ትንቢተ ኢሳይያስ 63

AMHNIVአማርኛ19 ጥቅሶች3:54 አዳምጥ
አዳምጥ 3:54 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ይህ ከኤዶም፣ ቀይ የተነከረ መጐናጸፊያ ለብሶ ከባሶራ የሚመጣ ማን ነው? ይህ ክብርን የተጐናጸፈ፣ በኀይሉ ታላቅነት እየተራመደ የሚመጣውስ ማን ነው? “በጽድቅ የምናገር፣ ለማዳንም ኀይል ያለኝ እኔው ነኝ።”

2መጐናጸፊያህ፣ ለምን በወይን መጭመቂያ ወይን እንደሚረግጡ ሰዎች ልብስ ቀላ?

3“እኔ በመጭመቂያው ወይኑን ብቻዬን ረገጥሁ፤ ከመንግሥታት ማንም ከእኔ ጋር አልነበረም፤ በቍጣዬ ረገጥኋቸው፤ በመዓቴም ጨፈለቅኋቸው፤ ደማቸው በመጐናጸፊያዬ ላይ ተረጭቶአል፤ ልብሴንም በክዬዋለሁ።

4የበቀል ቀን በልቤ አለ፤ የምቤዥበትም ዓመት ደርሶአል።

5ተመለከትሁ፤ የሚረዳ ግን አልነበረም፤ የሚያግዝ ባለመኖሩም ተገረምሁ፤ ስለዚህ የገዛ ክንዴ ድነትን አመጣልኝ፤ የገዛ ቊጣዬም አጸናኝ፤

6መንግሥታትን በቍጣዬ ረጋገጥሁ፤ በመዓቴም አሰከርኋቸው፤ ደማቸውንም በምድር ላይ አፈሰስሁ።”

7የእግዚአብሔርን ቸርነት፣ እግዚአብሔር ስላደረገልን ሁሉ፣ ስለሚመሰገንበት ሥራው፣ እንደ ፍቅሩና እንደ ቸርነቱ መጠን፣ ለእስራኤል ቤት ያደረገውን፣ አዎን፣ ስላደረገው መልካም ነገር እናገራለሁ።

8እርሱም፣ “ርግጥ ነው፤ እነርሱ ሕዝቤ ናቸው፤ የማይዋሹኝ ወንዶች ልጆቼ ናቸው” አለ። ስለዚህም አዳኝ ሆነላቸው።

9በጭንቃቸው ሁሉ ተጨነቀ፤ የፊቱም መልአክ አዳናቸው፤ በፍቅሩና በምሕረቱ ዋጃቸው፤ በቀደመው ዘመን ሁሉ አነሣቸው፤ ተሸከማቸውም።

10እነርሱ ግን ዐመፁ፤ ቅዱስ መንፈሱንም አሳዘኑ፤ ስለዚህ ተመልሶ ጠላት ሆናቸው፤ እርሱ ራሱ ተዋጋቸው።

11ከዚያም ሕዝቡ የጥንቱን ዘመን፣ የሙሴንና የሕዝቡን ጊዜ እንዲህ በማለት አስታወሱ፤ የበጎቹን እረኛ፣ ከባሕሩ ያወጣቸው እርሱ የት አለ? ቅዱስ መንፈሱንም፣ በመካከላቸው ያኖረ እርሱ የት አለ?

12የከበረው ኀያል ክንድ፣ በሙሴ ቀኝ እጅ ላይ እንዲያርፍ አደረገ፤ ለራሱ የዘላለም ዝና እንዲሆንለት፣ ውሆችን በፊታቸው ከፈለ።

13ፈረስ በምድረ በዳ እንደሚያልፍ ሁሉ፣ እነርሱንም በጥልቁ ውስጥ አሳልፎ መራቸው፤ ስለዚህም አልተሰናከሉም፤

14ወደ ሸለቆ እንደሚወርድ የከብት መንጋ፣ በእግዚአብሔር መንፈስ ዕረፍት ተሰጣቸው። ሕዝብህን በዚህ ሁኔታ የመራሃቸው፣ ስምህን የከበረ ለማድረግ ነው።

15ከተቀደሰው፣ ከተከበረውና ከፍ ካለው ዙፋንህ፣ ከሰማይ ወደ ታች ተመልከት፤ ኀይልህና ቅናትህ የት አለ? ገርነትህና ርኅራኄህ ከእኛ ርቀዋል።

16አብርሃም ባያውቀን፣ እስራኤልም ባያስታውሰን እንኳ፣ አንተ እኮ አባታችን ነህ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ አባታችን ነህ፤ ከጥንትም ቢሆን ስምህ “ቤዛችን” ነው።

17እግዚአብሔር ሆይ፤ ከመንገድህ እንድንወጣ፣ ልባችንን በማደንደን ለምን እንዳንፈራህ አደረግኸን? ስለ ባሮችህ ስትል፣ ስለ ርስትህ ነገዶች ስትል እባክህ ተመለስ።

18ለጥቂት ጊዜ ሕዝብህ የተቀደሰውን ስፍራ ወርሶ ነበር፤ አሁን ግን ጠላቶቻችን መቅደስህን ረገጡት።

19እኛ እኮ ጥንትም የአንተው ነን፤ እነርሱን ግን አንተ አላገዝሃቸውም፤ በስምህም አልተጠሩም።

ማብራሪያ

63:1-6 ነቢዩ በራእይ፣ ጠላቶቹን ድል ነስቶ፣ ኤዶም ምሳሌያቸው የነበረችውን፣ መሲሑን በድል ሲመለስ ይመለከታል። እርሱም በውጊያው የደከመ ሳይሆን፣ ነገር ግን በኃይሉ ታላቅነት፣ ሁሉንም ተቃዋሚ ኃይል ለማሸነፍ ተዘጋጅቶ ሲጓዝ ይታያል። መሲሑ የእግዚአብሔርን ቁጣ የወይን መጥመቂያ እንደረገጠ ያስታውቃል (ራእይ ፲፬፡፲፱፤ ፲፱፡፲፫)፤ በራሱም ኃይል፣ ያለ ምንም ሰብዓዊ እርዳታ፣ ግትር ተቃዋሚዎቹን እንደደቆሰ ይናገራል፤ ምክንያቱም የቤተ ክርስቲያኑን ቤዛነት ለማስፈጸም የተወሰነ የበቀል ቀን ደርሶ ነበርና። አንድ ጊዜ፣ እርሱ ስለ ኃጢአታችን ማስተሰረያ እንዲሆን የከበረ ደሙን ለማፍሰስ፣ በምድር ላይ በግልጽ በሚታይ ድካም ተገለጠ፤ ነገር ግን በተገቢው ጊዜ በኃይሉ ታላቅነት ይታያል። የወይን ፍሬው በፍጥነት እየበሰለ ነው፤ የተወሰነውና የተደነገገው የበቀል ቀን በፍጥነት እየቀረበ ነው፤ ኃጢአተኞች ኃይላቸውን ወደ ምድር ከማምጣቱ በፊት፣ ከጻድቅ ዳኛቸው ጋር እንዲታረቁ ይሹ። ክርስቶስ ‹በቶሎ እመጣለሁ› ይላልን? ልባችንም ‹አዎን፣ ና› ብሎ ይመልስ፤ የቤዛነት ዓመትም ይምጣ።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG ይህ ከኤዶምያስ፥ ልብሱም የቀላ ከባሶራ የሚመጣ፥ አለባበሱ ያማረ፥ በጕልበቱ ጽናት የሚራመድ ማን ነው? በጽድቅ የምናገር ለማዳንም የምበረታ እኔ ነኝ። አማርኛ ENGNIV Who is this coming from Edom, from Bozrah, with his garments stained crimson? Who is this, robed in splendor, striding … English BCV እዝ ካብታ ኣብ ኤዶምያስ ዘላ ኸተማ ባሶራ፥ ቀይሕ ግምጃ ለቢሱ፥ ብኽዳውንቲ ዘጌፀ፥ ምስ ምሉእ ሓይሉን ጕልበቱን እናሰጐመ ዝመፅእ ዘሎ፥ እዙይ መን እዩ? “እቲ ብፅድቂ ዝዛረብ፥ ንምድሓን ም… ትግርኛ GAZBIB Inni uffata dhiiga cuuphame uffatee biyya Edoom keessaa mandara Bozraatii as ba'u kun eenyu” Inni uffata miidhagaa uffa… Afaan Oromoo BCV GIZ መኑ ዝንቱ ዘበጽሐ እምኤዶም ቀይሐ አልባስ እምባሶር መካሕ ብእሲ ወኀያል ወግሩም በልብሰቱ? አንሰ እትዋቀሥ በእንተ ጽድቅ ወእፈትሕ ለአድኅኖ። giz GAZGAZ Inni uffata dhiiga cuuphame uffatee biyya Edoom keessaa mandara Bozraatii as ba'u kun eenyu” Inni uffata miidhagaa uffa… Afaan Oromoo BCV aksum እዝ ካብታ ኣብ ኤዶምያስ ዘላ ኸተማ ባሶራ፥ ቀይሕ ግምጃ ለቢሱ፥ ብኽዳውንቲ ዘጌፀ፥ ምስ ምሉእ ሓይሉን ጕልበቱን እናሰጐመ ዝመፅእ ዘሎ፥ እዙይ መን እዩ? “እቲ ብፅድቂ ዝዛረብ፥ ንምድሓን ም… ትግርኛ SWAHSUV Ni nani huyu atokaye Edomu, Mwenye mavazi ya kutiwa damu kutoka Bosra? Huyu aliye na nguo za fahari, Anayekwenda katika… Kiswahili