ትንቢተ ኢሳይያስ 9

AMHEVGአማርኛ20 ጥቅሶች3:53 አዳምጥ
አዳምጥ 3:53 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ነገር ግን ተጨንቃ ለነበረች ጨለማ አይሆንም። በመጀመሪያው ዘመን የዛብሎንንና የንፍታሌምን ምድር አቃለለ፤ በኋለኛው ዘመን ግን በዮርዳኖስ ማዶ በባሕር መንገድ ያለውን የአሕዛብን ገሊላ ያከብራል።

2በጨለማ የሄደ ሕዝብ ብርሃን አየ፤ በሞት ጥላ አገርም ለኖሩ ብርሃን ወጣላቸው።

3ሕዝብን አብዝተሃል፥ ደስታንም ጨምረህላቸዋል፤ በመከር ደስ እንደሚላቸው፥ ሰዎችም ምርኮን ሲካፈሉ ደስ እንደሚላቸው በፊትህ ደስ ይላቸዋል።

4በምድያም ጊዜ እንደ ሆነ የሸክሙን ቀንበር የጫንቃውንም በትር የአስጨናቂውንም ዘንግ ሰብረሃል።

5የሚረግጡ የሰልፈኞች ጫማ ሁሉ፥ በደምም የተለወሰ ልብስ ለቃጠሎ ይሆናል፥ እንደ እሳት ማቃጠያም ሆኖ ይቃጠላል።

6ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።

7ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም ድረስ በፍርድና በጽድቅ ያጸናውና ይደግፈው ዘንድ በዳዊት ዙፋንና በመንግሥቱ ላይ አለቅነቱ ይበዛል፥ ለሰላሙም ፍፃሜ የለውም። የእግዚአብሔር ቅንዓት ይህን ያደርጋል።

8ጌታ በያዕቆብ ላይ ቃልን ሰደደ፥ በእስራኤልም ላይ ወደቀ።

9በትዕቢትና በልብ ኵራት፦ ጡቡ ወድቆአል፥ ነገር ግን በተወቀረ ድንጋይ እንሠራለን፤ የሾላ ዛፎች ተቈርጠዋል፥ ነገር ግን ዝግባን እንተካባቸዋለን፡ የሚሉ በኤፍሬምና በሰማርያ የሚኖሩ ሕዝብ ሁሉ ያውቃሉ።

11ስለዚህ እግዚአብሔር በጽዮን ተራራ ላይ ተቋቋሚ ያስነሣበታል፥

12ጠላቶቹን ሶርያውያንንም ከምሥራቅ፥ ፍልስጥኤማውያንንም ከምዕራብ ያንቀሳቅስበታል፤ እስራኤልንም በተከፈተ አፍ ይበሉታል። በዚህም ሁሉ እንኳ ቍጣው አልተመለሰችም፥ ነገር ግን እጁ ገና ተዘርግታ ትኖራለች።

13ሕዝቡ ግን ወደ ቀሠፋቸው አልተመለሱም፥ የሠራዊትንም ጌታ እግዚአብሔርን አልፈለጉም።

14ስለዚህ እግዚአብሔር ራስና ጅራትን፥ የሰሌኑን ቅርንጫፍና እንግጫውን በአንድ ቀን ከእስራኤል ይቆርጣል።

15ሽማግሌውና ከበርቴው እርሱ ራስ ነው፤ በሐሰትም የሚያስተምር ነቢይ እርሱ ጅራት ነው።

16ይህን ሕዝብ የሚመሩ ያስቱአቸዋል፤ ተመሪዎቹም ይጠፋሉ።

17ሰው ሁሉ ዝንጉና ክፉ ሠሪ ነውና፥ አፍም ሁሉ ስንፍናን ይናገራልና ስለዚህ ጌታ በጕልማሶቻቸው ደስ አይለውም፥ ለድሀ አደጎቻቸውና ለመበለቶቻቸውም አይራራም። በዚህም ሁሉ እንኳ ቍጣው አልተመለሰችም፥ ነገር ግን እጁ ገና ተዘርግታ ትኖራለች።

18ክፋት እንደ እሳት ይቃጠላል፤ ኵርንችቱንና እሾሁን ይበላል፤ ጭፍቅ የሆነውንም ዱር ያቃጥላል፥ ጢሱም ተትጐልጕሎ እንደ ዓምድ ይወጣል።

19በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ቍጣ ምድር ተቃጥላለች፤ ሕዝቡም እሳት እንደሚበላው እንጨት ሆኖአል፤ ሰውም ለወንድሙ አይራራም።

20ሰው በቀኙ በኩል ይነቅላል ይራብማል፤ በግራም በኩል ይበላል አይጠግብምም፤ እያንዳንዱም የክንዱን ሥጋ ይበላል፤

21ምናሴ ኤፍሬምን ኤፍሬምም ምናሴን ይበላል፤ እነርሱ በአንድነት የይሁዳ ጠላቶች ይሆናሉ። በዚህም ሁሉ እንኳ ቍጣው አልተመለሰችም፥ ነገር ግን እጁ ገና ተዘርግታ ትኖራለች።

ማብራሪያ

9:1-7 በዚህ የተጠቀሱትን አገሮች አስቀድሞ ያወደሙት ሶርያውያንና አሦራውያን ነበሩ፤ ያም ክልል በመጀመሪያ የክርስቶስ ስብከት በረከት ያገኘ ነበር። ወንጌል የሌላቸው ሁሉ በጨለማና በታላቅ አደጋ ውስጥ ይሄዳሉ። ነገር ግን ወንጌል ወደ ማንኛውም ስፍራ፣ ወደ ማንኛውም ነፍስ ሲመጣ፣ ብርሃን ይመጣል። ወደ ልባችን እንዲበራ፣ ለእኛም ለመዳን ጥበበኞች እንድንሆን አጥብቀን እንጸልይ።

ወንጌል ከእርሱ ጋር ደስታን ያመጣል። ደስታ እንዲኖራቸው የሚፈልጉ ሁሉ፣ ገበሬው የመከር ደስታን ከማግኘቱ በፊት ከባድ ሥራ እንደሚጠብቀው ሁሉ፣ ከባድ ሥራን ማለፍ እንደሚኖርባቸው መጠበቅ አለባቸው፤ ወታደሩም ምርኮን ከመከፋፈሉ በፊት ከባድ ውጊያ እንደሚያደርግ ሁሉ ከባድ ትግልን ማለፍ ይጠበቅባቸዋል። አይሁድ ከብዙ አስጨናቂዎች ቀንበር ነፃ ወጥተው ነበር፤ ይህ ደግሞ አማኞች ከሰይጣን ቀንበር ነፃ የሚወጡበት ጥላ ነበር።

የአማኞች ነፍስ ከኃጢአት ኃይልና እርኩሰት የሚነጻው፣ እንደ ማንጻት እሳት በሆነ በመንፈስ ቅዱስ ተጽዕኖ ይሆናል። እነዚህ ታላላቅ የቤተ ክርስቲያን ነገሮች በመሲሑ በዕማኑኤል ይፈጸማሉ። ህፃኑ ተወልዷል፤ ይህ እውነት ነበር፤ ቤተ ክርስቲያንም ክርስቶስ በሥጋ ከመምጣቱ በፊት፣ እርሱ ባደረገው ሥራ ተጠቅማለች። ይህም ስለ እርሱና ስለ መንግሥቱ የተነገረ ትንቢት ሲሆን፣ የእስራኤልን መጽናናት ይጠባበቁ የነበሩት ሰዎች በደስታ ያነቡት ነበር።

ይህ ሕፃን የተወለደው ለእኛ ለሰዎች፣ ለእኛ ለኃጢአተኞች፣ ከዓለም መጀመሪያ እስከ መጨረሻ ላሉት አማኞች ሁሉ ጥቅም ነው። እርሱ እግዚአብሔርና ሰው ስለሆነ፣ ድንቅ ተብሎ መጠራቱ ትክክል ነው።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV Nevertheless, there will be no more gloom for those who were in distress. In the past he humbled the land of Zebulun an… English BCV ግና ኣብ ጭንቂ ንዝነበረት ደጊም ፀልማት ኣይኸውንን፤ ኣብቲ ቐዳማይ ዘመን ንምድሪ ዛብሎንን ንምድሪ ንፍታሌምን ኣዋረደ። ብዳሕረዋይ ዘመን ግና፥ ብማዕዶ ዮርዳኖስ፥ ብመንገዲ ባሕሪ ዘላ ናይ … ትግርኛ GAZBIB Warri dhiphina keessa turan si'achi dukkana keessa hin jiraatan; inni bara durii biyya Zaabiloonii fi biyya Niftaalem g… Afaan Oromoo BCV GIZ ወኢይትባላሕ ዘተመንደበ እሰከ አመ ይበጽሕ ዕድሜሁ ለዝ; ዘንተ ፍጡነ ግበር ወፍጡነ ስተይ ብሔረ ዛብሎን ወምድረ ንፍታሌም ተረፈ ጰራልዩ ወማዕዶተ ዮርዳኖስ ዘገሊላ ዘአሕዛብ። giz GAZGAZ Warri dhiphina keessa turan si'achi dukkana keessa hin jiraatan; inni bara durii biyya Zaabiloonii fi biyya Niftaalem g… Afaan Oromoo BCV aksum ግና ኣብ ጭንቂ ንዝነበረት ደጊም ፀልማት ኣይኸውንን፤ ኣብቲ ቐዳማይ ዘመን ንምድሪ ዛብሎንን ንምድሪ ንፍታሌምን ኣዋረደ። ብዳሕረዋይ ዘመን ግና፥ ብማዕዶ ዮርዳኖስ፥ ብመንገዲ ባሕሪ ዘላ ናይ … ትግርኛ AMHNIV ነገር ግን ተጨንቀው የነበሩ ከእንግዲህ ተስፋ ቢስ አይሆኑም። በቀደመው ዘመን የዛብሎንንና የንፍታሌምን ምድር አዋረደ፤ በሚመጣው ዘመን ግን ከዮርዳኖስ ማዶ፣ በባሕር መንገድ አጠገብ ያለውን … አማርኛ SWAHSUV Lakini yeye aliyekuwa katika dhiki hatakosa changamko. Hapo kwanza aliiingiza nchi ya Zabuloni na nchi ya Naftali katik… Kiswahili