ትንቢተ ኢሳይያስ 63

AMHEVGአማርኛ19 ጥቅሶች3:21 አዳምጥ
አዳምጥ 3:21 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ይህ ከኤዶምያስ፥ ልብሱም የቀላ ከባሶራ የሚመጣ፥ አለባበሱ ያማረ፥ በጕልበቱ ጽናት የሚራመድ ማን ነው? በጽድቅ የምናገር ለማዳንም የምበረታ እኔ ነኝ።

2ቀሚስህ ስለ ምን ቀላ? ልብስህስ በወይን መጥመቂያ እንደሚረግጥ ሰው ልብስ ስለ ምን መሰለ?

3መጥመቂያውን ብቻዬን ረግጫለሁ፥ ከአሕዛብም አንድ ሰው ከእኔ ጋር አልነበረም፤ በቍጣዬ ረገጥኋቸው በመዓቴም ቀጠቀጥኋቸው፤ ደማቸውም በልብሴ ላይ ተረጭቶአል፥ ልብሴንም ሁሉ አስድፌአለሁ።

4የምበቀልበት ቀን በልቤ ነውና፥ የምቤዥበትም ዓመት ደርሶአልና።

5ተመለከትሁ፥ የሚረዳም አልተገኘም፤ የሚያግዝም አልነበረምና ተደነቅሁ፤ ስለዚህ የገዛ ክንዴ መድኃኒት አመጣልኝ፥ ቍጣዬም እርሱ አገዘኝ።

6በቍጣዬም አሕዛብን ረገጥሁ በመዓቴም ቀጠቀጥኋቸው፥ ደማቸውንም ወደ ምድር አፈሰስሁት።

7እግዚአብሔር እንደ ሰጠን ሁሉ፥ የእግዚአብሔርን ቸርነትና የእግዚአብሔርን ምስጋና፥ እንደ ምሕረቱና እንደ ቸርነቱም ብዛት ለእስራኤል ቤት የሰጠውን ትልቅ በጎነት አሳስባለሁ።

8እርሱም፦ በእውነት ሕዝቤ፥ ሐሰትን የማያደርጉ ልጆች፥ ናቸው፡ አለ፤ መድኃኒትም ሆነላቸው።

9በጭንቃቸው ሁሉ እርሱ ተጨነቀ፥ የፊቱም መልአክ አዳናቸው፤ በፍቅሩና በርኅራኄውም ተቤዣቸው፥ በቀደመውም ዘመን ሁሉ አንሥቶ ተሸከማቸው።

10እነርሱ ግን ዐመፁ ቅዱስ መንፈሱንም አስመረሩ፤ ስለዚህ ተመልሶ ጠላት ሆናቸው፥ እርሱም ተዋጋቸው።

11እርሱም እንዲህ ብሎ የቀደመውን ዘመን አሰበ፦ የበጎቹን እረኛ ከባሕሩ ያወጣው ወዴት ነው ያለ? ቅዱስ መንፈሱንም በመካከላቸው ያኖረ ወዴት ነው ያለ?

12የከበረውንም ክንድ በሙሴ ቀኝ ያስሄደ፥ ለራሱም የዘላለምን ስም ያደርግ ዘንድ ውኃውን በፊታቸው የከፈለ፥

13በምድረ በዳም እንደሚያልፍ ፈረስ፥ በቀላይ ውስጥ ያለ ዕንቅፋት ያሳለፋቸው ወዴት ነው ያለ?

14ወደ ሸለቆ እንደሚወርዱ ከብቶች፥ እንዲሁ የእግዚአብሔር መንፈስ ወደ ዕረፍት አመጣቸው፤ እንዲሁም ለራስህ የከበረ ስም ታደርግ ዘንድ ሕዝብን መራህ።

15ከሰማይ ተመልከት፥ ከቅዱስነትህና ከክብርህም ማደሪያ ጐብኝ፤ ቅንዓትህና ኃይልህስ ወዴት ነው? ለእኔም የሆነው የልብህ ናፍቆትና ርኅራኄህ ተከለከለ።

16አብርሃም ባያውቀን እስራኤልም ባይገነዘበን አንተ አባታችን ነህ፤ አቤቱ፥ አንተ አባታችን ነህ፥ ስምህም ከዘላለም ታዳጊያችን ነው።

17አቤቱ፥ ከመንገድህ ለምን አሳትኸን? እንዳንፈራህም ልባችንን ለምን አጸናህብን? ስለ ባሪያዎችህ ስለ ርስትህ ነገዶች ተመለስ።

18የተቀደሰው ሕዝብህ መቅደስህን ጥቂት ጊዜ ወረሱት፤ ጠላቶቻችንም ረግጠውታል።

19ከዘላለም እንዳልገዛኸን በስምህም እንዳልተጠራን ሆነናል።

ማብራሪያ

63:1-6 ነቢዩ በራእይ፣ ጠላቶቹን ድል ነስቶ፣ ኤዶም ምሳሌያቸው የነበረችውን፣ መሲሑን በድል ሲመለስ ይመለከታል። እርሱም በውጊያው የደከመ ሳይሆን፣ ነገር ግን በኃይሉ ታላቅነት፣ ሁሉንም ተቃዋሚ ኃይል ለማሸነፍ ተዘጋጅቶ ሲጓዝ ይታያል። መሲሑ የእግዚአብሔርን ቁጣ የወይን መጥመቂያ እንደረገጠ ያስታውቃል (ራእይ ፲፬፡፲፱፤ ፲፱፡፲፫)፤ በራሱም ኃይል፣ ያለ ምንም ሰብዓዊ እርዳታ፣ ግትር ተቃዋሚዎቹን እንደደቆሰ ይናገራል፤ ምክንያቱም የቤተ ክርስቲያኑን ቤዛነት ለማስፈጸም የተወሰነ የበቀል ቀን ደርሶ ነበርና። አንድ ጊዜ፣ እርሱ ስለ ኃጢአታችን ማስተሰረያ እንዲሆን የከበረ ደሙን ለማፍሰስ፣ በምድር ላይ በግልጽ በሚታይ ድካም ተገለጠ፤ ነገር ግን በተገቢው ጊዜ በኃይሉ ታላቅነት ይታያል። የወይን ፍሬው በፍጥነት እየበሰለ ነው፤ የተወሰነውና የተደነገገው የበቀል ቀን በፍጥነት እየቀረበ ነው፤ ኃጢአተኞች ኃይላቸውን ወደ ምድር ከማምጣቱ በፊት፣ ከጻድቅ ዳኛቸው ጋር እንዲታረቁ ይሹ። ክርስቶስ ‹በቶሎ እመጣለሁ› ይላልን? ልባችንም ‹አዎን፣ ና› ብሎ ይመልስ፤ የቤዛነት ዓመትም ይምጣ።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV Who is this coming from Edom, from Bozrah, with his garments stained crimson? Who is this, robed in splendor, striding … English BCV እዝ ካብታ ኣብ ኤዶምያስ ዘላ ኸተማ ባሶራ፥ ቀይሕ ግምጃ ለቢሱ፥ ብኽዳውንቲ ዘጌፀ፥ ምስ ምሉእ ሓይሉን ጕልበቱን እናሰጐመ ዝመፅእ ዘሎ፥ እዙይ መን እዩ? “እቲ ብፅድቂ ዝዛረብ፥ ንምድሓን ም… ትግርኛ GAZBIB Inni uffata dhiiga cuuphame uffatee biyya Edoom keessaa mandara Bozraatii as ba'u kun eenyu” Inni uffata miidhagaa uffa… Afaan Oromoo BCV GIZ መኑ ዝንቱ ዘበጽሐ እምኤዶም ቀይሐ አልባስ እምባሶር መካሕ ብእሲ ወኀያል ወግሩም በልብሰቱ? አንሰ እትዋቀሥ በእንተ ጽድቅ ወእፈትሕ ለአድኅኖ። giz GAZGAZ Inni uffata dhiiga cuuphame uffatee biyya Edoom keessaa mandara Bozraatii as ba'u kun eenyu” Inni uffata miidhagaa uffa… Afaan Oromoo BCV aksum እዝ ካብታ ኣብ ኤዶምያስ ዘላ ኸተማ ባሶራ፥ ቀይሕ ግምጃ ለቢሱ፥ ብኽዳውንቲ ዘጌፀ፥ ምስ ምሉእ ሓይሉን ጕልበቱን እናሰጐመ ዝመፅእ ዘሎ፥ እዙይ መን እዩ? “እቲ ብፅድቂ ዝዛረብ፥ ንምድሓን ም… ትግርኛ AMHNIV ይህ ከኤዶም፣ ቀይ የተነከረ መጐናጸፊያ ለብሶ ከባሶራ የሚመጣ ማን ነው? ይህ ክብርን የተጐናጸፈ፣ በኀይሉ ታላቅነት እየተራመደ የሚመጣውስ ማን ነው? “በጽድቅ የምናገር፣ ለማዳንም ኀይል ያለ… አማርኛ SWAHSUV Ni nani huyu atokaye Edomu, Mwenye mavazi ya kutiwa damu kutoka Bosra? Huyu aliye na nguo za fahari, Anayekwenda katika… Kiswahili