ትንቢተ ኢሳይያስ 6

AMHNIVአማርኛ13 ጥቅሶች2:46 አዳምጥ
አዳምጥ 2:46 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ንጉሥ ዖዝያን በሞተበት ዓመት እግዚአብሔርን ከፍ ባለና በከበረ ዙፋን ላይ ተቀምጦ አየሁት፤ የልብሱም ዘርፍ ቤተ መቅደሱን ሞልቶት ነበር።

2ሱራፌልም ከእርሱ በላይ ቆመው ነበር፤ እያንዳንዳቸውም ስድስት ክንፍ ነበራቸው። በሁለት ክንፍ ፊታቸውን ይሸፍኑ ነበር፤ በሁለት ክንፍ እግራቸውን ይሸፍኑ ነበር፤ በሁለቱም ክንፍ ይበሩ ነበር፤

3እርስ በርሳቸው በመቀባበልም “ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ ምድር ሁሉ በክብሩ ተሞልታለችቃ ይሉ ነበር።

4ከድምፃቸው ጩኸት የተነሣ የመድረኩ መሠረት ተናወጠ፤ ቤተ መቅደሱም በጢስ ተሞላ።

5እኔም፣ “ከንፈሮቼ የረከሱብኝ ሰው ነኝ፤ የምኖረውም ከንፈሮቹ በረከሱበት ሕዝብ መካከል ነው፤ ዐይኖቼም ንጉሡን፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔርን አይተዋልና ጠፍቻለሁ፣ ወዮልኝ!” አልሁ።

6ከዚያም ከሱራፌል አንዱ፣ ከመሠዊያው ላይ የእሳት ፍም በጕጠት ወስዶ፣ ወደ እኔ እየበረረ መጣ።

7አፌንም በእሳቱ ነክቶ፣ “እነሆ፤ ይህ ከንፈሮችህን ነክቶአል፤ በደልህ ተወግዶልሃል፤ ኀጢአትህም ተሰርዮልሃል” አለኝ።

8ከዚያም የጌታ ድምፅ፣ “ማንን እልካለሁ? ማንስ ይሄድልናል?” ሲል ሰማሁት። እኔም፣ “እነሆኝ፤ እኔን ላከኝ” አልሁ።

9እርሱም እንዲህ አለኝ፤ “ወደዚህ ሕዝብ ሂድ፤ “ ‘መስማትን ትሰማላችሁ፤ ነገር ግን አታስተውሉም፤ ማየትንም ታያላችሁ፤ ነገር ግን ልብ አትሉም’ ብለህ ንገራቸው።

10የዚህን ሕዝብ ልብ አደንድን፤ ጆሮአቸውን ድፈን፤ ዐይኖቻቸውንም ክደን፤ ይህ ካልሆነማ፣ በዐይናቸው አይተው፣ በጆሮአቸው ሰምተው፣ በልባቸውም አስተውለው በመመለስ ይፈወሳሉ።”

11እኔም፣ “ጌታ ሆይ፤ ይህ የሚሆነው እስከ መቼ ነው?” አልሁት፤ እርሱም መልሶ እንዲህ አለኝ፤ “ከተሞች እስኪፈራርሱና፣ የሚኖሩባቸው እስኪያጡ፣ ቤቶችም ወና እስኪሆኑና፣ ምድርም ፈጽሞ ባድማ እስክትሆን ድረስ፤

12እግዚአብሔርም ሰዎችን እስከሚያርቅ፣ ምድሪቱም ጨርሶ ባዶ እስክትሆን፣

13ከዐሥር አንድ ሰው እንኳ በምድሪቱ ቢቀር፣ እርሱም ደግሞ ይጠፋል፤ ነገር ግን የኮምበልና የባሉጥ ዛፍ በተቈረጠ ጊዜ ጒቶ እንደሚቀር፣ ቅዱሱም ዘር እንዲሁ በምድሪቱ ጒቶ ሆኖ ይቀራል።”

ማብራሪያ

6:1-8 በዚህ ምሳሌያዊ ራእይ፣ መቅደሱ እስከ ቅድስተ ቅዱሳኑ ድረስ ተከፍቶ ይታያል። ነቢዩም ከቤተ መቅደሱ ውጭ ቆሞ፣ መለኮታዊው መገኘት በስርየት መቀመጫው ላይ፣ ከቃል ኪዳኑ ታቦት በላይ ከፍ ብሎ፣ በኪሩቤልና በሱራፌል መካከል ተቀምጦ ያያል፤ መለኮታዊውም ክብር መቅደሱን ሙሉ በሙሉ ሞልቶ ነበር። እግዚአብሔርን በዙፋኑ ላይ ተመልከቱ። ይህ ራእይ፣ ዮሐ 12:41 ላይ እንደተብራራው፣ ኢሳይያስ የክርስቶስን ክብር እንዳየና ስለ እርሱ እንደተናገረ ያሳያል፤ ይህም አዳኛችን አምላክ እንደሆነ ሙሉ ማረጋገጫ ነው። በክርስቶስ ኢየሱስ፣ እግዚአብሔር በጸጋ ዙፋን ላይ ተቀምጧል፤ በእርሱም ወደ ቅድስተ ቅዱሳን የሚወስደው መንገድ ክፍት ተደርጓል። የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ፣ በምድር ያለች ቤተ ክርስቲያኑን፣ በክብሩ ተሞልታ ተመልከቱ። የእርሱ ልብስ ዘርፍ (ጫፍ) መቅደሱን፣ መላውን ዓለም ሞልቶ ነበር፤ ምክንያቱም መላው ዓለም የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነው። ሆኖም ግን በእያንዳንዱ በተሰበረ ልብ ይኖራል።

የእርሱን መንግሥት የሚያገለግሉትን የተባረኩ አገልጋዮች ተመልከቱ። ከዙፋኑ በላይ ሱራፌል ተብለው የሚጠሩት ቅዱሳን መላእክት ቆመው ነበር፤ ሱራፌል ማለትም ‹የሚቃጠሉ› ማለት ነው። እነርሱም ለእግዚአብሔር ባላቸው ፍቅርና ለክብሩ ሲሉ በኃጢአት ላይ ባላቸው ቅንዓት ይቃጠላሉ። ሱራፌል ፊቶቻቸውን መሸፈናቸው፣ የእግዚአብሔርን ምክሮች፣ መንግሥት ወይም ተስፋዎች የተሰወሩትን ምክንያቶች ባይረዱም እንኳን፣ ለሁሉም የእግዚአብሔር ትእዛዛት ለመታዘዝ ዝግጁ መሆናቸውን ያውጃል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG ንጉሡ ዖዝያን በሞተበት ዓመት እግዚአብሔርን በረጅምና ከፍ ባለ ዙፋን ላይ ተቀምጦ አየሁት፥ የልብሱም ዘርፍ መቅደሱን ሞልቶት ነበር። አማርኛ ENGNIV In the year that King Uzziah died, I saw the Lord seated on a throne, high and exalted, and the train of his robe fille… English BCV በታ ንጉስ ኦዝያን ዝሞተላ ዓመት፥ ንእግዚኣብሄር ኣብ በሪኽን፥ ልዕል ኣብ ዝበለ ዙፋንን ተቐሚጡ ረአኽዎ፤ ዘፈር ልብሱ ኸዓ ነቲ ቤተ መቕደስ መሊእዎ ነበረ። ትግርኛ GAZBIB Bara Uziyaan mootichi du'e, gooftichi teessoo dheeraa fi ol ka'aa irra taa'ee andaarri uffata isaas mana qulqullummaa g… Afaan Oromoo BCV GIZ ወእምዝ በዓመት በዘ ሞተ ዖዝያን ንጉሥ ርኢክዎ ለእግዚአብሔር እንዘ ይነብር ዲበ መንበሩ ልዑል ወነዋኅ ወምሉእ ቤተ ስብሓቲሁ። giz GAZGAZ Bara Uziyaan mootichi du'e, gooftichi teessoo dheeraa fi ol ka'aa irra taa'ee andaarri uffata isaas mana qulqullummaa g… Afaan Oromoo BCV aksum በታ ንጉስ ኦዝያን ዝሞተላ ዓመት፥ ንእግዚኣብሄር ኣብ በሪኽን፥ ልዕል ኣብ ዝበለ ዙፋንን ተቐሚጡ ረአኽዎ፤ ዘፈር ልብሱ ኸዓ ነቲ ቤተ መቕደስ መሊእዎ ነበረ። ትግርኛ SWAHSUV Katika mwaka ule aliokufa mfalme Uzia nalimwona Bwana ameketi katika kiti cha enzi, kilicho juu sana na kuinuliwa sana,… Kiswahili