ትንቢተ ኢሳይያስ 6

AMHEVGአማርኛ13 ጥቅሶች2:36 አዳምጥ
አዳምጥ 2:36 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ንጉሡ ዖዝያን በሞተበት ዓመት እግዚአብሔርን በረጅምና ከፍ ባለ ዙፋን ላይ ተቀምጦ አየሁት፥ የልብሱም ዘርፍ መቅደሱን ሞልቶት ነበር።

2ሱራፌልም ከእርሱ በላይ ቆመው ነበር፥ ለእያንዳንዱም ስድስት ክንፍ ነበረው፤ በሁለት ክንፍ ፊቱን ይሸፍን ነበር፥ በሁለቱም ክንፍ እግሮቹን ይሸፍን ነበር፥ በሁለቱም ክንፍ ይበር ነበር።

3አንዱም ለአንዱ፦ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ ምድር ሁሉ ከክብሩ ተሞልታለች፡ እያለ ይጮኽ ነበር።

4የመድረኩም መሠረት ከጭዋኺው ድምፅ የተነሣ ተናወጠ፥ ቤቱንም ጢስ ሞላበት።

5እኔም፦ ከንፈሮቼ የረከሱብኝ ሰው በመሆኔ፥ ከንፈሮቻቸውም በረከሱባቸው ሕዝብ መካከል በመቀመጤ ዓይኖቼ የሠራዊትን ጌታ ንጉሡን እግዚአብሔርን ስለ አዩ ጠፍቻለሁና ወዮልኝ! አልሁ።

6ከሱራፌልም አንዱ እየበረረ ወደ እኔ መጣ፥ በእጁም ከመሠዊያው በጕጠት የወሰደው ፍም ነበረ።

7አፌንም ዳሰሰበትና፦ እነሆ፥ ይህ ከንፈሮችህን ነክቶአል፤ በደልህም ከአንተ ተወገደ፥ ኃጢአትህም ተሰረየልህ፡ አለኝ።

8የጌታንም ድምፅ፦ ማንን እልካለሁ? ማንስ ይሄድልናል? ሲል ሰማሁ። እኔም፦ እነሆኝ፥ እኔን ላከኝ፡ አልሁ።

9እርሱም፦ ሂድ፥ ይህን ሕዝብ፦ መስማትን ትሰማላችሁ አታስተውሉምም፤ ማየትንም ታያላችሁ አትመለከቱምም፡ በላቸው።

10በዓይናቸው እንዳያዩ፥ በጆሮአቸውም እንዳይሰሙ፥ በልባቸውም እንዳያስተውሉ፥ ተመልሰውም እንዳይፈወሱ፥ የዚህን ሕዝብ ልብ አደንድን፥ ጆሮአቸውንም አደንቍር፥ ዓይናቸውንም ጨፍን፡ አለኝ።

11እኔም፦ ጌታ ሆይ፥ እስከ መቼ ድረስ ነው? አልሁ። እርሱም መልሶ እንዲህ አለ፦ ከተሞች የሚኖርባቸውን አጥተው እስኪፈርሱ ድረስ፥ ቤቶችም ሰው አልቦ እስኪሆኑ ምድርም ፈጽሞ ባድማ ሆና እስክትቀር ድረስ፥

12እግዚአብሔርም ሰዎችን እስኪያርቅ፥ በምድርም መካከል ውድማው መሬት እስኪበዛ ድረስ ነው።

13በእርስዋም ዘንድ አሥረኛ እጅ ቀርቶ እንደ ሆነ እርሱ ደግሞ ይቃጠላል፤ በተቈረጡ ጊዜ ጉቶቻቸው እንደ ቀሩ እንደ ግራርና እንደ ኮምበል ዛፍ ሆኖ፥ ጉቶው የተቀደሰ ዘር ይሆናል።

ማብራሪያ

6:1-8 በዚህ ምሳሌያዊ ራእይ፣ መቅደሱ እስከ ቅድስተ ቅዱሳኑ ድረስ ተከፍቶ ይታያል። ነቢዩም ከቤተ መቅደሱ ውጭ ቆሞ፣ መለኮታዊው መገኘት በስርየት መቀመጫው ላይ፣ ከቃል ኪዳኑ ታቦት በላይ ከፍ ብሎ፣ በኪሩቤልና በሱራፌል መካከል ተቀምጦ ያያል፤ መለኮታዊውም ክብር መቅደሱን ሙሉ በሙሉ ሞልቶ ነበር። እግዚአብሔርን በዙፋኑ ላይ ተመልከቱ። ይህ ራእይ፣ ዮሐ 12:41 ላይ እንደተብራራው፣ ኢሳይያስ የክርስቶስን ክብር እንዳየና ስለ እርሱ እንደተናገረ ያሳያል፤ ይህም አዳኛችን አምላክ እንደሆነ ሙሉ ማረጋገጫ ነው። በክርስቶስ ኢየሱስ፣ እግዚአብሔር በጸጋ ዙፋን ላይ ተቀምጧል፤ በእርሱም ወደ ቅድስተ ቅዱሳን የሚወስደው መንገድ ክፍት ተደርጓል። የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ፣ በምድር ያለች ቤተ ክርስቲያኑን፣ በክብሩ ተሞልታ ተመልከቱ። የእርሱ ልብስ ዘርፍ (ጫፍ) መቅደሱን፣ መላውን ዓለም ሞልቶ ነበር፤ ምክንያቱም መላው ዓለም የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነው። ሆኖም ግን በእያንዳንዱ በተሰበረ ልብ ይኖራል።

የእርሱን መንግሥት የሚያገለግሉትን የተባረኩ አገልጋዮች ተመልከቱ። ከዙፋኑ በላይ ሱራፌል ተብለው የሚጠሩት ቅዱሳን መላእክት ቆመው ነበር፤ ሱራፌል ማለትም ‹የሚቃጠሉ› ማለት ነው። እነርሱም ለእግዚአብሔር ባላቸው ፍቅርና ለክብሩ ሲሉ በኃጢአት ላይ ባላቸው ቅንዓት ይቃጠላሉ። ሱራፌል ፊቶቻቸውን መሸፈናቸው፣ የእግዚአብሔርን ምክሮች፣ መንግሥት ወይም ተስፋዎች የተሰወሩትን ምክንያቶች ባይረዱም እንኳን፣ ለሁሉም የእግዚአብሔር ትእዛዛት ለመታዘዝ ዝግጁ መሆናቸውን ያውጃል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV In the year that King Uzziah died, I saw the Lord seated on a throne, high and exalted, and the train of his robe fille… English BCV በታ ንጉስ ኦዝያን ዝሞተላ ዓመት፥ ንእግዚኣብሄር ኣብ በሪኽን፥ ልዕል ኣብ ዝበለ ዙፋንን ተቐሚጡ ረአኽዎ፤ ዘፈር ልብሱ ኸዓ ነቲ ቤተ መቕደስ መሊእዎ ነበረ። ትግርኛ GAZBIB Bara Uziyaan mootichi du'e, gooftichi teessoo dheeraa fi ol ka'aa irra taa'ee andaarri uffata isaas mana qulqullummaa g… Afaan Oromoo BCV GIZ ወእምዝ በዓመት በዘ ሞተ ዖዝያን ንጉሥ ርኢክዎ ለእግዚአብሔር እንዘ ይነብር ዲበ መንበሩ ልዑል ወነዋኅ ወምሉእ ቤተ ስብሓቲሁ። giz GAZGAZ Bara Uziyaan mootichi du'e, gooftichi teessoo dheeraa fi ol ka'aa irra taa'ee andaarri uffata isaas mana qulqullummaa g… Afaan Oromoo BCV aksum በታ ንጉስ ኦዝያን ዝሞተላ ዓመት፥ ንእግዚኣብሄር ኣብ በሪኽን፥ ልዕል ኣብ ዝበለ ዙፋንን ተቐሚጡ ረአኽዎ፤ ዘፈር ልብሱ ኸዓ ነቲ ቤተ መቕደስ መሊእዎ ነበረ። ትግርኛ AMHNIV ንጉሥ ዖዝያን በሞተበት ዓመት እግዚአብሔርን ከፍ ባለና በከበረ ዙፋን ላይ ተቀምጦ አየሁት፤ የልብሱም ዘርፍ ቤተ መቅደሱን ሞልቶት ነበር። አማርኛ SWAHSUV Katika mwaka ule aliokufa mfalme Uzia nalimwona Bwana ameketi katika kiti cha enzi, kilicho juu sana na kuinuliwa sana,… Kiswahili