለሁ፤ ሕይወታቸውን ለማጥፋት የሚሹ ጠላቶቻቸው ከበው ሲያስጨንቋቸው፣ አንዱ የሌላውን ሥጋ ይበላል።’

10“ገምቦውንም ከአንተ ጋር በሄዱ ሰዎች ፊት ትሰብራለህ፤

11እንዲህም ትላቸዋለህ፤ ‘የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “የሸክላ ሠሪው ገንቦ እንደ ተሰበረና ሊጠገን እንደማይቻል፣ ይህን ሕዝብና ይህቺን ከተማ እንዲሁ እሰብራለሁ፤ የቀብር ቦታ ከመታጣቱ የተነሣ ሙታናቸውን በቶፌት ይቀብራሉ።

12በዚህ ስፍራና በውስጡም በሚኖሩት ላይ ይህን አደርጋለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር። ይህቺን ከተማ እንደ ቶፌት አደርጋታለሁ።

13በጣራዎቻቸው ላይ ለሰማይ ሰራዊት ዕጣን የታጠነባቸውና ለባዕዳን አማልክት የመጠጥ ቍርባን የቀረበባቸው፣ የኢየሩሳሌም ቤቶችና የይሁዳ ነገሥታት ቤቶች እንደ ቶፌት የረከሱ ይሆናሉ።

14ኤርምያስም እግዚአብሔር ትንቢት እንዲናገር ልኮት ከነበረበት ከቶፌት ተመልሶ፣ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አደባባይ በመቆም፣ ለሕዝቡ ሁሉ እንዲህ አለ፤

15“የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘እነሆ ዐንገታቸውን በማደንደን ቃሌን ስላልሰሙ በዚህች ከተማና በዙሪያዋ ባሉ መንደሮች ሁሉ ላይ ላደርስ ያሰብሁትን ጥፋት ሁሉ አመጣለሁ።’ ”

ማብራሪያ

19:1-9

ነቢዩ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ ስለሚመጣው ጥፋት ማስጠንቀቅ አለበት። ገዢዎችም ተገዢዎችም ትኩረት ሊሰጡት ይገባል። ቅድስና የምድር ሁሉ ደስታ ያደረገው ያ ስፍራ፣ ኃጢአት ግን የምድር ሁሉ መወገዝያና እፍረት አደረገው። ከእግዚአብሔር ፍርድ ማምለጥ የሚቻለው ወደ ምሕረቱ በመሸሽ ብቻ ነው።

19:10-15 የሸክላ ሠሪ ዕቃ ከደረቀ በኋላ ከተሰበረ ፈጽሞ ሊጠገን አይችልም።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፦ ሂድ፥ ከሸክላ ሠሪ ገምቦ ግዛ፥ ከሕዝቡም ሽማግሌዎችና ከካህናት ሽማግሌዎች ከአንተ ጋር ውሰድ፤ አማርኛ ENGNIV This is what the Lord says: “Go and buy a clay jar from a potter. Take along some of the elders of the people and of th… English BCV እግዚኣብሄር ከምዙይ በለኒ፦ “ኪድ፤ ካብቲ ሰራሒ መሬት ሳርማ ዓድግ። ካብቶም ዓበይቲ ህዝብን ካብቶም ዓበይቲ ኻህናትንውን ንገሊኣቶም ምሳኻ ተማላእ። ትግርኛ GAZBIB Waaqayyo wanta kanatti fufee jiru dubbatee,“Dhaqii nama suphee dha'u irraa cuggee tokko bitadhuu maanguddoota sabaa kee… Afaan Oromoo BCV GIZ ከመዝ ይቤ እግዚአብሔር፦ ሑር ተሣየጥ ለከ ቀሡተ ልሕኵት ግብረ እደ ለብሐዊ፡ ወንሣእ እምውስተ ረበናቶሙ ለሕዝብ ወእም ረበናተ ካህናት። giz GAZGAZ Waaqayyo wanta kanatti fufee jiru dubbatee,“Dhaqii nama suphee dha'u irraa cuggee tokko bitadhuu maanguddoota sabaa kee… Afaan Oromoo BCV aksum እግዚኣብሄር ከምዙይ በለኒ፦ “ኪድ፤ ካብቲ ሰራሒ መሬት ሳርማ ዓድግ። ካብቶም ዓበይቲ ህዝብን ካብቶም ዓበይቲ ኻህናትንውን ንገሊኣቶም ምሳኻ ተማላእ። ትግርኛ SWAHSUV Bwana akasema hivi, Enenda ukanunue gudulia la mfinyanzi, ukachukue pamoja nawe baadhi ya wazee wa watu, na baadhi ya w… Kiswahili