ትንቢተ ኢሳይያስ 56

AMHNIVአማርኛ12 ጥቅሶች2:35 አዳምጥ
አዳምጥ 2:35 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ፍትሕን ጠብቁ፤ መልካሙን አድርጉ፤ ማዳኔ በቅርብ ነው፤ ጽድቄም ፈጥኖ ይገለጣልና።

2ሰንበትን ሳያረክስ የሚያከብር፣ ክፉን ከማድረግ እጁን የሚሰበስብ፣ የሚገታ፣ እነዚህን የሚፈጽም ሰው የተባረከ ነው።”

3ወደ እግዚአብሔር የተጠጋ መጻተኛ፣ “እግዚአብሔር በርግጥ ከሕዝቡ ይለየኛል” አይበል፤ ጃንደረባም፣ “እኔ ደረቅ ዛፍ ነኝ” አይበል።

4እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ሰንበቶቼን ለሚያከብሩ ጃንደረቦች፣ ደስ የሚያሰኘኝን ለሚመርጡ፣ ቃል ኪዳኔን፣ ለሚጠብቁ

5በቤተ መቅደሴና በቅጥሮቼ ውስጥ፣ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች የበለጠ፣ መታሰቢያና ስም እሰጣቸዋለሁ፤ ለዘላለም፣ የማይጠፋ ስም እሰጣቸዋለሁ።

6እርሱን ለማገልገል፣ ራሳቸውን ከእግዚአብሔር ጋር ያቈራኙ መጻተኞች፣ የእግዚአብሔርን ስም በመውደድ፣ እርሱንም በማምለክ፣ ሰንበትን ሳያረክሱ የሚያከብሩትን ሁሉ፣ ቃል ኪዳኔንም የሚጠብቁትን፣

7ወደ ተቀደሰው ተራራዬ አመጣቸዋለሁ፤ በጸሎት ቤቴም ውስጥ ደስ አሰኛቸዋለሁ። የሚቃጠል መሥዋዕታቸውንና ሌሎች መሥዋዕቶቻቸውን፣ በመሠዊያዬ ቢሠዉ እቀበላቸዋለሁ፤ ቤቴ፣ ለሕዝቦች ሁሉ የጸሎት ቤት ተብሎ ይጠራልና።”

8የተበተኑትን እስራኤል የሚሰበስብ፣ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ከተሰበሰቡት በተጨማሪ፣ ሌሎችን እንደ ገና እሰበስባለሁ።”

9እናንት የምድር አራዊት ሁሉ ኑ፤ እናንት የዱር አራዊት ሁሉ ኑና በጥርሳቸሁ ቦጫጭቁ።

10የእስራኤል ጠባቂዎች ዕውሮች ናቸው፤ ዕውቀት የላቸውም፤ ሁሉም ድምፅ የለሽ ውሾች ናቸው፤ መጮኽ አይችሉም፤ ተጋድመው ያልማሉ፤ እንቅልፋሞች ናቸው።

11እጅግ ሲበዛ ሆዳም ውሾች ናቸው፤ ጠገብሁን አያውቁም፤ የማያስተውሉ እረኞች ናቸው፤ ሁሉም በየራሳቸው መንገድ ሄዱ፤ እያንዳንዳቸውም የግል ጥቅማቸውን ፈለጉ።

12እርስ በርሳቸውም፣ “ኑና የወይን ጠጅ እንገባበዝ፤ እስክንሰክር እንጠጣ፤ ነገም ያው እንደ ዛሬ፣ ምናልባትም የተሻለ ቀን ይሆንልናል” ይባባላሉ።

ማብራሪያ

56:1,2 ጌታ ከእኛ የሚጠበቀው ግዴታ ምን እንደሆነ ይነግረናል። በምትሰሩት ሁሉ ታማኞችና ቅኖች ሁኑ። እንዲሁም የሰንበትን ቀን በጥብቅ አክብሩ። በሳምንቱ ሙሉ በምትሰሩት ሥራ ላይ የእግዚአብሔር በረከት እንዲሆንላችሁ፣ ሰንበትን ቅዱስ አድርጎ መጠበቅን የሕሊና ጉዳይ አድርጉ። ከኃጢአት ራቁ። እግዚአብሔርን ከማያስደስቱና ለራሱ ነፍስ ከሚጎዱ ነገሮች ሁሉ እጁን የሚከለክል ሰው ብፁዕ ነው። በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት በእምነት የጽድቅን ተስፋ የሚጠብቁ፣ በቅዱስ ታዛዥነት መንገዶች ሲመላለሱ ይገኛሉ።

56:3-8 አለማመን ብዙውን ጊዜ ምእመናንን ተስፋ የሚያስቆርጡ ነገሮችን ያቀርባል፣ እግዚአብሔር ግን በግልጽ አስቀድሞ ከተከላከለባቸው። መንፈሳዊ በረከቶች ወንዶችና ሴቶች ልጆች ከመውለድ በምንም በማይተመን መልኩ ይበልጣሉ፤ ልጆች እንክብካቤ የሚያስፈልጋቸው ሲሆኑ፣ ሐዘንና ውርደትም ሊሆኑ ይችላሉና፤ በእግዚአብሔር ቤት የምንካፈላቸው በረከቶች…

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6