ትንቢተ ኢሳይያስ 66

AMHNIVአማርኛ24 ጥቅሶች6:15 አዳምጥ
አዳምጥ 6:15 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ሰማይ ዙፋኔ ነው፤ ምድርም የእግሬ ማረፊያ ናት፤ ታዲያ የምትሠሩልኝ ቤት፣ የማርፍበትስ ስፍራ የቱ ነው?

2እነዚህን ነገሮች ሁሉ እጄ አልሠራችምን? እንዲገኙስ ያደረግሁ እኔ አይደለሁምን?” ይላል እግዚአብሔር። “ነገር ግን እኔ ወደዚህ፣ ትሑት ወደ ሆነና መንፈሱ ወደ ተሰበረ፣ በቃሌም ወደሚንቀጠቀጥ ሰው እመለከታለሁ።

3ነገር ግን ወይፈን የሚሰዋልኝ፣ ሰው እንደሚገድል ነው፤ የበግ ጠቦት የሚያቀርብልኝ፣ የውሻ ዐንገት እንደሚሰብር ሰው ነው፤ የእህል ቍርባን የሚያዘጋጅልኝ፣ የዕሪያ ደም እንደሚያቀርብልኝ ሰው ነው፤ የመታሰቢያን ዕጣን የሚያጥንልኝም፣ ጣዖትን እንደሚያመልክ ሰው ነው፤ የገዛ መንገዳቸውን መርጠዋል፤ ነፍሳቸውም በርኵሰታቸው ደስ ይላታል።

4ስለዚህ ችግር እንዲደርስባቸው አደርጋለሁ፤ የፈሩትንም አመጣባቸዋለሁ፤ በተጣራሁ ጊዜ የመለሰ፣ በተናገርሁ ጊዜ ያደመጠ ሰው የለምና። በፊቴ ክፉ ነገር አደረጉ፤ የሚያስከፋኝንም መረጡ።”

5እናንት በቃሉ የምትንቀጠቀጡ፣ ይህን የእግዚአብሔር ቃል ስሙ፤ “እናንት ወንድሞቻችሁ የጠሏችሁ፣ ስለ ስሜም አውጥተው የጣሏችሁ፣ ‘እስቲ እግዚአብሔር ይክበርና፣ የእናንተን ደስታ እንይ’ አሏችሁ፤ ይሁን እንጂ ማፈራቸው አይቀርም።

6ያን የጩኸት ድምፅ ከከተማው ስሙ! ያን ጫጫታ ከቤተ መቅደሱ ስሙ! ይኸውም የእግዚአብሔር ድምፅ ነው፤ ለጠላቶቹም የሚገባቸውን ሁሉ ይከፍላቸዋል።

7“ከማማጧ በፊት፣ ትወልዳለች፤ በምጥ ጣር ከመያዟ በፊት፣ ወንድ ልጅ ትገላገላለች።

8እንዲህ ያለ ነገር ማን ሰምቶ ያውቃል? እንዲህ ያለ ነገርስ ማን አይቶ ያውቃል? አገር በአንድ ጀምበር ይፈጠራልን? ወይስ ሕዝብ በቅጽበት ይገኛል? ጽዮንን ምጥ ገና ሲጀምራት፣ ልጆቿን ወዲያውኑ ትወልዳለች።

9ሊወለድ የተቃረበውን፣ እንዳይወለድ አደርጋለሁን?” ይላል እግዚአብሔር። “በሚገላገሉበት ጊዜስ፣ ማሕፀን እዘጋለሁን?” ይላል አምላክሽ።

10“ወዳጆቿ የሆናችሁ ሁሉ፣ ከኢየሩሳሌም ጋር ደስ ይበላችሁ፤ ስለ እርሷም ሐሤት አድርጉ፤ ለእርሷ ያለቀሳችሁ ሁሉ፣ ከእርሷ ጋር እጅግ ደስ ይበላችሁ።

11ከሚያጽናኑ ጡቶቿ፣ ትጠባላችሁ፤ ትረካላችሁም፤ እስክትረኩም ትጠጣላችሁ፤ በተትረፈረፈ ሀብቷም ትደሰታላችሁ።”

12እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እነሆ፤ ሰላምን እንደ ወንዝ ውሃ አፈስላታለሁ፤ የመንግሥታትንም ብልጥግና እንደ ጅረት ውሃ አጐርፍላታለሁ፤ ትጠባላችሁ፤ በዕቅፏም ትያዛላችሁ፤ በጭኖቿም ላይ ትፈነድቃላችሁ።

13እናት ልጇን እሹሩሩ እንደምትል፣ እኔም እናንተን እሹሩሩ እላችኋለሁ፤ በኢየሩሳሌምም ትጽናናላችሁ።

14ይህን ስታዩ፣ ልባችሁ ሐሤት ያደርጋል፤ ዐጥንቶቻችሁም እንደ ሣር ይለመልማሉ፤ የእግዚአብሔር እጅ ከባሮቹ ጋር መሆኑ ይታወቃል፤ ቊጣው ግን በጠላቶቹ ላይ ይገለጣል።

15እነሆ፤ እግዚአብሔር በእሳት ነበልባል ይመጣል፤ ሠረገሎቹም እንደ ዐውሎ ነፋስ ናቸው፤ ንዴቱን በቍጣ፣ ተግሣጹንም በእሳት ነበልባል ይገልጣል።

16በእሳትና በሰይፍ፣ እግዚአብሔር ፍርዱን በሰው ሁሉ ላይ ያመጣል፤ በእግዚአብሔር ሰይፍ የሚታረዱት ብዙ ይሆናሉ።

17“ወደ አትክልት ቦታዎች ለመሄድና ከተክሎቹ አንዱን ለማምለክ ራሳቸውን የሚቀድሱና የሚያነጹ፣ የዕሪያዎችንና የዐይጦችን ሥጋ፣ የረከሱ ነገሮችንም የሚበሉ ሁሉ የመጨረሻ ፍርዳቸውን በአንድነት ይቀበላሉ” ይላል እግዚአብሔር።

18“እኔም ሥራቸውንና ሐሳባቸውን ስለማውቅ፣ መንግሥታትንና ልሳናትን ሁሉ ልሰበስብ እመጣለሁ፤ እነርሱም መጥተው ክብሬንም ያያሉ።

19“በመካከላቸው ምልክት አደርጋለሁ፤ ከእነርሱም የተረፉትን አንዳንዶቹን ወደ አሕዛብ ወደ ተርሴስ፣ ወደ ፉጥ፣ ወደ ታወቁት ቀስተኞች ወደ ሉድ፣ ወደ ቶባልና ያዋን እንዲሁም ዝናዬን ወዳልሰሙትና ክብሬን ወዳላዩት ራቅ ወዳሉት ደሴቶች እልካቸዋለሁ፤ በሕዝቦችም መካከል ክብሬን ይናገራሉ።

20ለእግዚአብሔር ቍርባን እንዲሆኑ ወንድሞቻችሁን ሁሉ ከየመንግሥታቱ ወደ ተቀደሰው ተራራዬ ወደ ኢየሩሳሌም በፈረስ፣ በሠረገላና በጋሪ፣ በበቅሎና በግመል ያመጧቸዋል” ይላል እግዚአብሔር። “እስራኤላውያን የእህል ቊርባናቸውን በሥርዐቱ መሠረት በነጹ ዕቃዎች ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደሚያቀርቡ እነዚህንም ያቀርቧቸዋል።

21እኔም ካህናትና ሌዋውያን ይሆኑ ዘንድ አንዳንዶቹን እመርጣቸዋለሁ” ይላል እግዚአብሔር።

22“እኔ የምሠራቸው አዲስ ሰማያትና አዲስ ምድር በፊቴ ጸንተው እንደሚኖሩ፣ የእናንተና የዘራችሁ ስም እንደዚሁ ጸንቶ ይኖራል” ይላል እግዚአብሔር፤

23“ከአንዱ ወር መባቻ እስከ ሌላው፣ እንዲሁም ከአንዱ ሰንበት እስከ ሌላው፣ የሰው ልጅ ሁሉ በፊቴ ሊሰግድ ይመጣል” ይላል እግዚአብሔር፤

24“ወጥተውም በእኔ ላይ ያመፁትን ሰዎች ሬሳ ያያሉ፤ ትላቸው አይሞትም፤ እሳታቸው አይጠፋም፤ ለሰውም ዘር ሁሉ አስጸያፊ ይሆናሉ።”

ማብራሪያ

66:1-4 አይሁድ በመቅደሳቸው እጅግ ይኮሩ ነበር። ነገር ግን ዘላለማዊው አእምሮ በሰው እጅ በተሠራ ቤት ምን እርካታ ያገኛል? እግዚአብሔር የራሱ የሆኑ ሰማይና ምድር አሉት፤ የሰው እጅ የሠሯቸው መቅደሶችም አሉ። ነገር ግን እነዚህን ትቶ፣ በመንፈሱ ለሚደኸይና ቁም ነገርተኛ ለሆነ ሰው፣ ራሱን ዝቅ ለሚያደርግና ራሱን ለሚክድ፣ ልቡም ስለ ኃጢአት በእውነት ለሚያዝን በጸጋ ለማየት ይመርጣል። እንዲህ ያለው ልብ ለእግዚአብሔር ሕያው መቅደስ ነው። የክፉዎች መስዋዕትነት ተቀባይነት የሌለው ብቻ ሳይሆን ለእግዚአብሔር ታላቅ በደል ነው። በሕጉ መሠረት አሁን መስዋዕት የሚያቀርብ ሰው፣ የክርስቶስን መስዋዕትነት ሙሉ በሙሉ ውድቅ እንደሚያደርግ ያህል ነው። ዕጣን የሚያጥን ሰው፣ የክርስቶስን ምልጃ ዕጣን ይንቃል፣ ጣዖትን እንደባረከም ያህል ነው። ሰዎች ራሳቸውን በሚያታልሉበት ከንቱ መታመን ይታለላሉ። የማያምኑ ልቦችና ያልነጹ ሕሊናዎች፣ የራሳቸው ፍርሃት በእነርሱ ላይ ከመምጣት ውጪ ሊያሳዝናቸው ሌላ ምንም አያስፈልጋቸውም። ሰዎች የክርስቶስን ክህነት፣ ስርየትና ምልጃ የሚተኩበት ማንኛውም ነገር፣ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ ሆኖ ይገኛል።

66:5-14 ነቢዩ በእግዚአብሔር ቃል ፊት ለሚንቀጠቀጡት ሰዎች ለመጽናናትና ለማበረታታት ዞሯል። እግዚአብሔር ይገለጣል፥ ይህም ለትሑት አማኝ ደስታ፣ ለግብዞችና ለአሳዳጆች ግን እፍረት ይሆናል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሰማይ ዙፋኔ ነው፥ ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፤ የምትሠሩልኝ ቤት ምን ዓይነት ነው? የማርፍበትስ ስፍራ ምንድር ነው? አማርኛ ENGNIV This is what the Lord says: “Heaven is my throne, and the earth is my footstool. Where is the house you will build for … English BCV እግዚኣብሄር ከምዙይ ይብል ኣሎ፦ “ሰማይ ዙፋነይ እዩ፤ ምድሪ ኸዓ መርገፂ እግረይ እያ። እቲ ንስኻትኩም እትሰርሑለይ ቤት ደኣ፥ ከመይ ዝበለ እዩ? እቲ ኣነ ዝዓርፈሉ ስፍራኸ፥ ከመይ ዝበለ … ትግርኛ GAZBIB Waaqayyo,“Bantiin waaqaa teessoo koo ti, laftis ejjeta miilla kootii ti, eessatti mana anaaf ijaartu” Iddoon boqonnaa k… Afaan Oromoo BCV GIZ ከመዝ ይቤ እግዚአብሔር፦ ሰማይኒ መንበርየ ወምድርኒ መከየደ እገርየ፤ አየኑ ቤተ ተሐንጹ ሊተ ወአይኑ ማኅደረ ምዕራፍየ? giz GAZGAZ Waaqayyo,“Bantiin waaqaa teessoo koo ti, laftis ejjeta miilla kootii ti, eessatti mana anaaf ijaartu” Iddoon boqonnaa k… Afaan Oromoo BCV aksum እግዚኣብሄር ከምዙይ ይብል ኣሎ፦ “ሰማይ ዙፋነይ እዩ፤ ምድሪ ኸዓ መርገፂ እግረይ እያ። እቲ ንስኻትኩም እትሰርሑለይ ቤት ደኣ፥ ከመይ ዝበለ እዩ? እቲ ኣነ ዝዓርፈሉ ስፍራኸ፥ ከመይ ዝበለ … ትግርኛ SWAHSUV Bwana asema hivi, Mbingu ni kiti changu cha enzi, na dunia ni mahali pa kuweka miguu yangu; mtanijengea nyumba ya namna… Kiswahili