ትንቢተ ኢሳይያስ 66

AMHEVGአማርኛ24 ጥቅሶች5:18 አዳምጥ
አዳምጥ 5:18 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሰማይ ዙፋኔ ነው፥ ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፤ የምትሠሩልኝ ቤት ምን ዓይነት ነው? የማርፍበትስ ስፍራ ምንድር ነው?

2እነዚህን ሁሉ እጄ ሠርታለችና እነዚህ ሁሉ የእኔ ናቸው ይላል እግዚአብሔር፤ ነገር ግን ወደዚህ ወደ ትሑት፥ መንፈሱም ወደ ተሰበረ፥ በቃሌም ወደሚንቀጠቀጥ ሰው እመለከታለሁ።

3በሬን የሚያርድልኝ ሰውን እንደሚገድል ነው፤ ጠቦትንም የሚሠዋ የውሻውን አንገት እንደሚሰብር ነው፤ የእህልን ቍርባን የሚያቀርብ የእርያን ደም እንደሚያቀርብ ነው፤ ዕጣንን የሚያጥን ጣዖትን እንደሚባርክ ነው። እነዚህ የገዛ መንገዳቸውን መረጡ፤ ነፍሳቸውም በርኵሰታቸው ደስ ይላታል፤

4እኔ ደግሞ የተሳለቀባቸውን እመርጣለሁ፥ የፈሩትንም ነገር አመጣባቸዋለሁ፤ በፊቴ ክፉ ነገርን አደረጉ፥ ያልወደድሁትንም መረጡ እንጂ በጠራሁ ጊዜ አልመለሱልኝምና፥ በተናገርሁም ጊዜ አልሰሙኝምና።

5በቃሉ የምትንቀጠቀጡ ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፦ የጠሉአችሁ ስለ ስሜም ያባረሩአችሁ ወንድሞቻችሁ፦ ደስታችሁን እናይ ዘንድ እግዚአብሔር ይክበር፡ ብለዋል፤ ነገር ግን ያፍራሉ።

6የጩኸት ድምፅ ከከተማ፥ ድምፅም ከመቅደስ፥ በጠላቶቹ ላይ ፍዳን የሚያመጣ የእግዚአብሔር ድምፅ ተሰምቶአል።

7ሳታምጥ ወለደች፤ ምጥም ሳያገኛት ወንድ ልጅን ወለደች።

8ከቶ እንዲህ ያለ ነገር ማን ሰምቶአል? እንዲህስ ያለ ነገር ማን አይቶአል? በውኑ አገር በአንድ ቀን ታምጣለችን? ወይስ በአንድ ጊዜ ሕዝብ ይወለዳልን? ጽዮን እንዳማጠች ወዲያው ልጆችዋን ወልዳለችና።

9በውኑ ወደ መውለድ የማደርስ እኔ አላስወልድምን? ይላል እግዚአብሔር፤ የማስወልድስ ማኅፀንን እኔ እዘጋለሁን? ይላል አምላክሽ።

10እናንተ የምትወድዱአት ሁሉ፥ ከኢየሩሳሌም ጋር ሐሤትን አድርጉ፥ ስለ እርስዋም ደስ ይበላችሁ፤ እናንተም የምታለቅሱላት ሁሉ፥ ከእርስዋ ጋር በደስታ ሐሤትን አድርጉ፥

11ትጠቡ ዘንድ ከማጽናናትዋም ጡት ትጠግቡ ዘንድ፤ እጅግ ጠጥታችሁ በክብርዋ ሙላት ደስ ይላችሁ ዘንድ።

12እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ እነሆ፥ ሰላምን እንደ ወንዝ፥ የአሕዛብንም ክብር እንደሚጐርፍ ፈሳሽ እመልስላታለሁ፤ ከዚያም ትጠባላችሁ፥ በጫንቃ ላይ ይሸከሙአችኋል በጕልበትም ላይ እያስቀመጡ ያቀማጥሉአችኋል።

13እናት ልጅዋን እንደምታጽናና እንዲሁ አጽናናችኋለሁ፥ በኢየሩሳሌምም ውስጥ ትጽናናላችሁ።

14ታያላችሁ፥ ልባችሁም ሐሤት ታደርጋለች፥ አጥንታችሁም እንደ ለምለም ሣር ትበቅላለች፤ የእግዚአብሔርም እጅ ለሚፈሩት ትታወቃለች፥ በጠላቶቹም ላይ ይቈጣል።

15እነሆ፥ እግዚአብሔር መዓቱን በቍጣ፥ ዘለፋውንም በእሳት ነበልባል ይመልስ ዘንድ ከእሳት ጋር ይመጣል፥ ሰረገሎቹም እንደ ዐውሎ ነፋስ ይሆናሉ።

16እግዚአብሔርም በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ በእሳትና በሰይፉ ይፈርዳል፤ በእግዚአብሔርም ተወግተው የሞቱት ይበዛሉ።

17በመካከላቸው ያለውን አንዱን ተከትለው ወደ ገነቱ ይገቡ ዘንድ ሰውነታቸውን የሚቀድሱና የሚያነጹ፥ የእሪያንም ሥጋ አስጸያፊ ነገርንም አይጥንም የሚበሉ በአንድነት ይጠፋሉ፥ ይላል እግዚአብሔር።

18ሥራቸውንና አሳባቸውን አውቄአለሁና፤ አሕዛብንና ልሳናትን ሁሉ የምሰበስብበት ጊዜ ይደርሳል፥ እነርሱም ይመጣሉ ክብሬንም ያያሉ።

19በመካከላቸውም ምልክት አደርጋለሁ፥ ከእነርሱም የዳኑትን ዝናዬን ወዳልሰሙ፥ ክብሬንም ወዳላዩ ወደ አሕዛብ ወደ ተርሴስ ወደ ፉጥ ወደ ሉድ ወደ ሞሳሕ ወደ ቶቤል ወደ ያዋን በሩቅ ወዳሉ ደሴቶች እልካቸዋለሁ፥ በአሕዛብም መካከል ክብሬንም ይናገራሉ።

20የእስራኤል ልጆች ቍርባናቸውን በጥሩ ዕቃ አድርገው ወደ እግዚአብሔር ቤት እንደሚያመጡ፥ እንዲሁ ለእግዚአብሔር ቍርባን ይሆን ዘንድ ወንድሞቻችሁን ሁሉ፥ በፈረሶችና በሰረገሎች፥ በአልጋዎችና በበቅሎች በጠያር ግመሎችም ላይ አድርገው፥ ከአሕዛብ ሁሉ ወደ ተቀደሰው ተራራዬ ወደ ኢየሩሳሌም ያመጡአቸዋል፥ ይላል እግዚአብሔር።

21ካህናትና ሌዋውያን እንዲሆኑ ከእነርሱ እወስዳለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።

22እኔ የምሠራቸው አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር ከፊቴ ጸንተው እንደሚኖሩ፥ እንዲሁ ዘራችሁና ስማችሁ ጸንተው ይኖራሉ፥ ይላል እግዚአብሔር።

23እንዲህ ይሆናል፤ በየመባቻውና በየሰንበቱ ሥጋ ለባሽ ሁሉ በፊቴ ይሰግድ ዘንድ ዘወትር ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር።

24ወጥተውም በእኔ ያመፁብኝን ሰዎች ሬሳቸውን ያያሉ፤ ትላቸው አይሞትምና፥ እሳታቸውም አይጠፋምና፤ ለሥጋ ለባሽም ሁሉ አስጸያፊ ነገር ይሆናሉ።

ማብራሪያ

66:1-4 አይሁድ በመቅደሳቸው እጅግ ይኮሩ ነበር። ነገር ግን ዘላለማዊው አእምሮ በሰው እጅ በተሠራ ቤት ምን እርካታ ያገኛል? እግዚአብሔር የራሱ የሆኑ ሰማይና ምድር አሉት፤ የሰው እጅ የሠሯቸው መቅደሶችም አሉ። ነገር ግን እነዚህን ትቶ፣ በመንፈሱ ለሚደኸይና ቁም ነገርተኛ ለሆነ ሰው፣ ራሱን ዝቅ ለሚያደርግና ራሱን ለሚክድ፣ ልቡም ስለ ኃጢአት በእውነት ለሚያዝን በጸጋ ለማየት ይመርጣል። እንዲህ ያለው ልብ ለእግዚአብሔር ሕያው መቅደስ ነው። የክፉዎች መስዋዕትነት ተቀባይነት የሌለው ብቻ ሳይሆን ለእግዚአብሔር ታላቅ በደል ነው። በሕጉ መሠረት አሁን መስዋዕት የሚያቀርብ ሰው፣ የክርስቶስን መስዋዕትነት ሙሉ በሙሉ ውድቅ እንደሚያደርግ ያህል ነው። ዕጣን የሚያጥን ሰው፣ የክርስቶስን ምልጃ ዕጣን ይንቃል፣ ጣዖትን እንደባረከም ያህል ነው። ሰዎች ራሳቸውን በሚያታልሉበት ከንቱ መታመን ይታለላሉ። የማያምኑ ልቦችና ያልነጹ ሕሊናዎች፣ የራሳቸው ፍርሃት በእነርሱ ላይ ከመምጣት ውጪ ሊያሳዝናቸው ሌላ ምንም አያስፈልጋቸውም። ሰዎች የክርስቶስን ክህነት፣ ስርየትና ምልጃ የሚተኩበት ማንኛውም ነገር፣ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ ሆኖ ይገኛል።

66:5-14 ነቢዩ በእግዚአብሔር ቃል ፊት ለሚንቀጠቀጡት ሰዎች ለመጽናናትና ለማበረታታት ዞሯል። እግዚአብሔር ይገለጣል፥ ይህም ለትሑት አማኝ ደስታ፣ ለግብዞችና ለአሳዳጆች ግን እፍረት ይሆናል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV This is what the Lord says: “Heaven is my throne, and the earth is my footstool. Where is the house you will build for … English BCV እግዚኣብሄር ከምዙይ ይብል ኣሎ፦ “ሰማይ ዙፋነይ እዩ፤ ምድሪ ኸዓ መርገፂ እግረይ እያ። እቲ ንስኻትኩም እትሰርሑለይ ቤት ደኣ፥ ከመይ ዝበለ እዩ? እቲ ኣነ ዝዓርፈሉ ስፍራኸ፥ ከመይ ዝበለ … ትግርኛ GAZBIB Waaqayyo,“Bantiin waaqaa teessoo koo ti, laftis ejjeta miilla kootii ti, eessatti mana anaaf ijaartu” Iddoon boqonnaa k… Afaan Oromoo BCV GIZ ከመዝ ይቤ እግዚአብሔር፦ ሰማይኒ መንበርየ ወምድርኒ መከየደ እገርየ፤ አየኑ ቤተ ተሐንጹ ሊተ ወአይኑ ማኅደረ ምዕራፍየ? giz GAZGAZ Waaqayyo,“Bantiin waaqaa teessoo koo ti, laftis ejjeta miilla kootii ti, eessatti mana anaaf ijaartu” Iddoon boqonnaa k… Afaan Oromoo BCV aksum እግዚኣብሄር ከምዙይ ይብል ኣሎ፦ “ሰማይ ዙፋነይ እዩ፤ ምድሪ ኸዓ መርገፂ እግረይ እያ። እቲ ንስኻትኩም እትሰርሑለይ ቤት ደኣ፥ ከመይ ዝበለ እዩ? እቲ ኣነ ዝዓርፈሉ ስፍራኸ፥ ከመይ ዝበለ … ትግርኛ AMHNIV እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ሰማይ ዙፋኔ ነው፤ ምድርም የእግሬ ማረፊያ ናት፤ ታዲያ የምትሠሩልኝ ቤት፣ የማርፍበትስ ስፍራ የቱ ነው? አማርኛ SWAHSUV Bwana asema hivi, Mbingu ni kiti changu cha enzi, na dunia ni mahali pa kuweka miguu yangu; mtanijengea nyumba ya namna… Kiswahili