ትንቢተ ኢሳይያስ 48

AMHEVGአማርኛ22 ጥቅሶች3:38 አዳምጥ
አዳምጥ 3:38 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1እናንተ በእስራኤል ስም የተጠራችሁ ከይሁዳም ውኆች የወጣችሁ፥ በእግዚአብሔር ስም የምትምሉ፥ በእውነት ሳይሆን በጽድቅም ሳይሆን የእስራኤልን አምላክ የምትጠሩ፥

2በቅድስት ከተማ ስም የተጠራችሁ፥ ስሙም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በሚባል በእስራኤል አምላክ የምትደገፉ፥ የያዕቆብ ቤት ሆይ፥ ይህን ስሙ።

3የቀድሞውን ነገር ከጥንት ተናግሬአለሁ፥ ከአፌም ወጥቶአል አሳይቼውማለሁ፤ ድንገት አድርጌዋለሁ ተፈጽሞማል።

4አንተ እልከኛ፥ አንገትህም የብረት ጅማት፥ ግምባርህም ናስ እንደሆነ አውቄአለሁ፤

5ስለዚህ፥ አንተ፦ ጣዖቴ ይህን አድርጎአል፥ የተቀረጸው ምስሌና ቀልጦ የተሠራው ምስሌ ይህን አዘዙኝ፡ እንዳትል፥ አስቀድሜ ነግሬህ ነበር ሳይሆንም አሳይቼህ ነበር።

6ሰምተሃል፤ ይህን ሁሉ ተመልከት፤ እናንተም የምትናገሩት አይደላችሁምን? የተሰወሩትን ያላወቅሃቸውንም አዲሶች ነገሮችን ከዚህ ጀምሬ አሳይቼሃለሁ።

7እነርሱም አሁን እንጂ ከጥንት አልተፈጠሩም፤ አንተም፦ እነሆ፥ አውቄአቸዋለሁ፡ እንዳትል ከዛሬ በፊት አልሰማሃቸውም።

8አልሰማህም፥ አላወቅህም፥ ጆሮህ ከጥንት አልተከፈተችም፤ አንተ ፈጽሞ ወንጀለኛ እንደ ሆንህ ከማኅፀንም ጀምረህ ተላላፊ ተብለህ እንደተጠራህ አውቄአለሁና።

9ስለ ስሜ ቍጣዬን አዘገያለሁ፥ እንዳላጠፋህም ስለ ምስጋናዬ እታገሣለሁ።

10እነሆ፥ አንጥሬሃለሁ ነገር ግን እንደ ብር አይደለም፤ በመከራም እቶን ፈትኜሃለሁ።

11ስለ እኔ፥ ስለ ራሴ አደርገዋለሁ ስሜ ተነቅፎአልና፤ ክብሬንም ለሌላ አልሰጥም።

12ያዕቆብ ሆይ፥ የጠራሁህም እስራኤል ሆይ፥ ስማኝ፤ እኔ ነኝ፤ እኔ ፊተኛው ነኝ እኔም ኋለኛው ነኝ።

13እጄም ምድርን መሥርታለች ቀኜም ሰማያትን ዘርግታለች፤ በጠራኋቸው ጊዜ በአንድነት ይቆማሉ።

14እናንተ ሁሉ፥ በአንድነት ተሰብስባችሁ ስሙ፤ ከእነርሱ ይህን የተናገረ ማን ነው? እግዚአብሔር የወደደው ፈቃዱን በባቢሎን ላይ ያደርጋል፥ ክንዱም በከለዳውያን ላይ ይሆናል።

15እኔ ራሴ ተናግሬአለሁ፤ እኔ ጠርቼዋለሁ፤ አምጥቼዋለሁ፥ መንገዱም ትከናወንለታለች።

16ወደ እኔ ቅረቡ ይህንም ስሙ፤ እኔ ከጥንት ጀምሬ በስውር አልተናገርሁም፤ ከሆነበት ዘመን ጀምሮ እኔ በዚያ ነበርሁ፥ አሁንም ጌታ እግዚአብሔርና መንፈሱ ልከውኛል።

17ታዳጊህ፥ የእስራኤል ቅዱስ፥ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔ የሚረባህን ነገር የማስተምርህ በምትሄድባትም መንገድ የምመራህ አምላክህ እግዚአብሔር ነኝ።

18ትእዛዜን ብትሰማ ኖሮ፥ ሰላምህ እንደ ወንዝ ጽድቅህም እንደ ባሕር ሞገድ በሆነ ነበር፤

19ዘርህም እንደ አሸዋ የሆድህም ትውልድ እንደ ምድር ትቢያ በሆነ ነበር፥ ስሙም ከፊቴ ባልጠፋና ባልፈረሰ ነበር።

20ከባቢሎን ውጡ ከከለዳውያንም ኰብልሉ፤ በእልልታ ድምፅ ተናገሩ ይህንም ንገሩ እስከ ምድርም ዳርቻ ድረስ አውሩና፦ እግዚአብሔር ባሪያውን ያዕቆብን ታድጎታል፡ በሉ።

21በምድረ በዳ በኩል በመራቸው ጊዜ አልተጠሙም፤ ውኃንም ከዓለቱ ውስጥ አፈለቀላቸው፥ ዓለቱንም ሰነጠቀ ውኃውም ፈሰሰ።

22ለክፉዎች ሰላም የላቸውም ይላል እግዚአብሔር።

ማብራሪያ

48:1-8 አይሁድ ከያዕቆብ ዝርያ በመሆናቸው ይኩራሩ ነበር፤ እንዲሁም የእግዚአብሔርን ስም እንደ አምላካቸው ይጠቀሙ ነበር። በኢየሩሳሌም እና በቤተ መቅደሱ ይኮሩ ነበር፤ ሆኖም በሕይወታቸው ውስጥ ቅድስና አልነበረም። በሃይማኖት ቅን ካልሆንን፣ የእግዚአብሔርን ስም በከንቱ እንጠራለን። ከመፈጸሙ ከረጅም ጊዜ በፊት እግዚአብሔር እንዴት እንደሚይዛቸው በትንቢት ተገልጾላቸው ነበር። ሰዎች በራሳቸው እንዳይመኩ ለመገሰጽ እግዚአብሔር በቂ የሆነውን ተናግሮአል እንዲሁም አድርጎአል፤ ይህ ደግሞ የኩሩዎችን ኃጢአትና ጥፋት የከፋ ያደርገዋል። ኋላም ሁሉም አፍ ይዘጋል፣ ሁሉም ከእርሱ ፊት ዝም ይላል። ሁላችንም የተወለድነው የዐመፅ ልጆች ሆነን ነው። የዘር ኃጢአት ባለበት ቦታ ሁሉ፣ የግብር ኃጢአት ይከተላል። የእያንዳንዱ ሰው ሕሊና ለመጽሐፍ ቅዱስ እውነት አይመሰክርምን? ጌታ ይመርምረን፣ የቃሉም ፈጻሚዎች ያድርገን።

48:9-15 እኛ እግዚአብሔር ለምን ምሕረትን እንዲያደርግልን የምንማፀንበት በራሳችን ምንም ነገር የለንም። እርሱ የሚምረውና የሚታገሠው ለራሱ ምስጋና፣ ለምሕረቱ ክብርም ሲል ነው። ሰዎችን በችግር ውስጥ እንዲያልፉ የሚያደርጋቸው ለበጎነታቸው ሲል ነበር። ሊያነጻቸው ነበር፣ ነገር ግን ሰዎች ብርን ሙሉ በሙሉ እንደሚያነጹት አይደለም። እግዚአብሔር ያን እርምጃ ቢወስድ ኖሮ፣ ሁሉም ዝገት ናቸውና በጽድቅ ሊወገዱ ይችሉ ነበር።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV “Listen to this, O house of Jacob, you who are called by the name of Israel and come from the line of Judah, you who ta… English BCV ኣቱም ብስም እስራኤል እትፅውዑ፥ ካብ ዓይኒ ማይ ይሁዳ ዝፈልፈልኩም፥ ብስም እግዚኣብሄር እትምሕሉ፥ ብሓቅን ብፅድቅን ደኣ ኣይኮነን እምበር፥ ንኣምላኽ እስራኤል እትፅውዑ፥ እዙይ ስምዑ። ትግርኛ GAZBIB Yaa ijoollee Yaaqoob warri Israa'el jedhamtan, warri gosa Yihudaa keessaa dhalattan, isin warri maqaa Waaqayyootiin kak… Afaan Oromoo BCV GIZ ስምዑ ዘንተ ቤተ ያዕቆብ እለ ተሰመይክሙ በስመ እስራኤል፤ ወእለ ወጽእክሙ እምይሁዳ፤ ወእለ ትምሕሉ በስመ እግዚአብሔር አምላከ እስራኤል፤ ወተዘከርኩክሙ አኮ በጽድቅ ወአኮ በርትዕ። giz GAZGAZ Yaa ijoollee Yaaqoob warri Israa'el jedhamtan, warri gosa Yihudaa keessaa dhalattan, isin warri maqaa Waaqayyootiin kak… Afaan Oromoo BCV aksum ኣቱም ብስም እስራኤል እትፅውዑ፥ ካብ ዓይኒ ማይ ይሁዳ ዝፈልፈልኩም፥ ብስም እግዚኣብሄር እትምሕሉ፥ ብሓቅን ብፅድቅን ደኣ ኣይኮነን እምበር፥ ንኣምላኽ እስራኤል እትፅውዑ፥ እዙይ ስምዑ። ትግርኛ AMHNIV “የያዕቆብ ቤት ሆይ፤ እናንት በእስራኤል ስም የተጠራችሁ፣ ከይሁዳ ዘር የተገኛችሁ፣ እናንት በእግዚአብሔር ስም የምትምሉ፣ በእውነት ወይም በጽድቅ ሳይሆን፣ የእስራኤልን አምላክ የምትጠሩ ይህ… አማርኛ SWAHSUV Sikieni haya, enyi watu wa nyumba ya Yakobo, mnaoitwa kwa jina la Israeli, mliotoka katika maji ya Yuda; mnaoapa kwa ji… Kiswahili