ትንቢተ ኢሳይያስ 9

AMHNIVአማርኛ21 ጥቅሶች4:07 አዳምጥ
አዳምጥ 4:07 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ነገር ግን ተጨንቀው የነበሩ ከእንግዲህ ተስፋ ቢስ አይሆኑም። በቀደመው ዘመን የዛብሎንንና የንፍታሌምን ምድር አዋረደ፤ በሚመጣው ዘመን ግን ከዮርዳኖስ ማዶ፣ በባሕር መንገድ አጠገብ ያለውን የአሕዛብን ገሊላ ያከብራል፤

2በጨለማ የሚኖር ሕዝብ ታላቅ ብርሃን አየ፤ በሞት ጥላ ምድር ለኖሩትም ብርሃን ወጣላቸው።

3ሕዝብን አበዛህ፤ ደስታቸውንም ጨመርህ፤ ሰዎች ምርትን ሲሰበስቡ፣ ምርኮንም ሲከፋፈሉ ደስ እንደሚላቸው ሁሉ፣ እነርሱም በፊትህ ደስ ይላቸዋል።

4ምድያም ድል በተመታ ጊዜ እንደሆነው፣ የከበዳቸውን ቀንበር፣ በትከሻቸው ላይ የነበረውን በትር፣ የተጨቈኑበትንም ዘንግ ሰብረህላቸዋል።

5የጦረኞች ጫማ ሁሉ፣ በደም የተለወሰ ልብስም ሁሉ፣ ለእሳት ይዳረጋል፤ ይማገዳልም።

6ሕፃን ተወልዶልናልና፤ ወንድ ልጅ ተሰጥቶናል፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል። ስሙም፣ ድንቅ መካር፣ ኀያል አምላክ፣ የዘላለም አባት፣ የሰላም ልዑል ይባላል።

7ለመንግሥቱ ስፋት፣ ለሰላሙም ብዛት ፍጻሜ የለውም፤ ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘላለም፣ መንግሥቱን በፍትሕና በጽድቅ ይመሠርታል፤ ደግፎ በመያዝም ያጸናዋል። በዳዊት ዙፋን ይቀመጣል፤ አገሩንም ሁሉ ይገዛል፤ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ቅናት ይህን ያደርጋል።

8ጌታ በያዕቆብ ላይ ቃል ላከ፤ በእስራኤልም ላይ ይወድቃል።

9ሕዝቡ በሙሉ፣ ኤፍሬምና የሰማርያ ነዋሪዎች ይህን ያውቃሉ፤ በትዕቢትና በልብ እብሪትም እንዲህ ይላሉ፤

10“ጡቦቹ ወድቀዋል፤ እኛ ግን በጥርብ ድንጋይ መልሰን እንገነባለን፤ የሾላ ዛፎቹ ተቈርጠዋል፤ እኛ ግን በዝግባ እንተካለን።”

11ነገር ግን እግዚአብሔር የረአሶንን ጠላቶች ያጠናክራል፤ በእነርሱም ላይ ያመጣባቸዋል፤ ባለጋራዎቻቸውንም ያነሣሣባቸዋል።

12ሶርያውያን ከምሥራቅ፣ ፍልስጥኤማውያን ከምዕራብ፤ አፋቸውን ከፍተው እስራኤልን ይቦጫጭቋታል። ይህም ሁሉ ሆኖ፣ ቍጣው ገና አልበረደም፤ እጁ እንደ ተዘረጋ ነው።

13ሕዝቡ ግን ወደ ቀጣቸው ፊታቸውን አልመለሱም፤ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔርንም አልፈለጉም።

14ስለዚህ እግዚአብሔር ራስንና ጅራትን፣ የዘንባባውን ቅርንጫፍና ሸምበቆውን ከእስራኤል በአንድ ቀን ይቈርጣል።

15ሽማግሌዎችና የተከበሩ ሰዎች ራስ፣ ሐሰትን የሚያስተምሩ ነቢያት ደግሞ ጅራት ናቸው።

16ይህን ሕዝብ የሚመሩት ያስቱታል፤ የሚመራውም ሕዝብ ከመንገድ ወጥቶ ይባዝናል።

17ስለዚህ ጌታ በጐበዛዝት ደስ አይሰኝም፤ አባት ለሌላቸውና ለመበለቶች አይራራም፤ ሁሉም ፈሪሀ እግዚአብሔር ያላደረበትና ክፉ አድራጊ ነው፤ የሁሉ አፍ አስጸያፊ ቃል ይናገራልና። ይህም ሁሉ ሆኖ፣ ቍጣው ገና አልበረደም፤ እጁም እንደ ተዘረጋ ነው።

18እንግዲህ ርኵሰት እንደ እሳት ይቀጣጠላል፤ እሾህንና ኵርንችትን ይበላል፤ ጥቅጥቅ ያለውን ደን ያነዳል፤ ጢሱም ተትጐልጕሎ እንደ ዐምድ ይቆማል።

19በሰራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ቍጣ ምድር ትጋያለች፤ ሕዝቡም እሳት ውስጥ እንደሚጨመር ማገዶ ይሆናል፤ ወንድሙንም ማዳን የሚችል ማንም የለም።

20በቀኝ በኩል ይጐርሳሉ፤ ነገር ግን ራባቸው አይታገሥም፤ በግራም በኩል ይበላሉ፤ ነገር ግን አይጠግቡም፤ እያንዳንዱም የገዛ ወገኑን ሥጋ ይበላል።

21ምናሴ ኤፍሬምን፣ ኤፍሬም ምናሴን ይበላል፤ በይሁዳም ላይ በአንድነት ይነሣሉ፤ ይህም ሁሉ ሆኖ፣ ቍጣው ገና አልበረደም፤ እጁም እንደ ተዘረጋ ነው።

ማብራሪያ

9:1-7 በዚህ የተጠቀሱትን አገሮች አስቀድሞ ያወደሙት ሶርያውያንና አሦራውያን ነበሩ፤ ያም ክልል በመጀመሪያ የክርስቶስ ስብከት በረከት ያገኘ ነበር። ወንጌል የሌላቸው ሁሉ በጨለማና በታላቅ አደጋ ውስጥ ይሄዳሉ። ነገር ግን ወንጌል ወደ ማንኛውም ስፍራ፣ ወደ ማንኛውም ነፍስ ሲመጣ፣ ብርሃን ይመጣል። ወደ ልባችን እንዲበራ፣ ለእኛም ለመዳን ጥበበኞች እንድንሆን አጥብቀን እንጸልይ።

ወንጌል ከእርሱ ጋር ደስታን ያመጣል። ደስታ እንዲኖራቸው የሚፈልጉ ሁሉ፣ ገበሬው የመከር ደስታን ከማግኘቱ በፊት ከባድ ሥራ እንደሚጠብቀው ሁሉ፣ ከባድ ሥራን ማለፍ እንደሚኖርባቸው መጠበቅ አለባቸው፤ ወታደሩም ምርኮን ከመከፋፈሉ በፊት ከባድ ውጊያ እንደሚያደርግ ሁሉ ከባድ ትግልን ማለፍ ይጠበቅባቸዋል። አይሁድ ከብዙ አስጨናቂዎች ቀንበር ነፃ ወጥተው ነበር፤ ይህ ደግሞ አማኞች ከሰይጣን ቀንበር ነፃ የሚወጡበት ጥላ ነበር።

የአማኞች ነፍስ ከኃጢአት ኃይልና እርኩሰት የሚነጻው፣ እንደ ማንጻት እሳት በሆነ በመንፈስ ቅዱስ ተጽዕኖ ይሆናል። እነዚህ ታላላቅ የቤተ ክርስቲያን ነገሮች በመሲሑ በዕማኑኤል ይፈጸማሉ። ህፃኑ ተወልዷል፤ ይህ እውነት ነበር፤ ቤተ ክርስቲያንም ክርስቶስ በሥጋ ከመምጣቱ በፊት፣ እርሱ ባደረገው ሥራ ተጠቅማለች። ይህም ስለ እርሱና ስለ መንግሥቱ የተነገረ ትንቢት ሲሆን፣ የእስራኤልን መጽናናት ይጠባበቁ የነበሩት ሰዎች በደስታ ያነቡት ነበር።

ይህ ሕፃን የተወለደው ለእኛ ለሰዎች፣ ለእኛ ለኃጢአተኞች፣ ከዓለም መጀመሪያ እስከ መጨረሻ ላሉት አማኞች ሁሉ ጥቅም ነው። እርሱ እግዚአብሔርና ሰው ስለሆነ፣ ድንቅ ተብሎ መጠራቱ ትክክል ነው።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG ነገር ግን ተጨንቃ ለነበረች ጨለማ አይሆንም። በመጀመሪያው ዘመን የዛብሎንንና የንፍታሌምን ምድር አቃለለ፤ በኋለኛው ዘመን ግን በዮርዳኖስ ማዶ በባሕር መንገድ ያለውን የአሕዛብን ገሊላ ያከብ… አማርኛ ENGNIV Nevertheless, there will be no more gloom for those who were in distress. In the past he humbled the land of Zebulun an… English BCV ግና ኣብ ጭንቂ ንዝነበረት ደጊም ፀልማት ኣይኸውንን፤ ኣብቲ ቐዳማይ ዘመን ንምድሪ ዛብሎንን ንምድሪ ንፍታሌምን ኣዋረደ። ብዳሕረዋይ ዘመን ግና፥ ብማዕዶ ዮርዳኖስ፥ ብመንገዲ ባሕሪ ዘላ ናይ … ትግርኛ GAZBIB Warri dhiphina keessa turan si'achi dukkana keessa hin jiraatan; inni bara durii biyya Zaabiloonii fi biyya Niftaalem g… Afaan Oromoo BCV GIZ ወኢይትባላሕ ዘተመንደበ እሰከ አመ ይበጽሕ ዕድሜሁ ለዝ; ዘንተ ፍጡነ ግበር ወፍጡነ ስተይ ብሔረ ዛብሎን ወምድረ ንፍታሌም ተረፈ ጰራልዩ ወማዕዶተ ዮርዳኖስ ዘገሊላ ዘአሕዛብ። giz GAZGAZ Warri dhiphina keessa turan si'achi dukkana keessa hin jiraatan; inni bara durii biyya Zaabiloonii fi biyya Niftaalem g… Afaan Oromoo BCV aksum ግና ኣብ ጭንቂ ንዝነበረት ደጊም ፀልማት ኣይኸውንን፤ ኣብቲ ቐዳማይ ዘመን ንምድሪ ዛብሎንን ንምድሪ ንፍታሌምን ኣዋረደ። ብዳሕረዋይ ዘመን ግና፥ ብማዕዶ ዮርዳኖስ፥ ብመንገዲ ባሕሪ ዘላ ናይ … ትግርኛ SWAHSUV Lakini yeye aliyekuwa katika dhiki hatakosa changamko. Hapo kwanza aliiingiza nchi ya Zabuloni na nchi ya Naftali katik… Kiswahili